ሐዋሳ ሃይቅን በመታከክ በታላቁ ሪፍት ቫሊ/ስምጥ ሸለቆ ላይ የምትገኝ የመዝናኛ እና የንግድ ከተማ ስትሆን በአሳ ሃብቷ፣ የጅልባ ላይ ሽርሽር፣ ሲዳማ ቡና፣ አሞራ ገደል ውስጥ ያለው የጦጣ ጥበቃ ማዕከሏ እንዲሁም በመጥፋት ላይ ያሉ ብርቅዬ እንስሳቶች መጠበቂያ ማዕከል የሆነውን የሰንቀሌ እንሳት መጠለያ ማዕከልን አካታ ይዛለች።
ዉሽዉሽ ሻይ ልማት ድርጅት ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል አረንጓዴ ሻይ ቅጠል በኪ.ግ በ4.92 ብር እንዲሁም ለውጭ ገበያ ደግሞ በ7.38 ብር ከአርሶ አደሮቹ ላይ ይረከባል።
በሃይቁ በቀን ብቻ ሳይሆን በለሊትም በዓሳ ማስገር ስራ የተሰማሩ ሰዎች ሲኖሩ የቀናቸው ከ200-300 ዓሳ፤ ያልቀናቸው ባዶ እጃቸውን የሚመለሱም አሉ
ለተለያዩ የጤና እክሎች “ፈዉስን” በሚሰጠው ሾርባቸው የተነሳ “ዶክተር” የሚል ቅፅል ስያሜ ከደንበኞቻቸው ያገኙት መርሳሞ መንግስቱ ለ22 ዓመታት በዚህ ስራ ላይ ቆይተዋል
“ግርማ ሰዐቱ” በመባል የሚታወቁት አቶ ግርማ ተስፋዬ ሰዓት እና ደቂቃ ሳይሳሳቱ የሚናገሩ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ ናቸው
የጉራጌ ዞን የሰባት ጎጎት ዶቢ ክስታኔ ማኅበረሰብ በመሰቃን ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በስሩ 16 ቀበሌያትን አቅፎ ይዟል። ከእነዚህ ውስጥ ጀሌ 1፣ 2 እና 3፣ ወገራም አንድ እና ሁለት፣ ድራማ፣ ይመርቾ አንድ እና ሁለት ተጠቃሽ ናቸው።
አሪ ወረዳ ወደ ዞን እንዲያድግ የቀረበው ጥያቄ መልስ ሳይሰጥበት ዘግይቷል በሚል ሰበብ የተነሳው ግጭት በአካባቢው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ምክንያት ሆኗል።
የሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ በሆነችው ጪሪ ወረዳ የተነሳው ግጭት ወደ ዳኤላ እና ሌሎች አጎራባች ወረዳዎች በመስፋፋት ላይ እንደሚገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያዊያንን ጥንታዊ የቤት አሰራር ስልት ተከትሎ የተገነባው “ቦንጋ ብሄራዊ የቡና ሙዚየም” ከአዲስ አበባ በ457 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ቦንጋ ከተማ ውስጥ ይገኛል።
በኦሞ ወንዝ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ዙሪያ ያሉ ቀበሌዎች ለከፍተኛ የምግብ እና የንፁሕ መጠጥ ውሃ ችግር ሰለባ እንደሆነ ሰምተናል።
ከሃይላንድ እና ከጄሪካን መፍጫ ማሽን በተጨማሪ በ30 ደቂቃ ውስጥ ከሁለት እስከ ሰባት ሺህ ሊትር ፈሳሽ ሳሙና ማምረቻ ማሽን፣ ደረቅ ሳሙና ማምረቻ፣ ፕላስተር መስሪያ ማሽን ሰርተዋል።