መጋቢት 8 ፣ 2014

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ለምን ሲሳይ በብሪታንያ ታላቅ እውቅና ተሰጠው

City: Addis Ababaዜና

በ1950ዎቹ መጨረሻ ለትምህርት ወደ እንግሊዝ ሃገር ከሄደች ኢትዮጵያዊት የተወለደው ለምን እናቱ ለማሳደግ ዝግጁ ስላልነበረች በማደጎ በእንግሊዛዊያን አሳዳጊዎቹ እጅ እንዳደገ የህይወት ታሪኩ ያስረዳል።

Avatar: Addis Zeybe
አዲስ ዘይቤ

የኢትዮጵያን አስደናቂ የከተማ ባህል፣ ታሪክ፣ ወቅታዊ ዜና እና ሌሎችንም ያግኙ።

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ለምን ሲሳይ በብሪታንያ ታላቅ እውቅና ተሰጠው
Camera Icon

Credit: Wegan today

ኢትዮ-እንግሊዛዊው ስመጥር ገጣሚ ለምን ሲሳይ በትላንታናው እለት “ብሪቲሽ ኢምፓየር አዋርድ” የተሰኘ የላቅ የክብር እውቅና ሽልማት ተበረከተለት።

በፈረንጆቹ 2012 የለንደን ኦሎምፒክ ‘ኦፊሺያል’ ገጣሚ የነበረው የ54 ዓመቱ ለምን ሽልማቱ የተበረከተለት በሥነ-ጽሑፍና በበጎ አድራጎት ስራዎቹ ላበረከተው የላቀ አስተዋጻኦ መሆኑ ታውቋል።

ለምን የበርካታ ተወዳጅ መጻሕፍት፣ የተውኔት ድርሰቶች እና የግጥሞች ደራሲ ሲሆን ዘጠኝ መጻሕፍትና ሰባት የመድረክ ተውኔቶች እንዲሁም አራት የራዲዮ ድራማዎችን ጽፏል።

በተጨማሪም ከ2015 ጀምሮ የማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆኖ ተመርጧል። ከሁለት የእንግሊዝ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችም የክብር ዶክትሬት ተቀብሏል።

በእንግሊዝ በርክሻየር ከተማ በጥንታዊው የዊንዘር ቤተ መንግስት በተዘጋጀ መርሀግብር የንጉሳዊ ቤተሰብ አባላትና ሌሎች እንግዶች ባሉበት ሽልማቱ ተበርክቶለታል።

በ1950ዎቹ መጨረሻ ለትምህርት ወደ እንግሊዝ ሃገር ከሄደች ኢትዮጵያዊት የተወለደው ለምን እናቱ ለማሳደግ ዝግጁ ስላልነበረች በማደጎ በእንግሊዛዊያን አሳዳጊዎቹ እጅ እንዳደገ የህይወት ታሪኩ ያስረዳል።

ለምን ሽልማቱን በተቀበለበት ወቅት “ሰዎች እነዚህን ሽልማቶች ሲያገኙ “ለእናቴ ወይም ለአባቴ ለመንገር  ጓጉቻለሁ፤ ምክንያቱም በዚህ  ኩራት ይሰማቸዋልና” ይላሉ።

“ይህ እኔጋ አይሰራም። ምክንያቱ ደግሞ ከግል ታሪኬ የመነጨ በመሆኑ ነው። ሽልማቱ ቤተሰቦቼ ላይ ሊፈጥር ይችል የነበረውን ስሜት ጨምሮ እኔ ላይ ጥልቅ ስሜት ፈጥሯል” በሏል።

አስተያየት