ግንቦት 24 ፣ 2012

በኢትዮጲያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደራጀ የመማርያ ማስተማርያ ዌብሳይት ተዘጋጅቷል

ትምህርትወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎች

ኢኖቬት መልቲ ሚዲያ በኢኖቬት መልቲ ሚዲያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤት በሆኑት አቶ እንዳልካቸው ታየ ሃሳብ አመንጭነት አምስት አባላት ያሉት…

በኢትዮጲያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተደራጀ የመማርያ ማስተማርያ ዌብሳይት ተዘጋጅቷል
 ኢኖቬት መልቲ ሚዲያ በኢኖቬት መልቲ ሚዲያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ባለቤት በሆኑት አቶ እንዳልካቸው ታየ ሃሳብ አመንጭነት አምስት አባላት ያሉት የመማርያ ማስተማሪያ ዌብሳይት ነው። በኢትዮጲያ በዌብሳይት ማስተማር ለሚፈልጉ መምህራን እና ከትምህርት ውጭ ሙያቸውን ለሌሎች አጋርተው ገቢ ማግኘት ለሚፈልጉ ሰዎች በማህበራዊ ሚዲያ ታግዘው እውቀታቸውን ማዳበር ከሚፈልጉ ሰዎች ጋር የሚያገናኝ  በኢትዮጵያ የተደራጀ የመማርያ ማስተማርያ ዌብሳይት በኢኖቬት መልቲ ሚዲያ አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቷል። ኤሌክትሮኒክ ለርኒግን በመጠቀም የሚሰጡ አጫጭር ትምህርቶችን ሰዎች ካላቸው ጊዜ ጋር በማጣጣም በቀላሉ በመማር እራሳቸውን እንዲያሻሽሉ የሚያግዝ የትምህርት ተቋም ነው። ኢኖቬት መልቲ ሚዲያ ላይ ለማስተማር የሚመጡ መምህራን በሚያስተምሩበት ትምህርት የሰለጠኑበትን የትምህርት ማስረጃ በቅድሚያ ማቅረብና ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው የገለፁት አቶ እንዳልካቸው ይህም በዌውብሳይቱ የሚሰጡ ትምህርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ አድርጎታል ይላሉ። ኢኖቬት መልቲ ሚዲያ ከማህበራዊ እና ከተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርቶች በተጨማሪ የኮምፒውተር እና የሙያ ትምህርቶች የሚሰጡበት ገፅ ነው። የሙያ ትምህርት የሚሰጡ መምህራንም የትምህርት ማስረጃቸውን ማቅረብ አይጠበቅባቸውም። እያንዳንዱ መምህር ለሚያስተምረው ትምህርት ተማሪዎች የሚከፍሉትን ክፍያ የሚወስነው መምህሩ ነው። መምህራኖች እንዲከፈላቸው ከሚጠይቁት ክፍያ 60 በመቶ የሚሆነው የመምህራኖቹ ድርሻ ሲሆን 40 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።በኢኖቬት መልቲሚዲያ ዌብሳይት የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች ከአማርኛ እና ከእንግሊዘኛ ውጭ በሌሎች በኢትዮጲያ በሚነገሩ ቋንቋዎች የሚሰጡ ሲሆን ለጊዜው ትግርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ሀዲያ እንዲሁም ሶማልኛ ቋንቋዎች ተመርጠው አገልግሎት እየሰጡ ነው። ይህ ዌብሳይት በኢትዮጲያ የሚገኙ መምህራን በብዛት እንዲሳተፉበት የተደረገ ሲሆን በውጭ ሃገራት የሚገኙ መምህራንንም የሚያሳትፍ ነው።በዌብሳይቱ ላይ ተመዝግበው የሚማሩ ተማሪዎች ከፍለው የሚማሩትን የትምህርት አይነት ሲጨርሱ ሰርትፊኬት ይወስዳሉ። ተማሪዎቹ ሰርቲፊኬቱን የሚወስዱት በዌብ ሳይቱ ላይ የሚለቀቁትን ትምህርቶች በሚገባ መከታተላቸውን ለማወቅ የተዘጋጁትን ፈተናዎች በአግባቡ ሰርተው ወጤታቸው 85 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ሲሆን እንደሆነ ለአዲስ ዘይቤ ያስረዱት አቶ እንዳልካቸው 85 ከመቶ ማምጣት ላልቻሉት ተማሪዎች ደግሞ ትምህርቱን ደጋግመው በማየት እና በማንበብ እንደገና ተፈትነው የተቀመጠውን መስፈርት ሲያሟሉ ሰርተፌኬት እንደሚሰጣችው አቶ እንዳልካቸው ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል ። 

አስተያየት