ጥንታዊና ታሪካዊ ረብ ካላቸው የኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ ስትሆን ስመጥሩ የአፄ ፋሲለደስ ቤተ መንግሥት ይዛለች፡፡ ይህም ከተማዋን የቱሪስቶች መነሐሪያ ስትሆን ብዙ ጎብኚዎች በተለይም ለጥምቀት በዓል ወደ ጎንደር ይጎርፋሉ፡፡
የሃይል አለመመጣጠን የውሃ መሳቢያ ማሽኖች ላይ ጉዳት በማድረሱና በጀኔሬተር አገልግሎት ለመስጠት በቀን ከ600 ሊትር በላይ ናፍጣ የሚጠይቅ በመሆኑ አገልግሎቱ ተቋርጧል
የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በሚል ትላንት ሚያዚያ 1 ቀን 2015 ክልከላዎች ሲያስቀም የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስን ከልክሏል፡፡
ከ600 በላይ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የገባ ሲሆን ይህ ዘገባ እስከወጣበት ሰዓት ድረስ እሳቱን ማጥፋት እንዳልተቻለ ኃላፊው ተናግረዋል
በአንድ በኩል የልዩ ኃይል እና ፋኖ ትጥቅ መፍታት ጉዳት ሊያስከትል ይችላል የሚሉ የመኖራቸውን ያህል ይህ ውሳኔ የክልሉን ነዋሪዎች ለመጉዳት ያለመ አይደለም የሚሉም አሉ
ለሁለት ዓመታት በትግራይ ሃይሎች ቁጥጥር ስር የነበሩት ኒሯቅ እና አበርገሌ ከተማዎች በዚህ ሳምንት መለቀቃቸውን ተከትሎ ከ67 ሺህ 961 በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው ሊመለሱ ነው
ሰሃላ ሰየምት ወረዳን ከሰቆጣ የሚያገናኘው የብረት ድልድይ ተደርምሶ ባለመጠገኑ እናቶች የወሊድ አገልግሎት ለማግኘት ከ300 ኪሎ ሜትር በላይ ለመጓዝ እየተገደዱ ነው
በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ በጎንደር ከተማ በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ተገንብቶ የካቲት 15/2015 ዓ.ም የተመረቀው የዳቦ ፋብሪካው ስራ አለመጀመሩ ተሰምቷል ፡፡
ሴትን ልጅ ለአቅመ ሔዋን ሳትደርስ ትዳር እንድትመሰርት በሚደረግበት የጎንደር እና አካባቢው ማህበረሰብ መንግስት ያለ እድሜ ጋብቻን ለማስቀረት ለሚደረገው ጥረት ፈተና እንደሆነበት ይገልፃል
በከተማው ነዋሪዎች ለጎንደር በመሰረተ ልማት ወደኋላ መቅረት ተጠያቂ የሚደረጉት በፍጥነት የሚቀያየሩት ከንቲባዎች ናቸው፣ በዚህ ወቅት በይፋ የተሾመ ከንቲባ የላትም
50 ሜትር ርዝመት፣30 ሜትር የጎን ስፋት እና 3 ሜትር ገደማ ጥልቀት ያለው ጥምቀተ ባህሩ በዩኔስኮ ተመዝግቦ ይገኛል