ሚያዝያ 2 ፣ 2015

በጎንደር ከተማ ከፀጥታ ኃይሎች ውጪ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ታገደ

City: Gonderወቅታዊ ጉዳዮች

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በሚል ትላንት ሚያዚያ 1 ቀን 2015 ክልከላዎች ሲያስቀም የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስን ከልክሏል፡፡

Avatar: Addis Zeybe
አዲስ ዘይቤ

የኢትዮጵያን አስደናቂ የከተማ ባህል፣ ታሪክ፣ ወቅታዊ ዜና እና ሌሎችንም ያግኙ።

በጎንደር ከተማ ከፀጥታ ኃይሎች ውጪ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ ታገደ

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በሚል ትላንት ሚያዚያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ከተፈቀደለት የመንግስት የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስን ከልክሏል።

በከተማው ያሉ ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ብቻ እንዲሰሩ ሲፈቀድ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ3 እግር ተሽከርካሪ ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት  መንቀሳቀስ ተከልክለዋል፡፡

በተጨማሪም ድምፅ አልባ መሳሪያዎችና ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ሲሆን በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ ስለመከልከሉ ይፋ አድርጓል፡፡

በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ የከለከለ መሆኑንና በተከለከሉ ቦታዎች በእምነት ተቋማት፣ በገቢያዎች፣ ህዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ፣ በሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና ግሮሰሪዎች፣ ልዩ ልዩ መዝናኛ ቦታዎች ጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ብሏል ኮማንድ ፖስቱ።

ከዚህ ባለፈ የሠራዊቱን ሚሊተሪ ማለትም -የልዩ ኋይል ፣የፓሊስ ፣የመከላከያ ሠራዊት ፣ የፌዴራል ፓሊስን አልባሳት ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው ፦ 

ኮማንድ ፖስቱ ያልተፈቀዱ ስብሰባዎችን ማለትም ከመንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት ስለመከልከሉና አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ ክልክል ነው ብሏል።

የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈላችሁ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስታችሁ ወደ ከተማችን የመጣችሁ በከተማችን በተዘጋጀው ማረፊያዎች እንድትሰባሰቡ እያሳሰብን ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ የተከለከለ ነው ተብሏል።

ኮማንደ ፖሰቱ ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ  እንዲሁም  ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል ነው ያለው።

ይሁን እንጅ አሁንም የተኩስ ድምጽ በከተማዋ እንደሚሰማ የአይን እማኞች ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል፡፡

አስተያየት