ጥር 12 ፣ 2015

ለአዘርባጃን ነፃነት ፈር የቀደደው የጥር 12ቱ አሰቃቂ ክስተት

ማስታወቂያ

አሳዛኝ በሆነው ነገር ግን እንደ ብሄራዊ ኩራት በሚቆጠረው ጥር 12 1982 ዓ.ም የአዘርባጃን ሕዝብ ነፃ፣ ሉዓላዊ እና ገለልተኛ ሆኖ መኖር እንደሚገባው ለዓለም አስታውቋል

Avatar: Addis Zeybe
አዲስ ዘይቤ

የኢትዮጵያን አስደናቂ የከተማ ባህል፣ ታሪክ፣ ወቅታዊ ዜና እና ሌሎችንም ያግኙ።

ለአዘርባጃን ነፃነት ፈር የቀደደው የጥር 12ቱ አሰቃቂ ክስተት
Camera Icon

ፎቶ፡ ከበይነ መረብ ምንጮች (እልቂቱን ተካትሎ የአዘርባጃን ብሄራዊ መሪ ሃይዳር አሊዬቭ ለህዝቡ ንግግር ሲያደርጉ)

በጥር 12 1982 ዓ.ም ምሽት ላይ በሶቪየት ጦር ሠራዊት እና በልዩ ኃይሎች እንዲሁም የውስጥ ተጠባባቂ ወታደሮች በሶቭዬት አመራሮች ትእዛዝ በአዛርባጃን ላይ በተፈጸመ ወታደራዊ ጥቃት በባኩ ፣ ሱምጋይት ፣ ላንካራን እና ኔፍታቻላ ከተሞች ሕፃናትን ፣ ሴቶችን እና አዛውንቶችን ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎች ተጨፍጭፈዋል።

በወራሪዎቹ በተደረገ ወታደራዊ ጥቃት 150 ንፁሀን ዜጎች ተገድለዋል። በተጨማሪም 744 ሰዎች ከባድ ጉዳት ሲደርስባቸው 4 ሰዎች ደግሞ ደብዛቸው ጠፍቷል።

በሶቭዬት ህብረት አመራር በሚደርስበት አድሏዊ ፖሊሲ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አዛርባጃናውያን ከታሪካዊ መሬታቸው (የአሁኑ አርሜኒያ) በጉልበት በመፈናቀላቸው፣ አርሜኒያ በካራባኽ ላይ መሰረተ ቢስ የግዛት ይገባኛል ጥያቄ በማንሳቷ ምክንያት በአዛርባጃን የተለኮሰውን ብሄራዊ የነጻነት እንቅስቃሴን በኃይል ለመደፍጠጥ በማሰብ ወደ አዛርባጃን  የተላከው የሶቭየት ጦር የዓለም አቀፍ ህጎችን እና ህገ-መንግስቱን በከፍተኛ ሁኔታ በመጣስ በሰላማዊ ህዝብ ላይ ታይቶ የማይታወቅ እልቂት ፈጽሟል።

ይህ ዘግናኝ ክስተት እንደተከሰተ በጥር 13 1982 ዓ.ም በሞስኮ የአዘርባጃን ቋሚ መልዕክተኛ የአዛርባጃን ብሔራዊ መሪ ሃይደር አሊዬቭ በአዘርባጃን ህዝብ ላይ የተፈፀመውን ወንጀል አጥብቆ በማውገዝ ፖለቲካዊ እና ህጋዊ ምርመራ እንዲደረግና  የጅምላ ጭፍጨፋውን የፈጸሙ ወንጀለኞች እንዲቀጡ ሲሉ በመጠየቅ ለአዘርባጃን ህዝብ ያላቸውን አጋርነት አሳይተዋል።

እ.ኤ.አ. በየካቲት 1994 በተካሄደው የሚሊ መጅሊስ (ፓርላማ) ልዩ ስብሰባ ላይ ጥር 12 1982 ዓ.ም በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ እንደ ወታደራዊ ጥቃት እና ወንጀል ተባለ። በመጋቢት ወር 1994 ዓም ደግሞ ባኩ ውስጥ በተፈጸሙ አሳዛኝ ኹነቶች ላይ የውሳኔ ኃሳብ ተላለፈ። ጥር 12ም ብሄራዊ የሃዘን ቀን ተብሎ ታወጀ።

ይህ ጥር 20 የተከሰተው አሳዛኝ ክስተት በአዘርባጃን ብሄራዊ ማንነት ምስረታ ላይ ወሳኝ ተፅእኖ ነበረው። የአዘርባጃን ነፃነት እንዲመለስ ትልቅ ምዕራፍ ሆነ። በሶቭዬት አገዛዝ ለ33 ዓመታት ወታደራዊ፣ ፖለቲካዊና የስነልቦና ጭቆና ሲደርስበት የኖረው የአዛርባጃን  ህዝብ ለታሪካዊ የትግል ባህሉ ቁርጠኛ መሆኑን አስመስክሯል። በዚያች አሳዛኝ ዕለት ለፍትህ ዘብ በመቆም ህይወታቸውን ለሰጡ የእናት ሀገር ልጆች በህዝባችን የጀግንነት ታሪክ ላይ ድንቅ ገፅ  ጽፈዋል። በታሪካችን አሳዛኝ በሆነው ነገር ግን እንደ ብሄራዊ ኩራት በሚቆጠረው ጥር 12 1982 ዓ.ም የአዘርባጃን ሕዝብ ነፃ፣ ሉዓላዊ እና ገለልተኛ ሆኖ መኖር እንደሚገባው ለዓለም አስታውቋል።

የጥር 12 ኹነቶች ሁሉም ዓለም አቀፍ ህጋዊ ሰነዶች በከፍተኛ ሁኔታ የተጣሱባቸው በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተፈጸሙት እጅግ አሰቃቂ ወንጀሎች መካከል የሚመደቡና ከተከሰቱ ደግሞ  33 ዓመታት ያለፉ ቢሆንም ዓለም አቀፍ ህጋዊ ምርመራ አልተደረገባቸውም። በዓለም አቀፍ ህግጋት መሠረት የጥር 12ቱ አሳዛኝ ክስተት በሰብአዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል ተብሎ መሠየም አለበት። እልቂቱን የወጠኑትም ሆኑ የፈጸሙት አጥፊዎች መቀጣት አለባቸው።

ዛሬ ለአዘርባጃን ነፃነት፣ እንዲሁም ለሀገራችን ሉዓላዊነትና ግዛታዊ አንድነት ህይወታቸውን የሰጡ የጀግኖች ሰማዕታቶች ነፍሶች እፎይታ ያገኛሉ። በአሸናፊው ጠቅላይ ጦር አዛዥ ግምባር ቀደምትነትና እና በሙሉው የአዛርባጃን ጦር ሰራዊት አማካኝነት ለ30 ዓመታት በወረራ የቆዩት ግዛቶቻችን ነጻ ወጥተዋል፣ የአዛርባጃን የግዛት አንድነትም ተመልሷል። ወደፊትም በአዛርባጃን ነጻነት፣ ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት ላይ የሚቃጣ ትንኮሳ በቂ ምላሽ ይሰጠዋል።

በድጋሚ ለሀገራችን የግዛት አንድነት፣ ለህዝባችን አርነት እና ለሀገራችን ነፃነት መስዋዕትነት የከፈሉትን ወገኖቻችንን በጥልቅ ሃዘን ውስጥ በመሆን ውድ ትዝታዎቻቸውን በክብር እንዘክራለን።

___________________

የአዘጋጁ መልዕክት፡ በዚህ ፅሁፍ የተካተቱት ኃሳቦች የፀኃፊውን እንጂ የአዲስ ዘይቤን አቋም አያንፀባርቁም

አስተያየት