ግንቦት 15 ፣ 2012

በአዲስ ዘይቤ የተዘጋጀ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሠራተኞች መብት ጥሰትን የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም በናሁ ቴሊቪዥን ዛሬ ማታ ይታያል

ባለሙያነትወቅታዊ ጉዳዮችፊቸር

በአዲስ ዘይቤ ዝግጅት ክፍል የተሰናዳ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሠራተኞች መብት ጥሰትን የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ግንቦት 15፣ 2012 ዓ.ም ከምሽቱ…

በአዲስ ዘይቤ የተዘጋጀ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሠራተኞች መብት ጥሰትን የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም በናሁ ቴሊቪዥን ዛሬ ማታ ይታያል
በአዲስ ዘይቤ ዝግጅት ክፍል የተሰናዳ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሠራተኞች መብት ጥሰትን የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም ዛሬ ግንቦት 15፣ 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በናሁ ቴሊቪዥን ይታያል።አዲስ ዘይቤ በተለያየ ወቅት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች እና ድርጅቱ መካከል የነበረ አለመግባባትን ሲዘግቡ ከነበሩ ግንባር ቀደም ሚዲያዎች መካከል መሆኗ ይታወሳል። ይሁንና ጉዳዩ መጠነኛ የሚባል የዜና ሽፋን ቢኖረውም እልባት ባለማግኘቱ ወደ ዝግጅት ክፍላችን የሚመጡ የሠራተኛው እሮሮዎች ባለመቆማቸው ጉዳዩ ውስብስብ እንደሆነ ተረዳን።
በወቅቱ በጥላቻ ንግግር ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨባጫ ዘጋቢ ፊልም እያዘጋጀን ነበር። የአየር መንገድንም ጉዳይ ሰፊ እና ውስብስብ ከመሆኑ አንጻር በዘጋቢ ፊልም መልክ ለማዘጋጀት የዝግጅት ክፍላችን አቀደ። ይህንን ውሳኔ ስንወስን በቂ መረጃ አግኝተን እንሰራው ይሆን የሚል ስጋት ውስጣችን ማጫሩ አልቀረም። ነገር ግን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሠረታዊ ማኀበር አመራር አና የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኀበራት ኮንፌዴሬሽን(ኢሠመኮ) ፕሬዝዳንት ጉዳዩን በዝርዝር በማስረዳት ተባበሩን።በትንሹ የጀመርነው ፕሮጀክት ሰፍቶ በደል ደረሰብን የሚሉ ሠራተኞች፣ የሠራተኛ ማኀበር አባላት፣ የሠራተኛ ማኀበራት ኮንፌዴሽን፣ ጉዳያዊ ዕውቅት ያላቸው አንጋፋ ሠራተኞች እና ከህግ ባለሙያ ጋር በርካታ ሰዓታት የፈጀ ቃለ መጠይቅ አደረግን። የምንሰራው ዘገባ የተሟላ እንዲሆን በማሰብ አንድም የሙያችን ስነ ምግባር ግድ ስለሚለን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እና የቀድሞ ለሚባለው የሠራተኛ ማኅበር በኢሜልና በደብዳቤ ምላሽ ጠይቀን ነበር፡፡ በወቅቱ የድርጅቱ ተጠባባቂ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩት አቶ ሔኖክ ሲራክ የኢሜይል መልዕክታችንን ተቀብለው ምላሽ በመስጠት የድርጅታችንን የሚዲያ ፈቃድ እና ያነጋገርናቸውን የድርጅቱ ሠራተኞች የተቀረፀ ፋይል እንድንልክላቸው ጠየቁ፡፡ እኛም ከብሮድካስት ባለስልጣን የተቀበልነውን ፍቃድ አያይዘን በመላክ ቃለ መጠይቅ ያደረኛቸውን ሠራተኞች ሰነድ አንልክም፤ ነገር ግን ለድርጅቱ ያዘጋጀነውን ጥያቄዎች አስቀድመን መላክ እንደምንችል አስረዳን፡፡ የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ይህንን ምልልስ አቋርጠው እንከሳቹሃለን የሚል ማስፈራሪያ ላኩለን፡፡ ኢሜይሉ ከዚህ ፅሑፍ ጋር ተያይዟል፡፡እኛም የድርጅቱ ምላሽ በመጉደሉ ቅር ብንሰኝም ያሰባሰብነውን ሰፊ መረጃ አሰናድቶ ወደ ህዝብ ለማቅረብ መሯሯጥ ጀመረን፡፡ የኮረና ቫይረስ በኢትዮጵያ መከሰት የቤት ስራቸንን ባሰብነው ጊዜ እንዳንጨርስ አገደን፡፡ ባሳለፍነው እሁድ ግንቦት 9፣ 2012 ዓ.ም እንደምንም ጨርሰን ለማደር አሰበን እስከ ለሊት ዘጠኝ ሰዓት ሰርተን ከትንሽ ለቀማ በቀር ስራውን አጠናቀቅን፡፡በንጋታው ጠዋት ወደ ቢሯችን ስንመለስ እንደተውነው አላገኘነውም፡፡ ቢሯችን ተዘርፎ አድሯል፡፡ አራት ላፕቶፕ ኮምፒዩተሮች እንዲሁም የደክምንበት በኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች ላይ የደረሰ የመብት ጥሰት የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም ፋይል ማስቀመጫ(ሀርድ ዲስክ) ተዘርፎ አድሯል፡፡ ወዲያውኑ ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አመለከትን፡፡ ፖሊስ ተጠርጣሪዎች ናቸው ያላቸውን አስሮ ምርመራ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡እኛም ሌሎች ውድ ዋጋ የሚያወጡ ንብረቶች እያሉ የዚህ ፕሮጀክት ሰነዶች እና ላፕቶፖች ብቻ ተለይተው መሰረቃቸው ቢያሳስበንም ጉዳዩን ለመርማሪ ባለሙያዎቹ ተትን ወደ ስራችን ተመለስን፡፡ ከፕሮጅክቱ የተወሰነውን ምትክ ፋይል ቀድተን ስላስቀመጥን ማድረግ የምንችለውን ተመካከርን፡፡ ምንም እንኳን ያለን ሰነድ የተሟላ ሆኖ በመጀመሪያ እንደተዘጋጀው ባይሆንም የተወሰነ የጥራት ጉድለት ቢኖርበትም ዋናው ሀሳብ ያስረዳል ብለን ሳላሰብን ባለን ሰንድ ጨርሰናዋል፡፡ ብዙ ሰው ጋር እንዲደርስ በነገው ዕለት በናሁ ቴሌቪዥን የሚተላለፍ ሲሆን ከዚያ በኋላ በአዲስ ዘይቤ ዩቱብ ቻናል ሁላችሁም ጋር እንዲደርስ እናደርጋለን፡፡የተባበሩን ናሁ ቴሌቪዥንን፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ መሠረታዊ የሠራተኞች ማኅበር አመራር አባላት እንዲሁም ኢሰመኮን እናመሰግናለን፡፡የአዲስ ዘይቤ ዝግጅት ክፍል

አስተያየት