ጥቅምት 22 ፣ 2014

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት አበይት ሁነቶች

City: Addis Ababaዜና

በግጭቱ ሂደት የተስተዋሉት ዋና ዋና ክስተቶች የሚከተሉት ናቸው።

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት አበይት ሁነቶች

አንድ ዓመት በሆነው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ቀላል የማይባል ውድመት ደርሷል። በሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። ወደ 400 ሺህ የሚጠጉ ለረሃብ ሲጋለጡ ከ2.5 ሚልዮን በላይ ያህሉ ከቀደመ ቀያቸው ተፈናቅለዋል። በግጭቱ ሂደት የተስተዋሉት ዋና ዋና ክስተቶች የሚከተሉት ናቸው።

ጥቅምት 25፣ 2013 – የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ህወሓት በትግራይ ክልል የሚገኙ ወታደራዊ ካምፖች ላይ ድንገተኛ ጥቃት እንደፈጸመ አሳወቁ።

እ.ኤ.አ. በ2018 ዐቢይ ሥልጣን እስከያዙበት ጊዜ ድረስ የብሄር ፖለቲካን ሲቆጣጠር የነበረው ህወሓት ወታደራዊ ትጥቅ መያዙን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ማሰሩን የገለፀው ዐቢይ በመስከረም ወር የፌደራል መንግሥትን ትዕዛዝ በመጣስ ምርጫ ካካሄደ በኋላ የጦርነት ዝግጅት ላይ እንደነበር ተገልዖአል።

በቀጣዮቹ ቀናት የኤርትራ ወታደሮች እና ከአጎራባች የአማራ ክልል ወታደሮች የኢትዮጵያን ጦር ለማጠናከር መንቀሳቀሳቸው ተሰምቷል።

ጥቅምት 30፣ 2013 - ብሔርን መሰረት ያደረገው ግድያ በማይ ካድራ ከተማ ተካሄደ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት ጠፋ። በመጀመሪያ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሰላማዊ ዜጎች በትግራይ ታጣቂዎች ጥቃት ደረሰባቸው። ከዚያም የትግራይ ሰላማዊ ሰዎች፣ በአማራ ታጣቂዎች ጥቃት ደርሶብናል አሉ። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች ከምዕራብ ትግራይ ወደ ሱዳን መሰደድ ጀመሩ።

ሕዳር 5፣ 2013 - ህወሓት ኤርትራ ወታደሮቿን ወደ ትግራይ ልካለች በሚል በአማራ ክልል ወደሚገኙ ሁለት አየር ማረፊያዎች እና ወደ በኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ሮኬቶችን ተኮሰ።

ሕዳር 19፣ 2013 - በትግራይ የተካሄደው ዘመቻ መጠናቀቁን እና ወታደሮች የትግራይን ዋና ከተማ መቐለን መቆጣጠራቸውን በፓርላማ ተገለጸ።

ሕዳር 19-20 - የኤርትራ ወታደሮች በአክሱም ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገድለዋል የሚለው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ይፋ ሆነ።

ጥር - የካቲት 2021 – የይገባኛል ጥያቄ የሚነሳባቸው አካባቢዎች ላይ የመደፈር እና የመፈናቀል ወንጀሎች ስለመፈጸማቸው ተነግሯል። በመጋቢት ወር የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን "የዘር ማጽዳት ድርጊቶች እየተፈጸሙ ነው" ብለዋል።

መጋቢት 14 ፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኤርትራ ወታደሮች ወደ ትግራይ መግባታቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ አረጋገጡ።

መጋቢት 26 - የኤርትራ ኃይሎች ከኢትዮጵያ መውጣት መጀመራቸው ተነገረ። የአካባቢው ነዋሪዎች ግን ወታደሮቹ እንዳልወጡና ሰላማዊ ዜጎችን መግደል መቀጠላቸውን ተናገሩ። ኤርትራ የቀረበባትን ክስ አስተባብላለች።

መጋቢት - የኤርትራ ወታደሮች በቡድን በመደፈር የትግራይ ተወላጆችን የወሲብ ባሪያ አድርገው ስለመያዛቸው የክልሉ ባለሥልጣን ተናግረዋል። ኤርትራ ክሱን አስተባብላለች።

ሰኔ 4 - የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 350ሺህ የትግራይ ተወላጆች በረሃብ እየተሰቃዩ እንደሆነ እና በሚሊዮን የሚቆጠሩት ተጨማሪ ስጋት ላይ ስለመኖናቸው ተናግረዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የእርዳታ ኃላፊ ኢትዮጵያ ርሃብን ለጦርነት ትጠቀማለች ሲል ከሷል። ኢትዮጵያ እርዳታ መከልከሏን ገለጸች።

ሰኔ 16 - 17 - በትግራይ ቶጎጋ ከተማ በደረሰ የአየር ድብደባ በትንሹ 51 ሰዎች ተገድለዋል። የጤና ባለሥልጣኑ ተጎጂዎቹ ሲቪሎች መሆናቸውን እና የተጎዱ ህጻናትን ፎቶ ያሳያል ብሏል። ሰራዊቱ ተዋጊዎችን መምታቱን ተናግሯል።

ሰኔ 22 - የህወሓት ተዋጊዎች በአካባቢው ገጠሮች ለወራት ከዘለቀው ጦርነት በኋላ መቐለን መቆጣጠራቸው ተነገረ። የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደሮች ከምእራብ ትግራይ ስለመውጣታቸው ተሰማ።

ሐምሌ 6 - የህወሓት ተዋጊዎች ወደ ደቡብ እና ምዕራብ እየገፉ የአማራ ክልል አጎራባች አካባቢዎችን መቆጣጠራቸው ተነገረ።

ሐምሌ 6 - ህወሓት ወደ ምስራቅ በመግፋት በአፋር ክልል አጎራባች አካባቢ ያለውን መንገድ እና ወደብ አልባዋ የኢትዮጵያ ዋና ከተማን ከጅቡቲ ወደብ የሚያገናኘው የባቡር መስመር ላይ ጉዳት አደረሱ።

ነሐሴ 17 - ዩናይትድ ስቴትስ በትግራይ በተቀሰቀሰው ግጭት ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣን ተፈጽሟል በሚል በኤርትራ መከላከያ ሰራዊት ዋና አዛዥ ላይ ማዕቀብ ጣለች።

መስከረም 19 - ወደ ትግራይ የሚደርሰው የእርዳታ ቁልቁል ብቻ ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መንግስትን ከስሷል።

ጥቅምት 1 - ኢትዮጵያ የህወሓትን ኃይል ከአማራ እና አፋር ለማስወጣት ያለመ የመሬት ጥቃት ሰነዘረች። በቀጣዩ ሳምንት ኢትዮጵያ በትግራይ የአየር ጥቃትን እንደገና ጀምራለች።

አስተያየት