ይህንን የኢትዮጲያ የወላጆችን ችግር ለማቅለል ያለመ በራቪ ሽክኩር የሚመራ ሶስት አባላት ያሉት ሆም ስኩሊንግ ኢትዮጲያ (Home-Schooling Ethiopia) የተሰኘ የቴሌግራም ቻናል ተከፍቷል፡፡ በሚያዝያ 29 የተጀመረው ይህ የቴሌግራም ቻናል ወላጆች ልጆቻቸውን በቤት ወስጥ በቀላሉ ማስተማር እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀ ገፅ ነው።በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በአለም ላይ ወላጆች ልጆቻቸውን በቤት ማስተማር ኣስቸጋሪ እንደሆነባቸው ይናገራሉ። ትምህርት የተዘጋበትን ሰዓት እንደ እረፍት ሰዓት በማየት ከወላጆቻቸው የሚሰጧቸውን ትእዛዞች ያለመቀበል ችግር እንዳለ ከዚህ መርሐ ግብር ጀማሪዎች መካከል አንዷ የሆነችው ወ/ሪት ሉላ ይትባለህ ለአዲስ ዘይቤ ተናግራለች። ልጆች የወላጆቻቸውን ትእዛዝ ያለመቀበላቸው፣ በቤት ወስጥ ትምህርት ለመማር የሚጋብዝ የተመቻቸ ሁኔታ አለመኖር እንዲሁም ከዚህ በፊት ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር የሚያሳልፉት ጊዜ አጭር ስለነበር አሁን ላይ ልጆቻቸውን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል።በሆም ስኩሊንግ የተሰኘው የቴሌግራም ገፅ ከላይ የተጠቀሰው ችግር ላጋጠማቸው ወላጆች እፎይታን የሚሰጥ ነው ያለችው ወ/ሪት ሉላ በዚህ የቴለግራም ገፅ ለወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት በቤት ወስጥ በቀላሉ ማስተማር እንደሚችሉ የሚያሳዪ ፎቶዎች እንዲሁም በድምፅ የታገዙ ምክሮች በቀላሉ በማግኘት ከልጆቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በማስተካከል ማስተማር እንደሚችሉ ለአዲስ ዘይቤ ተናግራለች።