ኅዳር 10 ፣ 2011

በሙሥና የተጠረጠሩ የ310 ባለሥልጣናትና ቤተሰቦታቸው ገንዘብና ንብረት ታገደ

ወቅታዊ ጉዳዮች

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ፣ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባስተላለፈው አስቸኳይ የዕግድ ትዕዛዝ መሠረት፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ…

በሙሥና የተጠረጠሩ የ310 ባለሥልጣናትና ቤተሰቦታቸው ገንዘብና ንብረት ታገደ
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ፣ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ባስተላለፈው አስቸኳይ የዕግድ ትዕዛዝ መሠረት፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ በሀገር ውስጥ በሚገኙ በአሥራ ስድስቱም (16) የግል ባንኮች ውስጥ የሚገኙ የ310 በሙሥና እና በሰብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ ኃላፊዎች እና ቤተሰቦቻቸው በሚሊየኖች የሚቆጠር ገንዘብና ተቀማጭና ተንቀሳቃሽ ንብረቶች (የከበሩ ማዕድናትን ጨምሮ) እንዳይንቀሳቀሱ ማገዱን ምንጮች ለዘጋቢያችን አረጋግጠዋል። በዕግድ ሒደቱ ላይ የድርጅቶቻቸውም የባንክ ሂሳብ ደብተሮችም ተካተዋል።በዚህ የባንክ የተቀማጭ ገንዘብና ተንቀሳቃሽ ንብረት የዕግድ ትዕዛዝ ውስጥ፣ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ኃላፊ የነበሩት የአቶ ጌታቸው አሰፋ እና ቤተሰቦቻቸው በተለያዩ ባንኮች የሚገኙ ሰባት (7) የባንክ ደብተሮች፣ የምክትላቸው የአቶ ያሬድ ዘርይሁን እና ቤተሰቦቻቸው አሥራ ስድስት (16) የባንክ ደብተሮች፣ የሀገር ውስጥ ደህንነት ም/ል ዋና ዳይሬክተር የነበሩት የአቶ ደርበው ደመላሽ እና ቤተሰቦቻቸው ሰባት (7) የባንክ ደብተሮች፣ የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ሥራ አስኪያጅ የነበሩት የሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው እና የቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ፣ የ310 ተጠርጣሪዎችና በቤተሰቦቻቸው ሥም የሚገኙ ገንዘብና ተቀማጭ ንብረቶች በአስቸኳይ ታግዶ መንግሥት እንዲያውቀው ተደርጓል ብለዋል።የገንዘብና ተንቀሳቃሽ ንብረት የዕግድ ትዕዛዙ ለባንኮቹ በምስጢር የተተላለፈው ከሰኞ ህዳር 3 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ፣ ማክሰኞ እና ረቡዕ (ለህትመት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ) በሦስት እርከን ተከፍሎ ሲሆን፣ ገና ይቀጥላል ተብሏል።የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ፣ በደብዳቤ ቁጥር 3/1717/11 በቀን 6/03/2011 ‹‹… ከላይ ሥማቸው የተጠቀሱ 310 ግለሰቦች የባንካችሁ ደንበኛ  መሆን አለመሆናችሁን፣ ከባንካችሁ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ከመቼ ጀምሮ እንደሆነ፣ በግልም ሆነ በጋራ ወይም በውክልና እና በዚህ ደብዳቤ በስም ካልተጠቀሱ ሰዎች ጋር በከፈቱት የቁጠባና ተንቀሳቃሽ ሂሳብ ውስጥ በአሁኑ ሰዓት ያለውን የሀገር ውስጥ ገንዘብ፣ የከበሩ ማዕድናት እና የውጭ አገር ገንዘብ እና በባንኩ ያላቸውን የሼር መጠን መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እስከምናመጣ በአዋጅ ቁጥር 882/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 4 መሠረት ታግዶ እንዲቆይ፣ ስለመታገዱም በተቻለ ፍጥነት እንድታሳውቁን በአዋጅ ቁጥር 433/07 አንቀጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 2 (ለ) እና አንቀጽ 28 ንዑስ አንቀጽ 3 እና 4 መሠረት የተለመደ የሥራ ትብብራችሁን እንጠይቃለን።›› ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ- ሲል ያትታል።የተጠርጣሪዎቹ ባለሥልጣናትና ቤተሰቦቻቸው በባንኮች ያንቀሳቅሱት የነበረው ገንዘብን ማገድ ብቻ ሳይሆን፣ በቅርብ ጊዜ እና በቆይታ በባንክ ደብተራቸው ያከናወኑት ገንዘብ የማስገባትና የማስወጣት እንቅስቃሴ፤ ከአንድ ሰው የባንክ ደብተር ወደ ሌላ ሰው የባንክ ደብተር የተከናወነ የገንዘብ ዝውውርና ሽግሽግ ሁሉ በአስቸኳይ ለፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ተልኳል ብለዋል- ለዘጋቢያችን።መንግሥት፣ የተጠርጣሪ ባለሥልጣናትንና ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ከማገድ ባሻገር፣ በልዩ ልዩ ባንኮችና ትልልቅ ድርጅቶች ውስጥ ያላቸውን የባለድርሻነት ሠርተፍኬት እየመረመረ ነው ያሉን ምንጮች፤ በሥማቸውና በወዳጅ ዘመድ ሥም የሚገኙ ትልልቅ ህንፃዎች፣ ቪላ ቤቶች፣ ውድ-ውድ መኪኖች እና ሌሎች ንብረቶችንም እያጣራ ነው በማለት ለዘጋቢያችን ገልጸዋል።በተለይ በወጋገን ባንክ በኩል የነበረውንና ያለውን የብድር አሰጣጥ የአሰራር ሂደት እየመረመረ ነው ያሉን ምንጮች፣ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የባንኩን ሊቀመንበር ማነጋገሩን አሳውቀውናል።ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሥም የተጠቀሱና ያልተጠቀሱ ባለሥልጣናት፣ ኃላፊዎች እና ቤተሰቦቻቸው፣ አቀባባይ ደላሎች፣ የጥቅም ትሥሥር ያላቸው ባለሃብቶች፣ ተዛማጅ-ነጋዴዎች፣ በሕገወጥ መንገድ ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ፣ መካከለኛው ምሥራቅና ሩቅ ምሥራቅ ሀገራት የሸሸውን የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሪ ገንዘብ ለማስመለስ መንግሥት፣ ጠቅላይ ምኒስትር ጽ/ቤት፣ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ከሀገራቱና ገንዘብ ሸስቶባቸዋል ከተባሉት ባንኮች ጋር ንግግር እያደረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። የባንክ ሂሳባቸው የታገደባቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች የሚከተሉት ናቸው
  1. አቶ ጌታቸው አሰፋ አበራ
  2. ልዕልቲ ጌታቸው አሰፋ (ልጅ)
  3. ዶ/ር ሀሽም ቶፊቅ መሐመድ
  4. አቶ ያሬድ ዘሪሁን ሽጉጤ
  5. ወይንሸት ዘሪሁን ሽጉጤ (እህት)
  6. ቤተልሄም ዘሪሁን ሽጉጤ (እህት)
  7. ትዕግስት ዘሪሁን ሽጉጤ (እህት)
  8. ዳንኤል ዘሪሁን ሽጉጤ (ወንድም?)
  9. አዳነች ተሰማ ቶላ (ሚስት)
  10. ሃዊ ተሰማ ቶላ (የሚስት እህት?)
  11. ጌታሁን ተሰማ ቶላ (የሚስት ወንድም)
  12. ንጉሱ ተሰማ ቶላ (የሚስት ወንድም)
  13. ጥላሁን ተሰማ ቶላ (የሚስት ወንድም)
  14. ውብሸት ተሰማ ቶላ (የሚስት ወንድም)
  15. ቅድስት ያሬድ ዘሪሁን (ልጅ)
  16. ካትሪን ያሬድ ዘሪሁን (ልጅ)
  17. በጸሎት ያሬድ ዘሪሁን (ልጅ)
  18. ሣራ ያሬድ ዘሪሁን (ልጅ)
  19. አቶ ጎሃ አጽብሃ ግደይ
  20. ዮርዳኖስ ገብረማርያም ሀጎስ (ሚስት)
  21. ኢርሴ ጎሃ አጽብሃ (ልጅ)
  22. ቅድስት ጎሃ አጽብሃ (ልጅ)
  23. አቶ አማኑኤል ኪሮስ መድህን
  24. ሀና አማኑኤል ኪሮስ (ልጅ)
  25. ብሩክ አማኑኤል ኪሮስ (ልጅ)
  26. ፋና ግርማይ ገብረእግዜአብሄር (ሚስት)
  27. አቶ ደርበው ደመላሽ ሽገጉ
  28. ወይንሸት ፋቱይ ተክሌ (ሚስት)
  29. ሰላም ደርበው ደመላሽ (ልጅ)
  30. ረድኤት ደርበው ደመላሽ (ልጅ)
  31. አላዛር ደርበው ደመላሽ (ልጅ)
  32. ቤልሔል ደርበው ደመላሽ (ልጅ)
  33. አሚን ደርበው ደመላሽ (ልጅ)
  34. አቶ ተስፋዬ ገብረፃድቅ
  35. ህያብ (ሰ) ተስፋዬ ገብረፃድቅ (ልጅ)
  36. ሙሉ ፍሰሃ ካህሳይ (ሚስት)
  37. ሄዋን ተስፋዬ ገብረፃድቅ (ልጅ)
  38. አቶ ቢንያም ማሙሸት መኮንን
  39. ሙሉ ሀጎስ ተክሌ
  40. ሩሃማ ቢንያም ማሙሸት (ልጅ)
  41. ቲዮብስታ ቢንያም ማሙሸት (ልጅ)
  42. አቶ ተሾመ ኃይሌ ፈንታሁን
  43. ኤልሳ ወንድሙ ተድላ (ሚስት)
  44. አቶ አሰፋ በላይ
  45. አቶ አዲሱ በዳሳ ኑመራ
  46. ሃይማኖት አዲሱ በዳሳ (ልጅ?)
  47. ሩት አዲሱ በዳሳ (ልጅ?)
  48. ፍራኦል ስመኝ አበራ ለገሠ (ሚስት?)
  49. አቶ ሸዊት በላይ ዓለማየሁ
  50. ሃናን ኢብራኢም ሰይድ
  51. ኮረኔል አሰፋ ዮሐንስ ሀደራ
  52. ሻምበል ሠመረ ኃይሌ ሀጎስ
  53. ሞሚና ታደሰ ዓለሙ
  54. ሻምበል ይኩኖአምላክ ተስፋዬ አዘዞም
  55. ቅዱስ ይኩኖአምላክ ተስፋዬ(ልጅ?)
  56. ትግስት አሰፋ ደሴ
  57. ወ/ሮ ሲሳይ ገብረመስቀል ሀረነት
  58. ሻለቃ ደሴ ዘለቀ ብርሃን
  59. ዳግማዊ ደሴ ዘለቀ (ልጅ?)
  60. ቅድስት ደሴ ዘለቀ (ልጅ?)
  61. ቃልኪዳን ደሴ ዘለቀ (ልጅ?)
  62. ሽከፍ ፈንታው ዘለቀ
  63. ሻለቃ ሰለሞን በርሄ
  64. ሻለቃ ይርጋ አብረሃ
  65. ሀይቅ ይርጋ አብረሃ (ልጅ?)
  66. አስቴር ጋይሞ ኪዳኔ
  67. ኮሮኔል ግርማይ ታረቀኝ
  68. ሻለቃ ካሳ ሮባ
  69. ጄኔራል ገብረስላሴ ገብረጊዮርጊስ ገብረህይወት
  70. ሰላማዊት ረዳ ተስፋ
  71. ናኦሚ ገብረስላሴ ገብረጊዮርጊስ (ልጅ?)
  72. ባሮክ (?) ገብረስላሴ ገብረጊዮርጊስ (ልጅ?)
  73. ሄኖክ ገብረስላሴ ገብረጊዮርጊስ (ልጅ?)
  74. ሻምበል ሰለሞን አብረሃ ዓለሙ
  75. ትርሃስ በርሄ ፍሌ
  76. ዳህና ሰለሞን አብረሃ (ልጅ?)
  77. ሀሩሪ ሰለሞን አብረሃ (ልጅ?)
  78. ኮሮኔል ሙሉ ወልደገብርኤል ገብረእግዚሃብዘሄር
  79. ሻምበል ካህሳይ ክሽን ዓለማየሁ
  80. መብርሂት ኃይለ ሀጎስ
  81. ኮሮኔል ተሰማ ግደይ ወልዱ
  82. ብርጋዴር ጄኔራል ጠና ቁርንዲ ኢዴታ
  83. ናኦል ጠና ቁርንዲ (ልጅ?)
  84. ፍራኦል ጠና ቁርንዲ (ልጅ?)
  85. ሮቤል ጠና ቁርንዲ (ልጅ?)
  86. በንጉሴ ጠና ቁርንዲ (ልጅ?)
  87. የሺ ገመቹ ግችሌ
  88. ብርጋዴር ጄኔራል ብርሃ በየነ
  89. ብርጋዴር ጄኔራል ጥጋቡ ፈትለ መረሣ
  90. ዮሴፍ ጥጋቡ ፈትለ (ልጅ?)
  91. ብርጋዴር ጄኔራል ሀድጉ ገብረጊዮርጊስ ገብረስላሴ
  92. ኤደን ሀድጉ ገብረጊዮርጊስ (ልጅ?)
  93. ናታን ሀድጉ ገብረጊዮርጊስ (ልጅ?)
  94. ቅዱስ ሀድጉ ገብረጊዮርጊስ (ልጅ?)
  95. አጸደ ኃይለእዝጊ ተስፋዬ
  96. ኮሮኔል ሸጋው ሙሉጌታ ተስፋሁን
  97. አሸናፊ ሸጋው ሙሉጌታ (ልጅ?)
  98. ወ/ሮ ደስታ ታከለ ገብረፃዲቅ
  99. ኮሮኔል ዙፋን በርሄ ይህደግላ
  100. ደሊና ተሰማ ግደይ
  101. ሻምበል አስመረት ኪዳኔ አብርሃ
  102. ጌታቸው መስፍን አስገዶም
  103. አማኑኤል ጌታቸው መስፍን (ልጅ?)
  104. ኮሮኔል ዓለሙ ሽመልስ ብርሃን
  105. ወ/ሮ ሻሼ ዳኘው ገብረስላሴ
  106. ሻሼ ኮንስትራክሽን ድርጅት
  107. አቶ ደግነህ ኃይሉ ተስፋዬ
  108. ናርዳ ቢዝነስ ኃላ/ የተ/የግ ማህበር
  109. ደግነህ የግል ንግድ ድርጅት
  110. ናይል ትራንዚት ኃላ/የተ/የግ ማህበር
  111. ወ/ሮ ለምለም ዳኘው ገብረስላሴ
  112. ኡስማን አብዱ (ዋህበረዲ)
  113. ኦላክ ቢዝነስ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
  114. ዮሐንስ መገርሳ
  115. ዜድ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
  116. አቶ ረመዳን ሁሴን
  117. ቸርነት ዳና (ዋይ ቲ ኦ ባለቤት)
  118. ዋይ ቲ ኦ ኃላ/የተ/የግ ማህበር
  119. አክሊሉ ግርማይ (የአናና ትሬዲንግ ባለቤት)
  120. አናና ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ ማህበር
  121. ዓለም ፍቅም ገብረስላሴ
  122. ዓለም ትሬዲንግ ኢንዳስትሬ ኃላ/ የተ/የግ/ማህበር
  123. ሚ.ር ኢታይ ተርነር
  124. አቮሪንጋ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
  125. አቶ አረጋዊ ግርማይ ገብረእግዚአብሔር
  126. ጸጋዬ አረጋዊ ግርማይ (ልጅ?)
  127. ጀማ ፋሚሊ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/ የግ/ማህበር
  128. አቶ ጸጋዬ በርሄ ኃይለጊወርጊስ
  129. ተስፋሁን ሰብስቤ ተሾመ
  130. ጸጋዬ ገብረእግዚሃብሔር
  131. ፍጹም የሺጥላ በቀለ (ጋዜጠኛ)
  132. ብሩክ ገብረመስቀል
  133. ሌ/ኮሮኔል ገብረመድህን ገብረስላሴ ሀድጎ
  134. ሻለቃ ጌታቸው ገብረስላሴ ታፈረ
  135. ሙሉካ ደሳለኝ ስዩም
  136. ሄማዳ ጌታቸው ገብረስላሴ(ልጅ?)
  137. ኤልያም ጌታቸው ገብረስላሴ(ልጅ?)
  138. ሌ/ኮሮኔል ይስሃቅ ኃይለማርያም አድሃኖም
  139. ናሆም ይስሃቅ ኃይለማርያም (ልጅ?)
  140. ኢዛና ይስሃቅ ኃይለማርያም (ልጅ?)
  141. ሚለን ይስሃቅ ኃይለማርያም (ልጅ?)
  142. ሄለን አድማሱ
  143. ሻለቃ ክንደያ ግርማይ ተሰማ
  144. ትራሃስ ካላዩ በላይ
  145. ሄራን አደም ክንደያ ግርማይ (ልጅ?)
  146. ሰሚና ክንደያ ግርማይ (ልጅ?)
  147. ሻለቃ አዳነ አጋርነው
  148. ሻለቃ ጌታቸው አጽብሃ ወልደጊዮርጊስ
  149. አጸደ ግደይ ሀረጎት
  150. ዮሀና ጌታቸው አጽብሃ (ልጅ?)
  151. ጎይቶም ከበደ ዓለሙ
  152. አዜብ ነጋ ዑቡይ
  153. ሠናይት ጎይቶም ከበደ (ልጅ?)
  154. ሀቢና ጎይቶም ከበደ (ልጅ?)
  155. ህያብ ጎይቶም ከበደ (ልጅ?)
  156. አታክልት ዳኘው ገብረሥላሴ
  157. መና ሴኪዩሪቲ ኃላ/የተ/የግ/ ማህበር
  158. ኮሮኔል ግደይ ገብረሚካኤል አንዴታ
  159. ዓለምነው ባሳዩት ፈጠነ
  160. መቅደስ ዓለሙ ሽመልስ
  161. ኤርሚያስ ዓለሙ ሽመልስ
  162. ኢዮሲያስ ዓለሙ ሽመልስ
  163. ኤፍላጦስ (?) ዓለሙ ሽመልስ
  164. ኮሮኔል ኢዱ ጸጋይ ይዳኑ
  165. ገነት ኃይሉ ለማ
  166. ኮሮኔል ያሬድ ኃይሉ ገብረዮሐንስ
  167. ኃይሉ ገብረዮሐንስ ተክላይ
  168. የትምነሽ አስገዶም
  169. ቴዎድሮስ ኃይሉ ሀጎስ
  170. አቶ ኃይሉ ሀጎስ
  171. ኮሮኔል ተከስተ ኃይለማርያም አድሃኖም (?)
  172. ያቆብ ተከስተ ኃይለማርያም (ልጅ?)
  173. አዶናይ ተከስተ ኃይለማርያም (ልጅ?)
  174. ዮርዳኖስ ሙሉጌታ ወርቅነህ
  175. ኮሮኔል ጌትነት ጉደያ ቦዴ (?)
  176. መብራት ገብርኤር ገብረእግዜአብሔር
  177. ኤደን ጌትነት ጉደያ (ልጅ?)
  178. አሀቲ ጌትነት ጉደያ (ልጅ?)
  179. ማርካን ጌትነት ጉደያ (ልጅ?)
  180. ኮሮኔል ሀዜብ ታደለ ኃይሉ
  181. ጄኔራል ዓለምሰገድ አደራ
  182. ሳሚ (?) ዓለምሰገድ አደራ (ልጅ?)
  183. - ዓለምሰገድ አደራ (ልጅ?)
  184. ዓለምሰገድ አደራ ተክሉ
  185. ኮሮኔል መሐመድ … ኢብራሂም
  186. ሃናን ኢብራኢም ሰኢድ (ሚስት)
  187. ፍቅር ወርቁ እንየው (ሚስት)
  188. አቶ አሸናፊ ተስፋሁን ላቀው
  189. አዜብ አሸናፊ ተስፋሁን (ልጅ)
  190. ኢዩኤል አሸናፊ ተስፋሁን (ልጅ)
  191. ሶፋኒያስ ሸዊት በላይ
  192. ሜሮን ሸዊት በላይ (ልጅ)
  193. ህሊና ሸዊት በላይ (ልጅ)

አስተያየት