ኅዳር 6 ፣ 2015

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማ ቆይታ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች

ዜናወቅታዊ ጉዳዮች

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማው ፊት ስለሰላም ንግግሩ፣ ስለምጣኔ ሀብት፣ ስለመልሶ ግንባታ እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን አንሰተዋል። የወልቃይት ጉዳይንም በተመለከተ የተናገሩት አለ።

Avatar: Addis Zeybe
አዲስ ዘይቤ

የኢትዮጵያን አስደናቂ የከተማ ባህል፣ ታሪክ፣ ወቅታዊ ዜና እና ሌሎችንም ያግኙ።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማ ቆይታ የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች

ዛሬ ህዳር 6 ቀን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች እና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። መልስ የሰጡባቸውን ዓበይት ጉዳዮች በዚህ መልኩ አጠናቅረናቸዋል።  

ግብርናን በተመለከተ ኢትዮጵያ፡-

  • ስንዴ ወደውጪ መላክ የምትችልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች 
  • የሩዝ ምርት ከውጪ ማስገባት የምታስቀርበት አቅም ላይ ደርሳለች 
  • የቡና ምርት በዚህ አመት በ20% ያድጋል
  • የግብርናው ዘርፍ ዋና አላማ በሬንና ገበሬን መለያየት እና በሬን ለእርሻ ማዋል ቀርቶ ማድለብ መጀመር ነው

ኢንደስትሪን በተመለከተ፡- 

  • የኢንደስትሪው ዘርፍ 4.9% እድገት ቢያሳይም ከአምናው ቅናሽ አሳይቷል
  • “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚለው ፕሮጀክት የቆሙ ኢንደስትሪዎች ስራ ስለጀመሩ ጥሩ እመርታ አሳይቷል 

አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በተመለከተ፡-

7.6% እድገት አሳይተዋል፤ ዋና ዋናዎቹ፡

  1. የኢትዮጵያ አየር መንገድ - ከኮሮና ጊዜ ጀምሮ ተደራሽነቱ አስፍቷል
  2. ኢትዮቴሌኮም - በለውጡ ማግስት 37 ሚሊዮን የነበሩት ደንበኞች አሁን 68.9 ሚሊዮን ደርሰዋል
  • ተደራሽነት እና ውጤታማነት ላይ ያተኩራል
  • ሞባይል ባንኪንግ ከ25.5 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች አሉት፤ ይህም 134 ቢሊዮን ብር በላይ የንግድ ልውውጥ እንዲካሄድ አስተዋጽኦ አድርጓል
  • በርካታ የግል እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች በቴሌኮም አገልግሎት መጠቀም ጀምረዋል
  1. የፋይናንስ ሴክተር - በ21% እድገት አሳይቷል፣ አጠቃላይ ሃብቱም 2.3 ትሪሊየን ብር ድርሷል።    
  • በባንክ በኩል 82.2 ሚሊየን የባንክ ደንበኞች ተፈጥረዋል
  • 1.6 ትሪሊዮን ብር በባንክ ተቀምጧል
  • ብድር በ29% አድጓል - 353 ቢሊየን ብር ብድር ተሰጥቷል
  • ማክሮ ኢኮኖሚው ከአምናው 6.4% ወደ 7.5% አድጓል

የዋጋ ንረትን በተመለከተ፡-

  • በፍላጎትና አቅርቦት መሃል ካለው ክፍተት በተጨማሪ ጦርነት አባብሶታል። ይህን ለማስተካከልና ገበያን ለማረጋጋት፡
  1. የእሁድ ገበያ - ገበሬው ምርቱን ይዞ የሚቀርብባቸውና ሸማቹን ቀጥታ የሚያገኝባቸው ቦታዎች ተዘጋጅተዋል
  2. የተማሪዎች ምገባ - ኢትዮጵያ በቀን ሁለት ጊዜ 9.5 ሚሊዮን ተማሪዎች ትመግባለች። 
  3. አዲስ አበባ ውስጥ ምንም ገቢ የሌላቸው ከ30 ሺ በላይ ችግረኛ ሰዎች ምሳ የሚበሉበት ቦታም ተዘጋጅቷል። 

ትምህርትን በተመለከተ፡-  

  • ላለፉት 4 አመታት አዲስ ዩኒቨርሲቲ አልተከፈተም። ወደፊትም በቅርቡ አይከፈትም። የሚያስፈልገው አጠቃላይ የትምህርት ስርዓት ለውጥ ነው። 
  • መዋዕለ ህጻናት በብዛት እየተከፈቱ ነው። ገንዘብ፣ ጉልበት፣ ጊዜ መውጣት ያለበት ከመሰረቱ ላይ ነው። 

የዋጋ ግሽበት፡-

  • የገበያ ትስስር ላይ ችግር አለ። ብላቴ የሚበቅል ሙዝና ፓፓያ፣ ጨንቻ እና ጅማ የሚበቅል አፕል አዲስ አበባ ገበያ መድረስ አቅቶት ይበላሻል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ አፕል ከውጪ ታስገባለች። 
  • የሌማት ትሩፋት የተባለ ፕሮጀክት ተጀምሯል። ከመሰረታዊ የምግብ አቅርቦት በላይ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ላይ የሚሰራ ነው። ማር፣ ዶሮ እና እንቁላል እርባታ፣ ላምና እርባታና ወተት አቅርቦት ላይ ይሰራል። 
  • ሩዝ፣ ስንዴ፣ በቆሎ ምርት ላይ በስፋት እየተሰራ ነው።
  • በሚቀጥሉት 4 አመታት እንደ አረንጓዴ ልማትና የከተማ ግብርና ባሉ ፕሮጀክቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ምግብ አጀንዳ እንዳይሆን ይሰራል። 

ለዋጋ ግሽበት መፍትሄ፦

  • ምርታማነትን መጨመር
  • ብክነት መቀነስ
  • ማዕድ ማጋራት
  • ከሌብነት መታቀብ
  • ከግጭት ሰላምን መምረጥ

ከውጪ የሚገቡ ሸቀጦችን እቀባ በተመለከተ፡-

  • ኢትዮጵያ ከውጪ በመደበኛ መንገድ በሚገቡ ሸቀጦች ብቻ ሸቀጦች ብሄራዊ ባንክ የሚያውቀው 18 ቢሊየን ብር ታወጣለች
  • ከ 6000 በላይ ሸቀጦች ከውጪ የሚገቡ ሲሆን አሁን እቀባ የተደረገው 38ቱ ላይ ብቻ ነው
  • እቀባው ለሃገር ውስጥ ምርቶች እድል ይሰጣል፤ ፍራፍሬ፣ ጭማቂ፣ ውሃ፣ ሳሙና በሃገር ውስጥ የሚመረቱ ናቸው። 
  • እቀባው የጥቁር ገበያን ንግድ እንደሚያዳክም ይታመናል
  • እቀባው መሰረታዊ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ ያተኮረ ነው
  • በእቀባው የሚጎዱ ግለሰቦች ቢኖሩም እንደሃገር ግን አትራፊ ነው

ኢንቨስትመንትን በተመለከተ፡-

  • ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት የመንግስትም የህዝብም አይደለም፣ የደላሎች እና የሌባ ሹመኛ ሆኗል፤ ስር ነቀል ማስተካከያ ያስፈልጋል፤ ቢያንስ በከተሞች መሬት የግለሰብ መሆን አለበት። 
  • ኢንቨስተሮች በኢንቨስትመንት ኮሚሽን በኩል ሲስተም ቢስተካከልም ለመጠቀም ተነሳሽነታቸው አነስተኛ ነው፤ የሚፈለገው መሬት ወስዶ፣ መሰረት አውጥቶ፣ ብር ከባንክ መበደር ነው። ይህ መቅረት አለበት።     

የከርሰ ምድር ውሃን በተመለከተ፡-

  • ኢትዮጵያ የከርሰ ምድር ውሃ ሃብት አላት፤ በርካታ ፓምፕ በማስገባት የመስኖና የግድብ ስራዎች እየተሰሩ ነው

ጤናን በተመለከተ፡-

  • እንደትምህርት ስራ ይጠይቃል። የግሉ ዘርፍም መሳተፍ አለበት

ስራ አጥነትን በተመለከተ፡- 

  • ኢትዮጵያ ውስጥ ስራ አለ፣ ሰራተኛም አለ። ሁለቱን ለማገናኘት የሰራተኛና ክህሎት ሚኒስቴር እጅግ አመርቂ ስራ እየሰራ ነው። 
  • የቅጥር መረጃን ዘንድሮ አሳክተናል። በተዘረጋው ሲስተም መሰረት በየቀኑ ስንት ሰው ስራ አገኘ የሚለውን ማወቅ ይቻላል። 
  • በዚህ አመት ከ 3 ሚሊየን በላይ ሰው ስራ ለማስያዝ እየተሰራ ነው
  • የህዳሴ ግድብ፣ የኮይሻ ፕሮጀክት፣ ግብርናው፣ የከተማ ህንጻ ግንባታዎች ስራ ይፈጥራሉ። 
  • የተማረም ያልተማረም ስራ እንዲይዝ ያስፈልጋል፣ ምክንያቱም ዜጋ ስራ ካልያዘ ክላሽ ያነሳል፣ ለሃገር ፈተና ይሆናል። 

ቱሪዝምን በተመለከተ፡-

  • የብልጽግና አእማድ ዋናው አገልግሎት ሰጪ ዘርፉ ነው
  • ላሊበላ በፈረንሳይ መንግስት ድጋፍ እየታደሰ ነው
  • ዩኒቲ ፓርክ ራሱን ችሎ ለኢዮቤልዩ ቤተመንግስትንም እድሳት እያዋጣ ነው። 
  • በርካታ ውድና ታሪካዊ ሃብቶችን የያዘው ኢዮቤልዩ ቤተመንግስት በሚቀጥለው አመት ለህዝብ ክፍት ይሆናል
  • ጎርጎራ ፕሮጀክት እጅግ ግዙፍና ውብ ነው። ሲያልቅ በ30 ደቂቃ የሃይቅ ላይ ጉዞ ዳጋ እስጢፋኖስ መሄድና የፋሲልና ሱስንዮስን መቃብሮች የመሰሉ ታሪካዊ ቦታዎች ማየት ይቻላል
  • አዲስ የተከፈተው ፓርክ በአንድ ሰንበት ብቻ ከመቶ ሺ በላይ ህጻናት ጎብኝተውታል
  • የሃገር ውስጥ ቱሪዝም በዚህ አመት በ8% አድጓል
  • በአዲስ አበባ ከ400-500 ቢሊየን ብር ወጪ የሳተላይት ከተማ እየተገነባ ነው። የሃገር ኩራት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።  

ድርድሩን በተመለከተ፡-

  • “የማያልቅ ጦርነት ውሃ በወንፊት ነው፤ እየተዋጉ መኖር የለም። ሰላምና ብልጽግናን ለማስቀጠል ጦርነት ማቆም አለብን”
  • የኢትዮጵያን ልዕልናና አንድነት የሚገዳደር ነገር መፋለም ያለ የሚኖር ነው፤ ከዚያ በመለስ ደግሞ መነጋገር ያስፈለጋል። 
  • የትግራይ ህዝብ የጥይት ድምጽ አይስማ የተባለው በመንግስት በኩል ከጦርነቱ በፊት ነበር። 
  • “ጦርነቱ ሰሜን ሸዋ ደርሶ ከዚያ ሲቀለበስና እስረኞች ሲፈቱ ብዙዎች ተቀይመዋል። እኛ ግን ይህንን ያደረግነው ከሰላም ስለምናተርፍ ነው
  • “በሰላም የሚጎዳ ኢትዮጵያዊ የለም አይባልም” ከጦርነቱ አትራፊ ነጋዴዎች አሉ። 
  • ሰላም ሲሆን ጦርነት፡ ጦርነት ሲሆን ሰላም የሚሉ “ግራ የሚያጋቡ” አሉ። 
  • “ብዙ ችግር አለብን፤ ነገር ግን  መነጋገር፣ መደማመጥ፣ መልሶ መመርመርና መጨረስ” ያስፈልጋል
  • ተነጋግረው የተስማሙት ሁለቱም ወገኖች ቃላቸውን መጠበቅ አለባቸው። “ተወያይተናል፣ ተስማምተናል፣ ፈርመናል። ለዚህ አበክረን መስራት አለብን”
  • “ህገ መንግስቱ ከአሸባሪ አትደራደር አይልም፤ አታስታጥቅ ነው የሚለው”

ወልቃይትን በተመለከተ፡-

  • ወልቃይትን በተመለከተ ብዙ ሴራዎች አሉ። እነዚህ ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት እጅ የለበትም። 
  • ወልቃይት ለትግራይ ወይም ለአማራ ይሁን የሚል አጀንዳ ፕሪቶሪያ ላይ አልተነሳም፤ ጉራጌ ክልል ይሁን አይሁን የሚለው እንዳልተነሳው ሁሉ። 
  • ህወሃት ከህገመንግስቱ በፊት በሃይል ወልቃይትን ወደትግራይ ጠቅልሏል። ያሁኑ መንግስት ተመሳሳይ ስህተት መስራት አይፈልግም። 
  • ወልቃይት የሁለቱም ህዝቦች ድልድይ ነው። 
  • መንግስት ውስጥ ስራቸውን በትክክል የማይሰሩ ግለሰቦች ቢኖሩም የሰላም ሂደቱ እንዳይሰናከል ጥንቃቄ እየተደረገ ነው። 
  • ብልጽግና ማለት ኢትዮጵያ እንዳልሆነው፣ አብን ማለት አማራ እንዳልሆነው፣ ህወሃትም የትግራይ ህዝብ ማለት አይደለም። ስለዚህ የትግራይን ህዝብ የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ማገዝ አለበት ለመልሶ ግንባታ። 
  • “ትግራይ ገብተን ያየነው ህዝቡ ሰላም፣ ውሃ፣ መብራት እንደሚፈልግ ነው”
  • ህወሃት የአማራን ህዝብ ከወልቃይት ከዚህ በፊት ስላፈናቀለ ሪፈረንደም ቢደረግ አማራ ይጎዳል የሚሉ ወገኖች አሉ፣ አሁን ደግሞ በጦርነቱ የትግራይ ተወላጆች ስለተፈናቀሉ ትግራይ ትጎዳለች የሚሉ ወገኖችም አሉ። 

በጦርነት የተጎዱ ቦታዎችን በተመለከተ፡-

  • መደገፍ፡ እህል በማቅረብ፣ ምርት በመሰብሰብ በሌሎችም መደገፍ
  • መገንባት፡ የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን መልሶ መገንባት 
  • መመለስ፡ በጦርነቱ የተፈናቀሉ ሰዎችን ወደቀያቸው መመለስ ላይ እየተሰራ ነው።    

ኦነግ ሸኔን በተመለከተ፡-

  • “በሽብር የሚገኝ ነጻነት፣ ዲሞክራሲ፣ ዘላቂ ጥቅም የለም”
  • ሸኔ እንኳን ለመንግስት ለሚልኩትም ያስቸገረ የማይጨበጥ፣ ስርዓት የሌለው ቡድን ሆኗል
  • ለኦሮሞ ቆምኩ ቢልም ኦሮሞና ኦሮሚያን እያደናቀፈ ይገኛል
  • ሸኔን ጨምሮ ለማንም የታጠቀ ቡድን ያለን መርህ ተመሳሳይ ነው፤ በትጥቅ የሚመጣ መፍትሄ የለም፣ በንግግር መስማማት ይቻላል።
  • መንግስት ሰፊ ስራ እየሰራ ቢሆንም ስራው ቀላል አይደለም

አዲስ አበባ እንዳይገቡ የተከለከሉ መንገደኞችን በተመለከተ፡-

  • አዲስ አበባ መገደኞች እንዳይገቡ የሚከለከሉት የሽብር ጥቃቶችን ለመከላከል ነው
  • የተከፈላቸውና ለሽብር ስራ የተሰማሩ ወጣቶች አሉ
  • በዚህ ጉዳይ መጉላላት የሚደርስባቸው ዜጎች ቢኖሩም ለሃገር ሰላም ነው ተብሎ መታሰብ አለበት

ሙስናን በተመለከተ፡-

  • ሙስና በጣም ተንሰራፍቷል፤ የተሰረቀን ገንዘብ ወደ ህጋዊ መስመር ማምጣት ይከብዳል
  • “እንደማህበረሰብ ሁሉም ተቋማት ውስጥ ሌብነትን እየተለማመድን ነው”
  • የፍትህ ስርዓቱ ውስጥ ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ ተንሰራፍቷል፣ “በቴሌግራም ቻናል ከፍተው ጉቦ የሚላላኩ ዳኞች አሉ”
  • ይህን ለማጥራት እየተሰራ ነው፣ እንደተፈለገው ግን እየሄደ አይደለም

የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ መርሆች፡-

  • ነጻነት፣ እኩልነትና ፍትሃዊነት 
  • ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ መፈለግ
  • በርካታ ችግር ቢኖርም በጋራ ማሸነፍ (win-win situation)

ዲፕሎማሲን በተመለከተ፡-

  • ባለፉት 3 ወራት ከጎረቤት ሃገራት ጋር አበረታች ለውጥ አለ፣ ሱዳንን ጨምሮ
  • በአለማቀፍ መድረኮች ላይ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጎን ቆማለች፣ ከህወሃት ጋር በተደረገው የመጨረሻ ውጊያም ሱዳን አልተሳተፈችም
  • በሰላም ስምምነቱ ላይ ለተሳተፉ ግለሰቦችና ተቋማት እንዲሁም ሃገሮች ኢትዮጵያ ታመሰግናለች
  • ሁሉም ዜጋ ለሃገሩ ዲፕሎማት መሆን አለበት፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ጭምር
  • የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ባሉበት የውጪ ሃገራት በመንግስት ስራዎች፣ ፓርላማዎች ውስጥ ተመራጭ በመሆን ሃገራቸውን መደገፍ አለባቸው 
  • በ50ዎቹ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚገኙት ከ50 ሺ በላይ ምሁራን በጥናታዊ ስራዎች በዲጂታል አውድ ውስጥ ውጤት ማምጣት አለባቸው
  • “የኢትዮጵያ ታክሲ ማህበራት መንግስት ባይደግፋቸውም መንግስትንና ሃገራቸውን ለመደገፍ ያደረጉትን ጥረት የኢትዮጵያ መንግስት ያመሰግናል”

ብሄራዊ ምክክርን በተመለከተ፡-

  • የምክክር ኮሚቴው አባላት የሚሳካላቸው የህዝብ ድጋፍ ሲያገኙ ነው
  • መንግስት ሙሉ ድጋፍ አለው
  • ምክክሩ በአግባቡ ከሄደ ለኢትዮጵያ ትልቅ እድል ነው፤ 70-80% ችግራችንን ሊያቃልል ይችላል

አስተያየት