ጥር 25 ፣ 2011

በወረራ ወቅት የተሰሩ ህፃዎችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ ለእይታ ቀረበ

ወቅታዊ ጉዳዮችኹነቶች

በጣሊያን ወረራ ጊዜ በአዲስ አበባ የተገነቡ ህንፃዎችን የሚያሳይና አሰፋፈራቸውን የሚገልፅ አውደ ርዕይና የምክክር መድረክ መስቀል አደባባይ በሚገኘው የከተማ…

በወረራ ወቅት የተሰሩ ህፃዎችን የሚያሳይ አውደ ርዕይ ለእይታ ቀረበ
በጣሊያን ወረራ ጊዜ በአዲስ አበባ የተገነቡ ህንፃዎችን የሚያሳይና አሰፋፈራቸውን የሚገልፅ አውደ ርዕይና የምክክር መድረክ መስቀል አደባባይ በሚገኘው የከተማ ማዕከል አንጋፋ እና ወጣት የኪነ ህንፃ ባለሞያዎች በተገኙበት ጥር 23፣ 2011 ዓ.ም ለእይታ ቀርቧል።በራስ አርክቴክትና እና በኖርዌይ ሮያል ዩኒቨርሲቲ ኦፍ አርት ትብብር የተዘጋጀው ይህ መርሃ ግብር አምስት ቦታዎችን በመለየት ትኩረት አድርጎ ሰርቷል። አራዳ፣ ብሄራዊ፣ ፖፖላሬ፣ መርካቶ እና ካዛኢንቺስ (በጣሊያንኛ ቋንቋአጠራር)።የፋሽስት ወረራ የህዝብን አሰፋፈር መሰረት ያደረገ እንደሆነ ባለሞያዎች ይናገራሉ። የተመረጡት ስፍራዎችም ይሰጡ በነበረው አገልግሎት እንደሆነ በዝግጅቱ ወቅት ተገልጿል።ናሆም ተክሉ የኪነ ህንፃ ባለሞያና የዚህ ፕሮጀክት አባል ነው። የተረጡትን ስፍራዎች አስመልክቶ ለአዲስ ዘይቤ ሲናገር “ምንም እንኳን በወረራው ጊዜ ለፋሽስቱ የተመረጡ ሌሎች ስፍራዎች በአዲስ አበባ ቢኖሩም በዞን ደረጃ ግን እነዚህ ቦታዎች በጣም ጠቃሚ ነበሩ።” ብሏል።“አራዳ” የአስተዳደሩ ማዕላዊ ስፍራ እና ለጣሊያኖቹ መገበያያ ሲሆን በአንጻሩ “መርካቶ” ደግሞ ለሀገሬው (ለኢትዮጵያውያን) የተሰራ የንግድ ስፍራ ነበር። ጣሊያኖቹ አጠገባቸው እንዳይደርሱ በማሰብ የተሰራ ነው። “ፖፖላሬ” የወታደሮች ካምፕና ለኢንዱስትሪ ስፍራነት ያገለግል ነበር። የለገሀርን መስመር ይዞ የሚገኘው “ብሄራዊ” አካባቢ ደግሞ አስተዳደራዊ ስራዎች የሚሰራበት እንዲሁም “ካዛኢንቺስ” የከፍተኛ ባለስልጣናት ሰፈር እንደነበሩ መረጃዎች ያመለክታሉ።[caption id="attachment_1769" align="alignnone" width="492"] ፎቶ፡- ማኀደር ገብረመድኅን ትዊተር(@bobomaheder )[/caption]ከላይ የተገለፁትን ምክንያቶች መሰረት በማድረግ የተሰራው ይሄ ፕሮጀክት ሀሳቡ የመነጨው በውይይት መሀል እንደነበር ነገር ግን እንደዚህ ተሰርቶ ለህዝብ ይፋ ይሆናል እምነት እንዳልነበራቸው የቡድኑ አባላት ተናግረዋል። ከሰባት በላይ አባላትን የያዘው ይህ ጥናት ዝግጁትን ለማጠናቀቅ አምስት ወር እንደፈጀም ተገልጿል።“በዚህ ስራ ወቅት መረጃዎችን ማሰባሰብ ፈታኝ ነበረ፤ ምርምር ለማድረግ ብቻ ሁለት ወር ፈጅቶብናል። በተጨማሪ አብዛኞቹ መረጃዎቹ በጣሊያንኛ መጻፋቸው ስራውን ከባድ አድርጎታል።” ሲል በውይይቱ ወቅት ስለቀረበው ስራ ማብራሪያ የሰጠው የቡድኑ አባል ፒተር ላቀው ተናግሯል።የዝግጅቱ ተሳታፊዎች አውደ ርዕዩን ላቀረቡት አባላት ያላቸውን አድናቆት በማቅረብ ለወደፊቱ ከወረራ በፊት እና በኃላም ያሉትን ያካተተ ስራ እንዲሰራ መንገድ ከፋች እንደሆነም ሀሳብ ሰንዝረዋል።ለጥናቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደነበረው የተገለጸው ”አዲስ አበባ ከተማዋ እና ኪነ-ህንፃዋ” መጽሐፍ ደራሲ ፋሲል ጊዮርጊስ በዝግጅቱ በመገኘት ስለአዲስ አበባ አመሰራረት አጭር መሰናዶ አቅርበዋል። ከኖርዌይ ከመጡት የልዑካን ብድን አባላት መካከል አና ናኦሚ ደሱዛ ፣ ኤምሊዮ እና አሌክሳንድሮ ፔቲ በኪነ ህንጻ ዙሪያ የተለያዩ መሰናዶዎችን አቅርበው ውይይትም ተደርጎባቸዋል።የከተማ ማዕከል ሀላፊ እና የቤት እስከ ከተማ አቅራቢ ማህደር ገብረመድህን ይሄን ፕሮጀክት የሰሩትን እና አስተባበሪዎችን አመስግነው አውደ ርዕዩ እስከሚቀጥለው ጥር 30 2011 ዓ.ም ክፍት እንደሚሆን በዝግጅቱ ወቅት ተናግረዋል።

አስተያየት