ታህሣሥ 20 ፣ 2013

በጅግጅጋ ለኮቪድ የሚደረገው ጥንቃቄ በቂ እንዳልሆነ ተነገረ

City: Jigjiga

በየቀኑ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ወደ ሕክምና ማዕከል ከሚገቡት 10 ታማሚዎች ውስጥ በአማካይ አራቱ ሰዎች የሚሆኑት ጽኑ ሕክምና ክፍል እንደሚገቡ የሶማሌ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ የሆነው ዶክተር ዩሱፍ ይናገራል፡፡

Avatar: Mohammed Hassen
Mohammed Hassen

journalism and communications graduate and an expert in communications affairs in the region and mobile journalist at Addis Zeybe.

በጅግጅጋ ለኮቪድ የሚደረገው ጥንቃቄ በቂ እንዳልሆነ ተነገረ

በየቀኑ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ወደ ሕክምና ማዕከል ከሚገቡት 10 ታማሚዎች ውስጥ በአማካይ አራቱ ሰዎች የሚሆኑት ጽኑ ሕክምና ክፍል እንደሚገቡ የሶማሌ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ የሆነው ዶክተር ዩሱፍ ይናገራል፡፡

ይህ የሆነበት ምክንያት ህብረተሰቡ ከጤና ባለሙያዎች የሚሰጡ ምክሮችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያለማድረጉ እንደሆነና የሚመለከታቸው አካላትም የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት መስጠት እየቀነሱ መምጣታቸው መሆኑ እንዲሁም የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል የመጠቀም ባህል በክልሉ ዋና ከተማ ጅግጅጋም ይሁን በሌሎች ከተሞች እየቀነሰ መምጣቱን  መሆኑን ሐላፊው አክሏል።

በክልሉ እሰካሁን ድረስ 1664 ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ስሆን 35 ህይወታቸው አጥተዋል፡፡
"ዛሬ በእግር ቆሜ ከልጆቼ ጋር የምገናኝ አልመሰለኝም ነበር፡፡ በሞትና በመኖር መሀል ነበርኩ፡፡ መጀመሪያ ወረርሽኙ ወደ ሀገር ዉሰጥ ገብቷል ሲባል ስቀልድ ነበር፡፡ አላህ ያመጣው እርግማን ነዉ በማለት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ለራሴ ተዉና ሌሎችም ሲለብሱ በሽታዉ መጀመሪያ እራሳቸዉን የሚይዛቸዉ ይመሰለኝ ነበር፡፡ አንድ ቀን ግን እንደ ድንገት አሞኝ ለመመርመር ሆሰፒታል ስሄድ በበሽታው እንደተያዝኩ ተነገረኝ፡፡ "ይላሉ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተጠቅተው የነበሩት አቶ መሀመድ ሙሳ ማቆያ የነበረው ቆይታቸዉን ሲያስታውሱ፡፡

በተጨማሪም "በሶማሊ ክልል ጅግጅጋ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ማለትም በሰርግ፣ በሀዘን፣ በሆተሎች፣ በመንግሰት መሰሪያ ቤቶች አከባቢ በሚገኙበት ጊዜ እንዲሁም በህዝብ ትራንስፖርት መገልገያ ሰዎች በሚሳፈሩበት ወቅት የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም፡ ርቀታቸውን ጠብቀው የመቀመጥ ልምድ እየቀነሰ መምጣቱን ማስተዋል ይቻላል፡፡" ብለዋል፡፡

«የሚጠነቀቀውን ሰው እንደ ፈሪ የማየት ዝንባሌ አለ፡፡ጉንፋን ነው፤ ምን ታካብዳለህ? ጊዜህ ከደረሰ ትሞታለህ የሚለው ሰው ብዙ ነው» ይላሉ ሌላኛው ከኮቪድ ሕመም ከ20 ቀናት በኋላ ያገገሙት አስተያየት ሰጪ አቶ ኢሰሃቅ ዩሱፍ በበኩላቸ
«የሶማሌ ህዝብ በሽታ የአላህ ቁጣ ነው ብሎ ስለሚያስብ በተደጋጋሚ ግንዛቤ ማስጨበጫ ብንሰጥም ለውጥ ማግኘት አልተቻለም፡፡ አሁን ላይ በበሽታው የሚያዘው ሰው ቁጥር እያደገ በመምጣቱ የለይቶ ማቆያዎች እና የህክምና ቁሳቁስ እጥረት እየገጠመን ነው፡፡ እርዳታ ለማግኘት ለፌደራል መንግሥት በተደጋጋሚ ጥያቄ ብንጠይቅም » ይላል የደጋህቡር ከተማ ጤና ቢሮ ሀላፊ ሁሴን አብዱልቃድር።

አስተያየት