የውሃ መያዣ ፕላስቲኩን ሰማያዊ ቀለም የሚሰጠው ጥሬ እቃ መቅረቱ በዓመት 50 ሚልየን ዶላር እንዲቆጠብ ቢያደርግም ለዋጋው መናር ፋብሪካዎች የችርቻሮ ነጋዴዎችን ይወቅሳሉ
የገንዘብ እጥረት ሲያጋጥም ለብሔራዊ ባንክ ቢያሳውቁም ገና አልተፈቀደም፣ መመሪያ አልተሰጠንም የሚል ምላሽ ማግኘታቸው ታውቋል
በባህር ዳር ከተማና አካባቢዋ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲያለሙ የተሰጣቸውን መሬት ወደ ሪል ስቴት ተቀይሯል በማለት የመሬት ደላሎች እና ባለቤቶች የመሬት ሽያጩን አጧጡፈውታል
“በሃገራችን ኢትዮጵያ የቱሪዝም ሃብቶችን ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ ባለመደረጋቸው ከአካል ጉዳተኞች መገኘት ያለበትን ገቢ እንዲያገኝ የሚያስችል ደረጃ ላይ አልተደረሰም”
የወረታ ደረቅ ወደብ አገልግሎት ምረቃ ስነስርዓት ወቅት የሁለተኛው ዙር ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር በወቅቱ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም እስካሁን የሁለተኛው ዙር ግንባታ አለመጀመሩን አዲስ ዘይቤ ተመልክታለች
ሁለቱ ወገኖች በደላላ መገበያየታቸውን የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ከደረሰበት ደላላው ይከፍል የነበረውን ግብርና ታክስ እጥፍ ሻጭና ገዥ እንዲከፍሉ ይደረጋል
ቴሌብር ከላይ የተጠቀሱትን የብድር እና ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ማንቀሳቀስ የቻለው ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ እንደሆነ መረዳት ተችሏል
የቅባት እህሎችን በስፋት የሚያመርተው የጎንደርና የአካባቢው ህዝብ የምግብ ዘይትን ለማግኘት እየተቸገረ ይገኛል።
የሰራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ አሰራር እና ህግን ተላልፎ የሚገኝ አካል በአዋጅ 618 መሰረት ከ 5 ዓመት ባላነሰ ከ10 ዓመት ባልበለጠ እና 100ሺ ብር መቀጮ ይቀጣል ይላል
ከጥቂት ሺህ ብሮች ጀምሮ እስከመቶ ሰማኒያ ሺህ ብር ድረስ ፊያስ-777 በተባለ ድርጅት ተጭበርብረናል ያሉ ሰዎች በተለያዩ መንገዶች ድምጻቸውን ሲያሰሙ ሰንብተዋል