ማስታወቂያ

በሱማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ በዳዋ ዞን ብቻ ከ63 ሺህ በላይ እንስሳቶች መሞታቸዉ ተነገረ

Avatar: Henok Terecha
ሄኖክ ተሬቻኅዳር 16 ፣ 2014
City: Addis Ababaዜና
በሱማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ በዳዋ ዞን ብቻ ከ63 ሺህ በላይ እንስሳቶች መሞታቸዉ ተነገረ

በሶማሌ ክልል ዳዋ ዞን በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሞቱ እንስሳት ቁጥር “ከ63 ሺ ማለፉን የዞኑ የእንስሳት ሀብት ሀላፊ ዲሞ ማሞ" ለአዲስ ዘይቤ አስታወቁ።

በድርቁ ምክንያት እስካሁን 6896 ግመሎች፣ 6452 ከብቶች እና 50,778 ፍየሎች መሞታቸውን የገለጹት ሀላፊው በአሁኑ ሰአት በድርቁ በርካታ እንስሣት በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ከድርቁ በተጨማሪ በ 2012 ዓ.ም. በክልሉ የገባው የግመል በሽታ እስካሁን ድረስ በግመሎች ላይ ጉዳት እያስክተለ መሆኑን፣ ፍየሎችን ኤልሲፍ ኮስሞስ እና ሌሎች በሽታዎችም እያጠቋቸው እንደሆነና በወቅቱ የሚጠበቀ የበልግ ዝናብ በሚፈለገው መጠን አለመዝነቡ ሁኔታውን እንዳባባሰው ሀላፊው ይገልጻሉ።

በክልሉ የተከሰተው ድርቅ ከእንስሳት ሞት ባሻገር በሰዎች ህይወት ላይ ጫና እየፈጠረ መሆኑንም ያመላከቱት ሀላፊው በድርቁ ምክንያት በዞኑ የሚገኙ በርካታ ነዋሪዎች ለመጠጥ ውሃ እጥረት እንዳጋጠማችውና ከዚህ በተጨማሪም በገበያ ላይ የወተት እና የስጋ ዋጋ በበሽታው ምክንያት በመቀነሱ ማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ መሆኑን አንስተዋል።

የክልሉ በመንግስት ወደ 18,400 የሚሆን ቤል ሳር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ወደ 200,000 እንስሣቶችን ህክምና እንዲያገኙ ከዚህም በተጨማሪ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለዩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የእስንሣት ምግብ አቅርቦት እና የቤት ለቤት ክትባትም እያደረጉ ነው ብለዋል።

ዞኑ በክልሉ ከሚገኘው የእንስሣት ሀብት ውስጥ 80 በመቶ የሚሆነው የያዘ መሆኑን ያነሱት ሀላፊው አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል አርብቶ አደር በሆነበት ዞን የድርቁ ሁኔታ በዚሀ የሚቀጥል ከሆነ በእንስሣትና በሰዎች ላይ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ያሰጋል ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

“ይሄ እንዳለ ሆኖ በዚሀ ድርቅ ምክንያት ከኬኒያ ሶስት ዞኖች ድርቁን ለማምለጥ ወደ ክልሉ በሚገቡበት ወቅት በሽታዎችን ይዝው በመምጣት በእንስሣት ጤና ላይ  ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ ይገኛል”  ብለዋል።

በኦድት ወረዳ ላይ የነበረውን ነዋሪ መጠነኛ ዝናብ ወዳለባቸው አጎራባች ቦታዎች እንዲሰፈሩ እየተሰራ መሆኑንና ጉጂ በተጨማሪም ከኬኒያ የገቡትን አርብቶ አደሮች ጋር ወደ ቦረና ዞን በቦርቦር ወርዳ እየገቡ እንደሚገኙ ሀላፊው ገልጸውልናል።

በተመሳሳይ የቦረና ዞን ካሉት ሰባት ሚሊዮን የእንስሳት ሀብት መካከል 50ሺ በድርቅ መሞታቸውን እና 70 ሺህ የሚጠጉት ደግሞ በሰው ድጋፍ የሚንቀሳቀሱና ህይወታቸው አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ መሆናቸውን በመጥቀስ በዚህም ምክንያት የእንስሳት ሞት በየቀኑ እየጨመረ እንደሚሄድ የቦረና ዞን አስተዳደር መግለፁ ይታወሳል።

Author: undefined undefined
ጦማሪሄኖክ ተሬቻ

Henok is a reporter at Addis Zeybe. He is passionate about storytelling and content creation.