(አዲስ ዘይቤ - አዳማ ) በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዳማ ከተማ አስተዳድር የመሬት ይዞታን ለማዘመን 940 ህገወጥ ቤቶች ትናንት ማፍረስ ተጀምሯል፡፡
የአዳማ ከተማ የመሬት አስተዳደር ሃላፊ አቶ ደስታ መርጋ ስራዉ ከነዋሪዎቹ ጋር በመነጋገር እና በመተባበር መሳካቱን ገልፆ ቤት ለፈረሰባቸው ነዋሪዎችም በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ችግሩን በማስተካከል አዲስ ቦታ ከነካርታ እና ፕላን እንደሚያስረክቡ አክሏል።
ቤት የፈረሰባቸው ነዋሪዎችም ይህ ተግበራ እስኪጠናቀቅ ድረስ አቅም ያላቸው ሰዎች በኪራይ እንዲቆዩ አቅም የሌላቸው ደግሞ በላስቲክ ቤት ተጠልለው በመቆየት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ካርታ እና ፕላን እንደሚረከቡ ገልፀዋል ።
የማህበረሰቡ አባላትም “ለዘመናት እኛ ሳናውቅ ያፈርሱብናል ብለን ስንሳቀቅ ነበር ነገር ግን አሁን ክቡር ከንቲባውም በተገኙበት ምክክር አድርገን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የቤት ባለቤት መሆናችንን አረጋግጠውልናል በዚህ ሂደት ተስማምተን እያፈረስን እንገኛለን”
ሲሉ ሃሳባቸውን ተናግረዋል ።
«የከተማዋ ህብረተሰብ በራሳቸው ተነሳሽነት ህገወጥ የነበረውን መሬት ወደ ህጋዊነት ካዳስተር ሲስተም ለማምጣት እና የከተማዋን ገፅታ ከማዘመን አኳያ ቤቶቹ እንዲፈርሱ መወሰናቸዉ ትልቅ ስራ ነው፡፡» ያሉትየአዳማ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሀይሉ ጀልዴም፡፡
አክለውም በአጭር ጊዜ ውስጥ የመሬትን አቅርቦት በፍጥነት በማመቻቸት የመሬቱን ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ለመስጠት እንዲሁም የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት እንደሚረጋገጥ አመላክተዋል።
ኅዳር 25 ፣ 2013
አዳማ ከተማ፡ መስተዳደሩ 940 ህገወጥ ቤቶችን ማፍረስ ጀመረ
(አዲስ ዘይቤ - አዳማ ) በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አዳማ ከተማ አስተዳድር የመሬት ይዞታን ለማዘመን 940 ህገወጥ ቤቶች ትናንት ማፍረስ…