You can paste your entire post in here, and yes it can get really really long.
ጨቋኝ ከተጨቋኝ- አይፈቃቀሩም- ሲሉ እንዳላፋቱበአፍላ ዕድሜያችን- የመዋደድ እሳት- ውሃ እንዳልከተቱጥላቻ እንደወተት- በቀል እንደአጃ- እኛኑ እንዳልጋቱውሃና ዘይት ነን- ከቶ የማንዋሃድ- ወሬ እንዳላተቱስንለያይ ጊዜ- ሰማዩ እንደሚደምቅ- እንዳልወተወቱበነሱ ቃላት ጦስ- እንዳልተራረዱ- ድሆች እንዳልሞቱፖለቲካ እንጂ- አንድ ነን እያሉ- አየሽ ሲገዘቱ!ፈጣሪ የሰጠንን፤ ፍቅር አጠራጥረውመዓት የግፍ ታሪክ፤ ጠቃቅሰው አጣቅሰውመፃህፍት አትመው፤ ሃውልት አስቀርፀውጥላቻ አብኩተው፤ ቂም በቀልን ጋግረውስንክሳሩን ሁሉ፤ በበደል ለውሰውአንድ ነው ደማችን- ሲሉ የነበሩትን- ረግመው እንደጠላትአፍርሰው አሳደው- በወዮልህ ዛቻ- በያሪኮ ጩኸትፍቅር ሰባኪውን- ባደባባይ ወግረው- አስደፍተው አንገትሽማግሌ አሳቀው- እውነት ገባኝ ባለ- የጎረምሳ ት'ቢትያገር ፍቅር ባዩን- በጥብጠው ጥላቻ- አጠጥተው ሀሞትበሰዋሰው ቅርጫ- ባለጎሳ ፋፍቶ- ባለራዕይ ሲሞትመቃብሩን ረግጠው- አንለያየምን- እዪው ሲዘምሩት::አየሽ ግፋቸውን!እኛን አለያይተው፤ ፍቅር እንዳልቀሙዛሬ ደሞ እነሱ፤ ስለፍቅር ቆሙ::የሰጡንን ይዘን- ለጋ ልቦች ላይ- ጥላቻ ስንዘራሃገር እሾህ ሆና- እኔንም አንቺንም- ወጋግታ አባራየፍቅር ብርሃን- ልባችን ተቀብሮ- የመዋደድ ጮራየይስሙላ ጎጆ- ባ'ጥንት ቀልሰን- ከጎሳ ሰው ጋራማፈንገጥ እንዳይሆን- ከዘውግ ቃልኪዳን- ከደቦ አደራናፈቅሽኝ መባባል- መጠያየቅ እንኳን- ይሉኝታ ስንፈራሽማግሌ ያልናቸው- ያለያዩን ሰዎች- በአዲስ ፉከራአንድ ነን አሉ እኮ- ምንም የማይለየን- ደማችን የጋራ::ይሄ ነው ቀልዳቸው፤ ስላቃቸው ረቂቅበቃ አትዙር አሁን፤ ብሎ የሚያሸማቅቅ::ጨቋኝ ከተጨቋኝ- አይፈቃቀሩም- ሲሉ እንዳላፋቱበአፍላ ዕድሜያችን- የመዋደድ እሳት- ውሃ እንዳልከተቱጥላቻ እንደወተት- በቀል እንደአጃ- እኛኑ እንዳልጋቱውሃና ዘይት ነን- ከቶ የማንዋሃድ- ወሬ እንዳላተቱስንለያይ ጊዜ- ሰማዩ እንደሚደምቅ- እንዳልወተወቱበነሱ ቃላት ጦስ- እየተረራረዱ- ድሆች እየሞቱፖለቲካ እንጂ- አንድ ነን እያሉ- ማሉ ተገዘቱ!የተሳደደውን- የተገደለውን- ክቡር ሰው ላይተካፍቅርን አጥፍቶ- የጨላለመውን- ልብ ላያፈካያንን ፀጋችንን- ቀኑን ላይመልሰው- የኔና አንቺን እንኳእውነትንም ቢሆን- ደርሶ እንደዘበት- ሲሉት ያማል ለካ::ሰኔ: 2010 ዓ.ም