አሶሳ በምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ በሀገሪቱ እጅግ በጣም ጥሩ የሚባለውን ማንጎ የምታመርት ከተማ ስትሆን በአከባቢው በባህላዊ መንገድ ተቆፍሮ የሚወጣ ወርቅ የሚሸጥባት ከፍተኛ ማኅበረሰባዊ ትስስር ያለባት ናት፡፡
ወደ ዲዛ ዛፍ ተጠግተው ሲመለከቱ በትልቁ የተቀረፀ አቀራረፅ ቀ.ኃ.ሥ የሚል እና በውል የማይለይ ዓመተ ምህረት ዛፉ ላይ ተቀርፆ ይታያል
ወደ በርታ ማኅበረሰብ የመኖርያ አካባቢዎች በእንግድነት የተገኘ ማንኛውም ሰው የእንግድነት ስሜት አይሰማውም። ነዋሪዎቹ ለአካባቢው እንግዳ የሆነ ሰው ሲመለከቱ እንደ ቅርብ ዘመድ የሞቀ ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ ወደ “አልከልዋ” ይወስዱታል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በምትገኘው ወንበራ ወረዳ የአካባቢው ማኅበረሰብ ወንጀልን ለመከላከል የሚጠቀምበት “ቴራ” የተባለው ባህላዊ ክዋኔ በአካባቢው በሚገኝ ሰፋ ያለ ሜዳ ላይ ሁሉም በተገኘበት እና ስርአት ባለው ሰልፍ የሚደረግ ነው።
በሀገራችን ለ400 ዓመታት ያህል ተለያይተው የቆዩት የጎንጋ እና የሺናሻ ህዝቦች 'የጎንጋ ሕዝቦች ሕዝብ ለሕዝብ ፎረም' በማለት በካፋ ዞን አዘጋጅነት በቦንጋ ከተማ በደማቅ ስነስርዓቶች በመታጀብ የተረሳሱት ወንድማማቾች መገናኘት ችለዋል፡፡