ደሴ በሰሜን መሀል ኢትዮጵያ የምትገኝ ከተማ ናት። በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ የምትገኘው ደሴ ከመዲናይቱ አዲስ አበባ በስተሰሜን 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች። በ30 ቀጠናዎች ውስጥ ከ200,000 በላይ ሰዎች አሏት።
ልጅ ሆኜ የቆሎ ተማሪ እያለሁ እርሳቸው የሚተክሉትን ችግኝ ከወንዝ ውሃ እያመጣን በማጠጣት እናግዛቸው ነበር። ተግባሩን ልማድ አድርጌው አሁን ድረስ ችግኝ እተክላለሁ ~መሪጌታ እዝራ በአምላኩ
የወይባ ጭስ በወሊድ ውቅት ማህፀን አካባቢ የሚፈጠር ቁስለት ቶሎ እንዲደርቅና እንዲድን ከማድረጉ ባሻገር ለመልካም ጠረንና ለሰውነት ጥራት እንደሚጠቅም በማህበረሰቡ ይታመናል
የስነ ቃል ግጥሞች ለገበሬው ኃሳቡን የመግለጽ፣ የመንገር፣ የማነቃቃት፣ የማስተማር፣ የማሳወቅ፣ የማዝናናት ሚና ያላቸው ሃብቶቹና ገጠመኙን ማድመቂያ ጌጦቹ ናቸው
ቃልኪዳን ችግኞቹን የተከለችባቸው ቦታዎች ከከተማ የራቁ በመሆናቸው ዳግም ሄዳ ለማየት ባትችልም፤ ችግኞቹን ለመንከባከብ ግን ፍላጎት አላት።
ባለሃብቶች የሚገጥሟቸው የመልካም አስተዳደር ችግሮች እና መሬት ካገኙ በኋላም ቶሎ ወደስራ አለመግባታቸው ለኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው ማነቆ ሆኗል
በክልል ደረጃ በሞዴልነት ተሸላሚ የነበረው ይህ የተፋሰስ ልማት በውሃ እጥረት ምክንያት የለሙት የፍራፍሬ ዛፎች ጠውልገው፣ ከፊሎቹም ደርቀዋል
አሽከርካሪዎች በህገወጥ ቀረጡ በመማረር ስራ እያቆሙ ይገኛሉ
የአዳራሹ ግቢ ኮረብታማ ቦታ ላይ በመመስረቱ በጦርነት ጊዜ ጠላትን ለማጥቃት አመች እንደሆነ ይነገራል
ሼዶቹ ለተጠቃሚ ሲተላለፉ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለተሰማሩ አንቀሳቃሾች ተብሎ ቢሆንም አብዛኞቹ ከታለመላቸው ዓላማ ውጭ መኖሪያ ቤት፣ መቃሚያ ቤት፣ መጠጥ ቤት ሆነዋል።
በደሴ ከተማ ውስጥ የሚገኙ 88 ኢንተርፕራይዞች የወሰዱትን የተዘዋዋሪ ፈንድ ብድር መክፈል አልቻሉም።