ሐዋሳ ሃይቅን በመታከክ በታላቁ ሪፍት ቫሊ/ስምጥ ሸለቆ ላይ የምትገኝ የመዝናኛ እና የንግድ ከተማ ስትሆን በአሳ ሃብቷ፣ የጅልባ ላይ ሽርሽር፣ ሲዳማ ቡና፣ አሞራ ገደል ውስጥ ያለው የጦጣ ጥበቃ ማዕከሏ እንዲሁም በመጥፋት ላይ ያሉ ብርቅዬ እንስሳቶች መጠበቂያ ማዕከል የሆነውን የሰንቀሌ እንሳት መጠለያ ማዕከልን አካታ ይዛለች።
የሲዳማ ክልል ከኦሮሚያ ከሚያዋስናቸዉ አከባቢዎች ወቅትን እየጠበቁ በተደጋጋሚ ለሚነሱት ግጭቶች ተጠያቂዉ የሁለቱ ክልል አመራሮች ናቸዉ ሲሉ ነዋሪዎች ለአዲስ ዘይቤ ተናገሩ ።
ያለፍርድ ቤት ማዘዣ ከሌሊቱ 9 ሰዓት ላይ ወደ 42 የሚጠጉ ልዩ ኃይሎች “አጥር ዘለዉ ገብተዉ የክልልነት ጥያቄን ደግፈሻል በሚል ነፍሰጡር እህቴን ወስደዋታል- የዞኑ ነዋሪ
የዎህዴግ አመራሮች የቀድሞ እና አዲሶቹ በሚል ተከፋፍለው ህብረተሰቡን በመከፋፈል እና ፓርቲዉን በማፍረስ በሚል እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ ሲሆን ከአመራርነት ታግደዋል የተባሉ አመራሮች እግዳውን አልተቀበሉም
በተደረገው ጥናት መሰረት ዝቅተኛው የቤት ኪራይ አበል 3 ሺህ ብር የነበረ ቢሆንም ተግባራዊ ይደረጋል በተባለው ስሌት ግን 1 ሺህ ብር ዝቅተኛው መሆኑን የጥናት ቡድኑ አባል ገልፀዋል
የውሃ መያዣ ፕላስቲኩን ሰማያዊ ቀለም የሚሰጠው ጥሬ እቃ መቅረቱ በዓመት 50 ሚልየን ዶላር እንዲቆጠብ ቢያደርግም ለዋጋው መናር ፋብሪካዎች የችርቻሮ ነጋዴዎችን ይወቅሳሉ
በገዢዉ ብልፅግና ፓርቲ አማካኝነት የቀረበዉ የክላስተር አደረጃጀት የመፍትሔ ሀሳብ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ያልተከተለ እና መንግስት በሚፈለገው መንገድ ብቻ እያስኬደዉ የሚገኝ በመሆኑ “ሊቆም ይገባል” ተብሏል
70 አባላት የሚኖረው የብሔረሰቦች ምክር ቤት የክልሉን ህገመንግስት መተርጎም፣ አጣሪ ጉባኤ ማደራጀት እንዲሁም በአስተዳደር እርከኖች መካከል የሚነሱ ችግሮችን መፍታት ከተሰጡት ስልጣኖች ዋነኞቹ ናቸው
አንድ ተቋም አዲስ ሰራተኛ የሚያስፈልገው ከሆነ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥያቄ አቅርቦ ካቢኔዉ ካመነበትና ዉሳኔ ከተሰጠበት ነው አዲስ ቅጥር የሚፈፀመው
መንግስት ለዩኒቨርሲቲ መምህራን እና የቴክኒክ ረዳቶች ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ “የሶስት ሳምንታት ጊዜ ለመስጠት” በሚል አድማው መቋረጡ ተሰምቷል። የስራ ማቆም አድማውን መቋረጥ ያልደገፉ መምህራንም ቅሬታቸውን እየገለፁ ነው።
የሚመረቁበት ጊዜ በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ሳቢያ የተራዘመባቸው ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርት አንገባም ብለዋል። ዩኒቨርሲቲው በበኩሉ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ምንም አልተፈጠረም ብሏል።