ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ 150 ሚልየን ዶላር የከፈለበትን የሞባይል ገንዘብ ዝውውር አገልግሎት በቅርብ ሳምንታት ውስጥ የሚጀምር ሲሆን በሚቀጥለው ዓመት 10 ሚልየን ደንበኛ ለመድረስ አቅዷል
በመምህርነት ለ25 ዓመታት ያገለገሉ አንድ አስተማሪ በጦርነቱ ሳቢያ ክፍያቸው በመቋረጡ ስድስት ቤተሰቦቻቸውን ለማስተዳደር የጉልበት ሰራተኛ ሆነዋል፣ ለረሃብና ሞት የተዳረጉም መኖራቸው ተሰምቷል
በየቀኑ እስከ 100 የሚደርሱ አህያዎች በኢትዮጵያ እንደሚታረዱ የተገለፀ ሲሆን በዚህ ከቀጠለ ሀገሪቱን አህያ ከማሳጣት ባለፈ የስራ ጫናዎችን በመፍጠር ማህበራዊ ቀውስም ሊያስከትል ይችላል
በሐዋሳ፣ በባህር ዳር፣ በአዳማ እና በጎንደር ከተሞች ባደረግነው ቅኝት በሌላ ዘርፍ የንግድ ፈቃድ ወስደዉ በድብቅ የነዳጅ ምርቶችን የሚሸጡ ነጋዴዎች መኖራቸውን አረጋግጠናል
በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ባትሪዎች ከውጭ የሚመጡ ሲሆኑ በሀገር ውስጥ ጠግኖ ወደ ምርት የሚመልሰው ብቸኛው አዋሽ ባትሪ በአሁኑ ወቅት በስራ ላይ አይገኝም።
የወረታ ደረቅ ወደብ አገልግሎት ምረቃ ስነስርዓት ወቅት የሁለተኛው ዙር ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር በወቅቱ ተገልጾ የነበረ ቢሆንም እስካሁን የሁለተኛው ዙር ግንባታ አለመጀመሩን አዲስ ዘይቤ ተመልክታለች
ህገ ወጥ የነዳጅ ሽያጭ እና ክምችት መበራከቱ ስጋት ፈጥሯል። አሽከርካሪዎች በነዳጅ እጦት ሳቢያ ከህገ ወጥ ነጋዴዎች በእጥፍ መግዛት እና ህገ ወጥ ነዳጅ ክምችት ባለባቸው አካባቢዎች የአደጋዎች መከሰት ዋነኛ ችግር ሆነዋል።
“ሀረ ሸይጣን” ማለት የሰይጣን ሀይቅ ወይም የሰይጣን ውሃ ማለት እንደሆነ በአፈታሪክ ሲነገር ቆይቷል። ዛሬም ብዙዎቹ የአካባቢው ነዋሪዎች ሀይቁን በሩቁ ያዩታል እንጂ አይቀርቡትም
በአራት ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው የዋጋ ጭማሪ ከ57 በመቶ እስከ 90 በመቶ የሚደርስ ጭማሪ አለው።
በ2014 ዓ.ም. 33 ሚልየን ብር ለማትረፍ አቅዶ የነበረው ድርጅት በግብዓት እጥረትና ስራ ማቆም ምክንያት 5.3 ሚልየን ብር መክሰሩን ገልጿል።