ኅዳር 8 ፣ 2011

ታላቁ ሩጫ፣ የብሶትና ተቃውሞ መግለጫ

ሶምሶማወቅታዊ ጉዳዮችፊቸር

በ30ዎቹ እድሜ መጀመሪያዎቹ ላይ የሚገኙት፣ የልብ ወዳጆች ወዳጆች የሆኑት ሄኖክ ግዛው እና ኩሩቤል ጥላዬ ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ውድድሮች ውጪ የታላቁ ሩጫን…

ታላቁ ሩጫ፣ የብሶትና ተቃውሞ መግለጫ
በ30ዎቹ እድሜ መጀመሪያዎቹ ላይ የሚገኙት፣ የልብ ወዳጆች ወዳጆች የሆኑት ሄኖክ ግዛው እና ኩሩቤል ጥላዬ ከመጀመሪያዎቹ ሁለት ውድድሮች ውጪ የታላቁ ሩጫን ላለፉት 16 አመታት ሳያቋርጡ ከሮጡት የሸገር ነዋሪዎች መካከል ናቸው፡፡ሁለቱ ወጣቶች ከብዙዎቹ የከተማይቱ ነዋሪዎች በተለየ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን አብዝተው የሚያዘወትሩት ሁለቱ ወጣቶች ለታላቁ ሩጫ ትልቅ ቦታ አላቸው፡፡ሄኖክና ኩሩቤል በተለይ ውድድሩ የሚካሄድበት ህዳር ወር ሲቃረብ በቀን ሁለት ጊዜያት (ንጋትና አመሻሽ ላይ) ወደመስቀል አደባባይ በመምጣት ለውድድሩ ራሳቸውን ያዘጋጃሉ፡፡ ከሰሞኑም ብርዳማ አንዳንዴም ደግሞ ዝናባማ የሆነው ተለዋዋጭ አየር ሳይበግራቸው በግዙፉ የከተማይቱ የስፖርት ስፍራ ልምምዳቸውን ሲያካሄዱ ከርመዋል፡፡በትምህርት ደረጃቸው እውቀት ከጠለቃቸው እና  በስራ ገበታቸውም ቢሆን በትልቅ የሹመት ቦታ ላይ ለሚገኙት ሄኖክና ኩሩቤል ታላቁ ሩጫ ከስፖርታዊ ፉክክርነትም ሆነ የአካላዊ ጤና መጠበቂያነቱ ያለፈ ትልቅ ትርጉም ይዞ ቆይቷል፡፡ሁለቱ ወጣቶች ነፍስ ካወቁበት ጊዜ አንስቶ ከወራት በፊት የዐቢይ አስተዳደር ወደስልጣን እስከመጣበት ጊዜ ድረስ መንግስትን ባገኙት አጋጣሚ ሲተቹና ሲነቅፉ በመቆየታቸው ታላቁ ሩጫን እንደትልቅ የውስጣቸውን መተንፈሻ መድረክነት እንደተጠቀሙበትም ይናገራሉ፡፡"እንዴ ምን ልበልህ?! እኛ እኮ ስፖርትን በየዕለቱ ሊባል በሚችል ደረጃ እናዘወትራለን፤ ነገር ግን ታላቁ ሩጫ እስኪደርስ ያለን ጉጉት በስማም!! ሰዎች ውድድሩን ለተለያየ አላማነት ያስቡታል፤ እኛ ግን አምባገነኑን መንግስት መቃወሚያ ፌስቲቫል አድርገን ነበር የምናየው፡፡"እርግጥ ነው ብዙ ሌሎቹም የእኛ አይነት መንፈስ እንዳላቸው እረዳ ነበር፤ አብረንም በነበረው አምባገነን መንግስት ላይ የተቃውሞ መልዕክት ስናስተላልፍ ቆይተናል፡፡" ሲልም ሄኖክ ይናገራል፡፡የመጀመሪያዎቹ አመታትታላቁ ሩጫ በ1994 አሐዱ ብሎ ሲበሰር ብዙ መልካም ነገሮች ብልጭ ብለው ወዲያው ከሚከስሙበት የሀገራችን ልማድ አንፃር ማንም እዚህ ይደርሳል ብሎ አልጠበቀም፡፡ ነገር ግን እድለኝነትም በሚመስል መልኩ ውድድሩ ተወዳጅነትን ለማትረፍ ብዙ አመታትን አላስፈለገውም፡፡በውድድሩ የመጀመሪያ ጊዜያት (የውድድሩን መስራች) ሀይሌ ገብረሥላሴን ጨምሮ ስለሺ ስህን፣ ብርሃኔ አደሬ፣ እና ጥሩነሽ ዲባባ የመሳሰሉ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ላይ ትልቅ አሻራ ጥለው ያለፉ አትሌቶች መሳተፍ ለውድድሩ ድምቀትና ተወዳጅነት በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ሌላው ነገር ውድድሩ ያለምንም መቋረጥ በተከታታይ መደረጉ ብዙዎችን ለመሳብና ከጎኑ ለማሰለፍ እንደጠቀመው ይገለፃል፡፡ ከሶስተኛው ውድድር አንስቶ ዘንድሮ ለተከታታይ 16ኛ ጊዜ የሚሳተፉት ሄኖክና ኩሩቤልም ሀሳቡን ይጋሩታል፡፡"ውድድሩ በ1994 ዓ.ም. ከተጀመረ በኋላ ሁለት አመታት በተከታታይ ሲደረግ አስታውሳለሁ፡፡ በሀገራችን የጎዳና ላይ ሩጫ ያልተለመደ ቢሆንም ያማረ የሚባል አይነት ነበር፤ እኛም እንሞክረው ብለን ሰምጠን ቀረን፡፡" ሲልም ኩሩቤል የመጀመሪያዎቹን አመታት ያስታውሳል፡፡ድህረ 97 እና የብሶት መድረክነትታላቁ ሩጫ በመጀመሪያዎቹ አመታት ከመደበኛ ሩጫነት ባለፈ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ረገድ እምብዛም ነበር፡፡ በተለይ ደግሞ ብዙ ህዝብ የሚሳተፍባቸውን የአደባባይ ስፍራ ትዕይንቶች የተቃውሞ መድረክ መነሻ አድርጎ ይመስድ ለነበረው ህውሓት መራሹ የቀድሞ መንግትሥት የመጀመሪያዎቹ አመታት ከብሶት የፀዱ የሚባሉ አይነት ነበሩ፡፡ነገሮች መቀየር የጀመሩትም ከምርጫ 97 በኋላ መሆኑ ይገለፃል፡፡ "ይገርምሀል እኛ ከ97 ምርጫ በፊት የነበረውን አንድ አመትም ተሳትፈናል፡፡ ነገር ግን በተቃውሞ መድረክነቱ ትዝ አይለኝም፡፡ ይልቅ ከ 97 ምርጫ በኋላ ነው ነገሮች የተጋጋሉት፡፡" በማለትም ሄኖክ ለማስረዳት ይሞክራል፡፡በ97ቱ ምርጫ ሙሉ ለሙሉ ድምፁን ለቅንጅት ሰጥቶ የነበረው የከተማዋ ህዝብ ከምርጫው በኋላ በተከሰቱ ችግሮች ድምፄን ተነቄያለሁ ብሎ ማሰቡ እንዲሁም ደግሞ ከኑሮ መናር ጀምሮ የተለያዩ ማኀበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ በደሎች መደጋገም ባገኘው አጋጣሚ መንግስትን እንዲቃወም እና ብሶቱን እንዲያሰማ እንደገፋው ተደጋግሞ ተገልጿል፡፡በሰላማዊ ሰልፍና ሌሎች መንገዶች ብሶቱን እንዳያሰማ ተከልክሎ የነበረው የአዲስ አበባ ህዝብም ታላቁ ሩጫን ብሶቱን ለማሰማት እንደብቸኛ አማራጭ መውሰዱም ይጠቀስ ነበር፡፡ከድህረ ምርጫው በኋላ በነበሩ ተከታታይ አመታት ውስጥም በጣም ብዙ የተቃውሞ ድምፆች በውድድሩ ላይ ይስተጋቡ እንደነበር ሄኖክና ኩሩቤል ቀዳሚ ምስክሮች ናቸው፡፡በተለይም ደግሞ በወቅቱ "እንዴት ይረሳል? እንዴት ይረሳል? ረሳሽው ወይ፣ 97ን?""ኢትዮጵያችን ሃብታም፤ እኛ ኪሳችን ባዶ፤ ቤታችን ባዶ። ባለስልጣን ሃብታም፤ በሙስና፣ በሌብነት፣ በዘረፋ""ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም፣ ባባቶቻችን ደም፤ እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም፤ ወያኔ ይውደም።""የመለስ ስልጣን ገደብ ይኑረው""ታላቁ ሩጫ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ብሶት መግለጫ" የሚሉት የብሶት ድምፆች ቀድሞው የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ቀድሞም ቢሆን ለተቃወሙት ምላሹ አፈና እንደሆነ የሚነገርለት የያኔው የመለስ ዜናዊ አስተዳደር በታላቁ ሩጫ ላይ የተመለከታቸውን የድህረ 97 ብሶታዊ እንቅስቃሴዎች ተከትሎ ውድድሩን በአይነ ቁራኛ እንዲከታተል እንዳነሳሳው ይገመታል፡፡በውድድሩ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የሲቪልና መደበኛ የፀጥታ ሀይል በመመደብ በውድድሩ ላይ የተቃውሞ ድምፆች እንዳይሰሙ ጥረት እስከማድረግ መደረሱም ይታወሳል፡፡"ውድድሩ ላይ እኮ የሚሳተፈው የፀጥታ አስከባሪ ከሯጮቹ በላይ ነው ጭማሪ ያሳየው፡፡" በማለትም ሄኖክ ሁኔታውን በስላቅ ይገልፀዋል፡፡ኩሩቤል በበኩሉ "ከመደበኛው ሀይል በተጨማሪ ተሳታፊ መስለው የሚሮጡ የመንግስት ደኅንነቶች ይበተናሉ ስለሚባልም አንተ በመንግስት ላይ ስትጮህ ፈርተው የሚሸሹም ነበሩ፡፡" በማለት የቁጥጥሩን እየጠበቀ መምጣት ተከትሎ ህዝቡ በነፃነት ተቃውሞውን ለማሰማት ፍርሀት እንደነበረበት ይጠቁማል፡፡በውድድሩ ላይ የነበሩ ተቃውሞዎች ያሰጋው የሚመስለው መንግስትም ከፍተኛ የፀጥታ ሀይል በመመደብ ተቃውሞዎች እንዳይደረጉ ከማድረግ ያለፈ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ለዚህም ማሳያው ውድድሩን ተቃውሞ ከሚሰነዘርባቸው ትልልቅ መንግስታዊ ተቋማት ማራቅ ነው፡፡ከ2003 አንስቶም ውድድሩ በመደበኛነት ይካሄድበት ከነበረውና ቤተመንግስትን ጨምሮ የተለያዩ ትልልቅ መንግስታዊ ተቋማት ከሚገኙበት የአራት ኪሎ መስመር ወደቄራ እና ጎተራ ማሳለጫ መንገድ እንዲዘዋወር መደረጉ በቀዳሚ ማስረጃነት ይጠቀሳል፡፡በወቅቱ የውድድሩ ስፍራ መቀየርን ተከትሎም "ዞረች አሉ በማሳለጫ ቤተመንግስት እንዳትንጫጫ" የሚል ትልቅ ቅኔ አዘል መልዕክት በውድድሩ ላይ ተደምጧል፡፡በዚህ ሁሉ የመንግስት ተቃውሞን የማዳፈን ጥረቶችም ውስጥ ግን የውድድሩ ተሳታፊ የሆነው የከተማው ነዋሪ በአመት አንድ ጊዜ የሚያገኛትን እድል በመጠቀም ብሶቱን ከማሰማት አልተመለሰም፡፡"ወያኔ ሌባ፣ ለዛሬ አመት በአዲስ መንግስት""ምን አለ? እስክንድር ምን አለ? አገሬን ትቹ አልሄድም አለ!! ምን አለ? ተመስገን (ደሳለኝ) ምን አለ? አገሬን ትቼ አልሰደድም አለ!!""ሰላም ነው እያለ መሬቱን ሸጠው" የሚሉት ድምፆችም የውድድሩ አንድ ትልቅ ድምቀቶች ነበሩ፡፡ ከዚህ ባለፈም ከአረብ ፀደይ አብዮት ጋር በተያያዘ "እንደ ጋዳፊ አይቀርም ጥፊ፤ ሳንፈልጋቸው 20 አመታቸው" የሚሉ የተለያዩ ትንቢት አዘል መፈክሮች መሰማት ቀጥለው ነበር፡፡የጥቁር ሪባን ተቃውሞና አለመግባባትበ2006 የተደረገው ውድድር ከዛ ቀደም በይፋ ሳይነገሩና ዝግጅት ሳይደረግባቸው በውድድሩ ላይ ይሰሙ የነበሩ ብሶቶችና ተቃውሞዎችን በይፋ እንዲደረጉ ቅስቀሳ የተደረገበት ነው፡፡በወቅቱ ተፅዕኖ ፈጣሪው ሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን መፈናቀል ተከትሎ የውድድሩ ተሳታፊዎች ጉዳቱን በሐዘን ለመግለፅ ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ ጥሪ ያቀረበበት በውድድሩ አስተባባሪዎች ዘንድ ደግሞ 'የታላቁ ሩጫ ውድድሩ ስፖርታዊ እንጂ ፖለቲካዊ መልዕክት ማስተላለፊያ አይደለም' በሚል ጥሪው ላይ ተቃውሞ የቀረበበት ወቅት ነበር።የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው ብርሀኑ ተክለያሬድ ጉዳዩን በማስመልከት ከአንድ ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቆይታም "በሳውዲ አረቢያ እየደረሰ ያለው የዜጐች ሰቆቃ የፖለቲካ ጉዳይ አይደለም። በሩጫው የሚሳተፉ ሰዎች ጥቁር ሪቫን ያድርጉ ስንል ሰማያዊ ፓርቲን ይደግፉ ማለታችን አይደለም። ለወገኖቻቸው ሰቆቃ ሐዘናቸውን ይግለፁ፤ ለአለም አቀፍ ህብረተሰብም ያስታውቁ ነው ያልነው፡፡" ሲል ተደምጧል፡፡በመጨረሻም በሁለቱ አካላት መካከል መግባባት ላይ ሳይደረስ ውድድሩ ለመካሄድ በቅቷል፡፡ በወቅቱ ከውድድሩ በፊት በሚደረገው ጥብቅ ፍተሻ ምክንያት ጥቁር ሪቫኖቹ በውድድሩ ላይ መታየት ባይችሉም የፓርቲው አባላትና የተወሰኑ የውድድሩ ተሳታፊዎች የሳውዲውን መፈናቀል በመቃወም ድምፃቸውን አሰምተው ነበር፡፡ዘንድሮስታላቁ ሩጫ ባለፉት 18 አመታት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር የመደረግን አስፈሪ ድባቦች ጭምር በስኬት ተሻግሮ 'የአፍሪካ ግዙፉ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር' የሚል ስያሜን አስከማግኘት ደርሷል፡፡ባለፉት ተከታታይ 16 አመታት በውድድሩ ሲሳተፉ በቆዩት ሄኖክና ኩሩቤል ዘንድም የዘንድሮው ውድድር ልቆ ተገኝቷል፡፡ ባለፉት አመታት ከፀጥታ አካላት ጋር እየተደባበቁ በመንግስት ላይ ያሰሙት የነበረው ተቃውሞም በዚህኛው መሻሩን ይገልፃሉ፡፡"ያው ዘንድሮ የፌሽታ ሩጫ ተቃውሞ የለም፡፡ አዲስ መንግስት መጥቷል፤ ነገሮች ገና ቢሆኑም አሪፍ ነገሮች አሉ፡፡" ሲል ሄኖክ ይናገራል፡፡ የልብ ወዳጁ የሆነው ኩሩቤልም 'ልክ ነው' በሚመስል አዝማሚያ አንገቱን ይነቀንቃል፡፡'ታላቁ ሩጫ የብሶት መግለጫም' በነገው ዕለት ማለዳ ሸገርን እንደሚያደምቅ ይጠበቃል፡፡

አስተያየት