የአባይ ወንዝ መነሻ፣ የጣና ሀይቅ መገኛ፣ የሆነችው ባህር ዳር ከተማዋ 37 የደሴቶች ሲኖራት ሀያ አንዱ ደሴቶች ጥንታዊያን ገዳማት ናቸው። ይህ ደግሞ ከተማዋን ቀዳሚ የቱሪስት መስህብ አድርጓታል። ባህር ዳር በብዝሀ ህይወት ጥበቃ በዩኔስኮ ተመዝግባለች።
ከባህር ዳር- ጎንደር ተጓዦች ለሚከፍሉት ከታሪፍ በላይ ክፍያ ራሳቸው ተባባሪ ሰለመሆናቸው ተገልጿል
ከ28 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ተቸግረው የሚገኙበት ደብረብርሃን ከተማ ከአዲስ አበባ ዙሪያና ከኦሮሚያ ክልል አዲስ ተፈናቃዮች በመምጣታቸው የየከተማ አስተዳደሩ ከአቅሜ በላይ ነው አለ
በወልዲያ ከተማ ዙሪያ በቅርብ ርቀት በምትገኜው ጎብየ ተብላ በምትጠራ ቦታ በልዩ ሃይሎችና በሃገር መከላከያ ሰራዊት መካከል ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር ነዋሪዎች ገልፀዋል
በጣና ሀይቅ የተስፋፋው የእምቦጭ አረም ከሐይቁ ደህንነት አለፎ በሀይቁ ዓሳ ምርት እንዲቀንስ ማድረጉ ተነገረ
በአማራ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ 103 ዳኞች ሥራ መልቃቸውን ተከትሎ በክልሉ ከ937 በላይ ክፍት የዳኛ መደቦች መፈጠራቸውን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሪፖርት ያሳያል።
በክልል ደረጃ የፀረ ሙስና ኮሚቴ ከመቋቋሙ በፊት ከ70 በላይ ጥቆማዎች ለኮሚሽኑ ደርሰው የነበረ ሲሆን ኮሚቴው ከተቋቋመ በኋላ ግን በጥቆማ መስጫ ሳጥን የደረሱ ጥቆማዎች ከ12 አይበልጡም
“ለውሃ መሳቢያ ማሽን ቤንዚን አጥቼ በጥቁር ገበያ እየገዛሁ ያመረትኩትን ስንዴ በፈለኩት ዋጋ ለፈለኩት አካል መሸጥ እፈልጋለሁ”- አርሶ አደር
በማህበር የተደራጁ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ሲሰጣቸው በማስረጃ የተደገፈ ፍተሻ ተደርጎ ተረጋግጦ ቢሆንም አሁን በድጋሜ ለማጣራት በሚል ሰበብ መታገዳቸውን ቅሬታ አቅርበዋል
የጣናነሽ በ1957 ዓ.ም በጀርመን ሀገር እንደተሰራችና በ1960 ዓ.ም መጀመሪያ ወደ ሀገር ወስጥ እንደገባች ይነገራል
በእንጅባራ ከተማ ዓመታዊውን የፈረሰኞች ትርዒት የሚወክልና ለጎብኚዎች ክፍት የሚሆን የፈረስ ትርዒት ማዕከል ለመገንባት ዝግጅት መደረጉን ሰምተናል