በጅማ ከተማ ከሀሰን ጋራዥ አልፎ ወደ ጅማ መናሀሪያ በሚወስደው መንገድ አካባቢ በአንድ የግለሰብ ቤት ላይ ከፍተኛ የሆነ የእሳት አደጋ ደረሰ፡፡
እዛው መኖሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ መኮንን የእንጨት ስራዎች በሚል መጠሪያ በከተማው ታዋቂ የሆነ የቤት እቃዎች የሚሰራው መኮንን ታከለ እሳቱን ያስተዋለው ሌሊት 11 ሰዓት ገደማ መሆኑን ለአዲስ ዘይቤ ተናግሯል፡፡
«ሌሊት ስነቃ ቤቱ በጭስ ታፍኖ አየሁ ልጆቼን እና ባለቤቴን ይዤ በነጠላጫማ ከመውጣት ውጭ ምንም ንብረት ማትረፍ አልቻልኩም፡፡አሁን በዚህ ፍጥነት የወደመብኝን ንብረት በእርግጠኝነት ማስላት ባልችልም በግምት ግን ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ ነው ይሆናለ፡፡ምክንያቱም ስቶር የነበሩ የተሰሩ እቃዎች እና ለመጫን የታሸጉ እቃዎች ነበሩ፡፡ የከተማው እሳት እና ድንገተኛ አደጋም ሲደርስ ወደ ሌላ ቦታ እሳቱ እንዳየይዛመት ከማድረግ በስተቀር ምንም ንብረት ሊተርፍልኝ አልቻለም፡፡» በማለት የተፈጠረውን ለአዲስ ዘይቤ አስረድቷል፡፡
የከተማው አሳት አደጋ መከላከያ አስተባባሪ የሆነው አቶ መሃመድ ኑር አደም በበኩሉ “የተከሰተውን እሳት አደጋ ለማጥፋትና ወደ ሌለ ቦታ እንዳይዛመት አየር መንገድ ካሉ የእሳት አደጋ መከላከያ ሰራተኞች ጋር በመሆን ትልቅ ሥራ ተሰረቷል፡፡ ሶስት ሰዓት የወሰደ የእሳት አደጋ መከላል ሥራው 12 ቦቶ ውሃ ፍጅቷል ፡፡ በብዛት እንጨት ውጤቶች ማምረቻ ውስጥ የነበሩ ጣውለዎችና ሰጋቱራዎች የእሳት አደጋው እንዲባባስ አድጓል፡፡ የመከላለክ ሥራው በአግባቡ ባይሰራ ኖሮ አከባቢው የተያያዙ ገራዦችና ሆቴሎች በመኖረቸው ከተማውን ማውደም ይችል ነበር፡፡ የወደመው ንብረትም ገና በበለሙያ እስኪገመት ምንያክል እንደሆነ አየታወቅም” ሲል ለአዲስ ዘይቤ ተናግሯል፡፡
መንስዔው እስካሁን ያልታወቀ ይህ የእሳት አደጋ ከፍተኛ የሆነ የንብረት ውድመት እንደተከሰተ አዲስ ዘይቤ በቦታው ተገኝታ ታዝባለች፡፡
በስሩ 21 ሰራተኞችን ቀጥሮ ሲያሰራ የነበረው መኮንን አሁን የአካባቢው ህብረተሰብ ያለውን እያዋጣለት እንደሚገኝም ለማስተዋል ችለናል፡፡