ታህሣሥ 20 ፣ 2013

“ሃይሌሥላሴ አነሳሳቸው፣ አወዳደቃቸው” የተሰኘው መጽሐፍ ለትርጉም በቃ

City: Addis Ababaየአኗኗር ዘይቤ

በሃጋይ ኤርሊክ ተጽፎ የተዘጋጀው “ኃይሌሥላሴ አነሳሳቸው፣ አወዳደቃቸው” የተሰኘው መጽሃፍ በሔዋን ስምዖን ተተርጉሞ ለንባብ ሊበቃ ነው።

Avatar: Selam Fisseha
ሰላም ፍሰሃ

Selam Fisseha is a graduate of Addis Ababa University Law School and a Mobile Journalist from Addis Ababa at Addis Zeybe.

“ሃይሌሥላሴ አነሳሳቸው፣ አወዳደቃቸው” የተሰኘው መጽሐፍ ለትርጉም በቃ

በሃጋይ ኤርሊክ ተጽፎ የተዘጋጀው “ኃይሌሥላሴ አነሳሳቸው፣ አወዳደቃቸው” የተሰኘው መጽሃፍ በሔዋን ስምዖን ተተርጉሞ ለንባብ ሊበቃ ነው። መጽሐፉ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት የነበሩትን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ህይወት ከአንድ ሃገር መሪ ህይወት በኩል ሳይሆን በተቃራኒው ከአንድ የቤተሰብ ሰው ህይወት ታሪክ አንጻር እንደተጻፈ ተርጓሚዋ ለአዲስ ዘይቤ ተናግራለች።

መፅሐፉ የተፃፈው በእስራኤላዊው የታሪክ ባለሙያ  ሃጋይ ኤርሊክ ሲሆን ፕሮፌሰሩ በመካከለኛው ምስራቅ እና የኢትዮጵያ ታሪክ ተጠቃሽ ምሁር ሲሆኑ በራስ አሉላ አባነጋ ታሪክ ዙሪያ ለሦስተኛ ዲግሪያቸው ማሟያ ያደረጉት ምርምር ተጠቃሽ ስራቸው ነው፡፡ 

በጀርመን ሀገር ሐምቡርግ ከተማ፣ በኢዮብ ሎዶልፍ ማዕከል የኢትዮጵያ ታሪክ ተማሪ የሆነችው ሔዋን ስምዖን ይህ ትርጉም ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ የመለሰችው የመጀመሪያ ስራዋ ነው። “ከደርግ መንግስት በፊትም ሆነ በኋላ ያሉት አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ታሪክ መፅሐፍት በፖለቲካው ስርአት ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ ይህ መጽሐፍ ግን የንጉሱን ግላዊ ህይወት የሚዳስስ ነው” ስትል ለአዲስ ዘይቤ ተናግራለች።

መጽሐፉ 316 ገጾች ሲኖሩት ሙሉ ለሙሉ ተርጉሞ ለመጨረስ ስድስት ወራት እንደፈጀባት ገልጻ በኢክሊፕስ አሳታሚ ድርጅት ታትሞ በመጪው መጋቢት ወር ለንባብ እንደሚበቃ ተናግራለች።

አስተያየት