ከተሞች
በብሔራዊ ፖሊሲዎች ፣ በአካባቢያዊ ፖለቲካ እና በባህል እና ክልላዊ ጉዳዮች ሰብአዊ መብቶችን ፣ ተጠያቂነትን እና ማህበራዊ ትስስርን በገለልተኛ ሚዲያዎች ለመደገፍ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚቀርብ ዘገባ ፡፡
አዳማ
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHከአዲስ አበባ 91.9 ኪሜ ርቀት ላይ ያለች ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የምትገኝ ከተማ ነች። ምስራቅ ኢትዮጵያን ከመዲናይቱ ጋር የምታገናኝ የንግድ እና የትራንስፖርት ከተማ ስትሆን የኮንፈረንስ ቱሪዝም መዳረሻ ነች፡፡
አዲስ አበባ
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHየኢትዮጵያ መዲና፣ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንዲሁም ሌሎች አለም ዓቀፍ ድርጅቶች መነሐሪያ ስትሆን የኢትዮጵያ ህዝቦች ባህልን ከሌሎች ሀገራት ከመጡ ልማዶች እና የኑሮ ዘይቤ ጋር በአንድ አስተባብራ የያዘች ከባሕር ጠለል በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝ ከተማ ነች፡፡
አሶሳ
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHአሶሳ በምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ በሀገሪቱ እጅግ በጣም ጥሩ የሚባለውን ማንጎ የምታመርት ከተማ ስትሆን በአከባቢው በባህላዊ መንገድ ተቆፍሮ የሚወጣ ወርቅ የሚሸጥባት ከፍተኛ ማኅበረሰባዊ ትስስር ያለባት ናት፡፡
ባህር ዳር
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHየአባይ ወንዝ መነሻ፣ የጣና ሀይቅ መገኛ፣ የሆነችው ባህር ዳር ከተማዋ 37 የደሴቶች ሲኖራት ሀያ አንዱ ደሴቶች ጥንታዊያን ገዳማት ናቸው። ይህ ደግሞ ከተማዋን ቀዳሚ የቱሪስት መስህብ አድርጓታል። ባህር ዳር በብዝሀ ህይወት ጥበቃ በዩኔስኮ ተመዝግባለች።
ቤኒሻንጉል ጉሙዝ
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHቤኒሻንጉል ጉሙዝ በምዕራብ ኢትዮጵያ የምትገኝ ክልላዊ ሃገር ስትሆን ስፋቷ እስከ ሱዳን ድንበር ድረስ ነው። ክልሉ ቀደም ሲል ክልል 6 በመባል የሚታወቅ ሲሆን ዋና ከተማው አሶሳ በመባል ይታወቃል።
ደብረ ብርሃን
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHደብረ ብርሃን በኢትዮጵያ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ የምትገኝ ከተማ ስትሆን ከአዲስ አበባ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ በ 120 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።
ደሴ
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHደሴ በሰሜን መሀል ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ናት። በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ የምትገኘው ደሴ ከመዲናይቱ አዲስ አበባ በስተሰሜን 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። በ30 ቀጠናዎች ውስጥ ከ200,000 በላይ ሰዎች አሏት።
ድሬዳዋ
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHከዚራ ሰፊው መንገድ፣ ኢትዮጵያን ከጅቡቲ የሚያገናኘው የባቡር ሐዲድ እና ታሪኩ፣ የመጋላ ገበያ ስፍራ እንዲሁም የእስልምና የኪነ ህንጻ ጥበቦች በስፋት የሚታዩባት ከተማ ድሬዳዋ መልክ ብዙ እና ልዩ ናት።
ጎንደር
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHጥንታዊና ታሪካዊ ረብ ካላቸው የኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ ስትሆን ስመጥሩ የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት ይዛለች፡፡ ይህም ከተማዋን የቱሪስቶች መነሐሪያ ስትሆን ብዙ ጎብኚዎች በተለይም ለጥምቀት በዓል ወደ ጎንደር ይጎርፋሉ፡፡
ሐዋሳ
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHሐዋሳ ሃይቅን በመታከክ በታላቁ ሪፍት ቫሊ/ስምጥ ሸለቆ ላይ የምትገኝ የመዝናኛ እና የንግድ ከተማ ስትሆን በአሳ ሃብቷ፣ የጅልባ ላይ ሽርሽር፣ ሲዳማ ቡና፣ አሞራ ገደል ውስጥ ያለው የጦጣ ጥበቃ ማዕከሏ እንዲሁም በመጥፋት ላይ ያሉ ብርቅዬ እንስሳቶች መጠበቂያ ማዕከል የሆነውን የሰንቀሌ እንሳት መጠለያ ማዕከልን አካታ ይዛለች።
ጅግጅጋ
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHጅግጅጋ ለጎረቤት ሀገራት ሶማሌላንድ እና ኬንያ ያላት ቅርበት የንግድ እና የተለያዩ ቢዝነሶች ማዕከል አድርጓታል፡፡ በብዛት የሚጎርፉት ብስክሌቶች፣ ከሰዓት በኋላ ያለው ጨዋታ እና የሻይ መጠጣት ልማድ እና በቅርብ የሚታዩት የካራማራ ተራሮች የጅግጅጋ ጌጦች ናቸው፡፡
ጅማ
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHጅማ ወሳኝ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ማዕከል በመሆኗ በርካታ ነጋዴዎች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ይመጣሉ፡፡ ከተማዋ በዙሪያዋ የሚገኘው የቡና እርሻ ተያይዞ የብዙዎች ማረፊያ ናት፡፡
መቐለ
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHሰሜናዊቷ ኮከብ መቀሌ ከተማ ከደናክል ሸለቆ ለጨው ንግድ ብለው የሚመጡ በርካታ ነጋዴዎችን ታስተናግዳለች። ከተማዋ የአፄ ዮሀንስ አራተኛው ቤተ-መንግስትን ጨምሮ የሰማዕታት መታሰቢያ ሀውልት ይገኙባታል።
ሶማሌ
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHየሶማሌ ክልል ከኦሮሚያ ክልል ቀጥሎ ትልቁ ነው። እንዲሁም በሰሜን ጅቡቲ እና ሶማሌላንድ፣ ሶማሊያ በምስራቅ እና በደቡብ; እና ኬንያ በደቡብ ምዕራብ። ጅጅጋ የሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ነች።
ሰመራ
0 ARTICLES IN THE PAST MONTHሠመራ በሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ የአፋር ክልል ዋና ከተማ የሆነችውን አሳይታ ለመተካት አዲስ የተመሰረተች ከተማ ነች። ሰመራ በማደግ ላይ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ ነች። ዱብቲ፣ አሳይታ እና ሎጊያ ሰመራን የሚያዋሰኑአት ከተሞች ናቸው።