በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ የዋጋ ጭማው መባባሱን ያመለከተውን የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጀንሲን መረጃ መነሻ በማድረግ በጎንደር ከተማ ያለውን የሸቀጦች ዋጋና የማኅበረሰቡን አቀባበል በጥቂቱ እንዳስሳለን።
ሀይማኖታዊ በአላት ሲከበሩ ከሃይማኖታዊ ይዘት ባሻገር ምግቦች፣ አልባሳት እና የተለያዩ መዋቢያ ቁሳቁሶች ለበአሉ ድምቀት ሲሆኑ ይስተዋላል። በዘንድሮው የኢድ-አል አድሀ አረፋ በአል የገበያ ሁኔታ ምን ይመስላል? አዲስ ዘይቤ ቃኝታለች!
በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ በተለይም የክረምትን መግባት ተከትሎ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በቆሎ ሻጮችን እና ተገበያዮችን መመልከት የተለመደ ነው። በበቆሎ ገበያው ላይ የዋጋ ጭማሪ መኖሩ ግን ይሄን ኡደት ያስተጓጎለው ይመስላል።
በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ አካባቢዎች የታየው የጸጥታ ችግር የምግብ እና ሌሎች ሸቀጦች ዋጋ እንዲንር ምክንያት ሆኗል፤ ካሳለፍነው ዓመት መጋቢት ወር ጀምሮ በሐገራችን በስፋት መታየት የጀመረው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሸቀጦችን ዋጋ አንሯል፡፡