ከአዲስ አበባ 91.9 ኪሜ ርቀት ላይ ያለች ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የምትገኝ ከተማ ነች። ምስራቅ ኢትዮጵያን ከመዲናይቱ ጋር የምታገናኝ የንግድ እና የትራንስፖርት ከተማ ስትሆን የኮንፈረንስ ቱሪዝም መዳረሻ ነች፡፡
በሰብስቴሽኑ ላይ ብልሽት ሲከሰት የጥገና ቡድኑ ከሻሸመኔ 400 ኪ.ሜ ተጉዞ እስኪደርስ ለቀናት የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ስለሚፈጠር ከፍተኛ የደንበኞችን ቅሬታና ግጭት አስከትሏል
የአካባቢው ህብረተሰብ የንፁህ ውሃ መጠጥ አቅርቦት ጥያቄ ከአዲሱ ፕሮጀክት ጋር ብቻ የሚፈታ እንደሆነ ነዋሪዎችም ሆነ የጉዳዩ ባለድርሻ አካላት ይስማማሉ
የዝርፊያው አጠቃላይ ኪሳራ እየተሰላ እንደሆነ ገልጸው ሁለት የብረት ምሰሶዎች መውደቃቸውንና ሦስተኛው ምሰሶ በሁለቱ መውደቅ ምክንያት መጣመሙን ነግረውናል።
የአዳማ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሕግ ተገዢነት ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ዝናው ደረበ ለአዲስ ዘይቤ እንደተማገሩት የተያዙት እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ ግምት 19 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ነው፡፡
መንገዱ የተዘጋው በኢትዮጵያ ዋነኛ የወጪ ገቢ ንግድ መስመር ላይ በምትገኘው “አውራ ጎዳና” በተሰኘች አነስተኛ መንደር አካባቢ በተነሳ ግጭት ነው። በግጭቱ ምክንያት ዋና ዋና መንገዶች በመዘጋታቸው አሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ አልቻሉም ነበር።
ባሳለፍነው ዓመት በደጋፊዎች እና በቡድኑ ማኔጅመንት መካከል አለመግባባት ካስነሱ ጉዳዮች መሃከል የውጤት ቀውስ ዋነኛው ነው።
የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ከማስተር ፕላን ትግበራ ቁጥጥር ጋር በ17 ቦታዎች ባካሄደው የናሙና ጥናት ዘጠኙ በአግባቡ ጥቅም ላይ ሲውሉ ስምንቱ ከታለመላቸው አገልግሎት ውጭ ውለው መገኘታቸው ታውቋል።
ሞተር ሳይክልን በመጠቀም ሥራቸውን የሚያቀላጥፉ የከተማዋ ነዋሪዎች ለአዲስ ዘይቤ እንደተናገሩት እገዳው በእለታዊ ሥራቸው ላይ ከባድ ተጽእኖ አሳድሯል።
የተለመደ የቀድሞ ሥራቸውን በአዲስ አመራር የቀጠሉት ከአንድ ሺህ በላይ የፋብሪካው ሰራተኞች ከአዲሱ አመራር ጋር አለመግባባት ውስጥ እንደሚገኙ ስማችን እንዳይጠቀስ ያሉ የፋብሪካው ሰራተኞች ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።
የ4መቶ 48 ሺህ ሰዎች የሚኖሩባት አዳማ ከተማ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት የሚሰጡ ሁለት የግል ጤና ተቋማት ይገኙባታል።