ሚያዝያ 17 ፣ 2012

የመስቀል አደባባይ የመልሶ ማልማት ስራ ተጀምሯል፤ የሚመለከታቸው የሙያ ማኅበራት መረጃ የላቸውም

City: Addis Ababaወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎችኹነቶች

(አዲስ ዘይቤ)በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው ታሪካዊው የመስቀል አደባባይን በአዲስ መልክ የማልማት ስራ ተጀምሯል። ከተማዋ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት…

የመስቀል አደባባይ የመልሶ ማልማት ስራ ተጀምሯል፤ የሚመለከታቸው የሙያ ማኅበራት መረጃ የላቸውም
(አዲስ ዘይቤ)በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው ታሪካዊው የመስቀል አደባባይን በአዲስ መልክ የማልማት ስራ ተጀምሯል። ከተማዋ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ነዋሪው በመጠኑ በቤቱ በመከተቱ ምክንያት ከወትሮው መቀዛቀዝ ቢታይባትም በመስቀል አደባባይ ግን በስራ ላይ ያሉ የግንባታ መኪናዎች እና ሠራተኞች ከወዲያ ወዲህ ሲንቀሳቀሱ ተስተውሏል፡፡ከዚህ በፊት `መስቀል አደባባይ ለህዝባዊ አደባባይነት በሚመጥንና በዘመናዊ መልኩ’ መልሶ ለመገንባት ቅድመ ዝግጅት እንደተጠናቀቀ በፋና ቴሌቪዥን ተዘግቦ የነበረ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በአንድ ንግግራቸው ጠቆም አድርገው ከማለፋቸው በስተቀር ስለ መልሶ  ግንባታው ዝርዝር መረጃ አልተገለፀም፡፡[caption id="attachment_1843" align="aligncenter" width="526"] መስቀል አደባባይ በመልሶ ግንባታ ላይ[/caption]ስለ ፕሮጀክቱ መረጃ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕሬስ ሴክሪታሪ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት ፌቨን ተሾመ የልማት ስራውን በባለቤትነት  የጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እንደሚያሰሩት ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት ተቆጥበው በሚቅጥለው ሳምንት የፕሮጀክቱ የመክፈቻ መርሐ ግብር እንደሚኖርና ዝርዝር መረጃው ይፋ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ቀደም ሲል 1400 ተሽከርካሪ ለማቆም የሚያስችል የመኪና ማቆሚያ፣ ፋውንቴንና የተለያዩ መዝናኛዎችን እንደሚያካትት ስለተገለፀው መልሶ ማልማት የሚያቁት ነገር እንዳለ የጠየቅናቸው የኢትዮጲያ የኪነ ህንፃ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አማኑኤል ተሾመ በባለቤትነት ከሚያሰሩት አካላት ማኅበሩ ምንም መረጃ እንዳልደረሰው ተናግረው ነገር ግን ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ በቴሌዢዥን መስኮት ስለ ልማቱ የሰጡትን መግለጫ እንድሰሙ ተናግረዋል።የኢትዮጲያ የከተማ ፕላነሮች ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሮቤል የሽዋስ በበኩላቸው ማኅበራቸው ምንም አይነት የማማከር ስራ እንዳልተጠየቀ እና መረጃው እንደሌላቸው የማኅበሩ አባላት መሳተፋቸውን እንደማያውቁ ገልፀዋል፡፡ እንደዚህ አይነት ታሪካዊ ቦታዎች የመልሶ ማልማት ስራዎች ሲኖሩ ቀደም ብለው ለህዝብ፣ ለታሪክ አዋቂዎች እንዲሁም ለባለሙያዎች ክፍት የሆኑ ውይይቶች መዘጋጀት እንዳለባቸው አስረድተዋል።በከተማ ውስጥ የሚደረጉ ማንኛውም የልማት ስራዎች ለከተማ እድገት ጥሩ እንደሆነ የገለፁት አቶ አማኑኤል የመስቀል አደባባይ ታሪካዊ አሻራውን በመልሶ ልማቱ ምክንያት ያጣል አያጣም ከሚል አስተያይት ተቆጥበዋል፡፡ ስለ ታሪካዊ ይዘቱ አስተያየት ለመስጠት መጀመሪያ የልማት ስራው ምን እንድሚያካትት እና ንድፉ ምን እንደሚመስል ማወቅ እንደሚያስፈለግ ተናግረዋል።  አያይዘውም  በአንድ ሃገር ውስጥ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ላይ ሃገር በቀል ባለሙያዎች ሲሳትፉ ጥሩ የሆነ ስራ መስራት ይቻላል። ነገር ግን በዚህ የመልሶ ግንባታ ስራ ላይ በኢትዮጲያ የሚገኙ የኪነ ህንፃ ባለሙያዎች ተሳትፎ ምን ያህል እንደሆነ እርሳቸው የሚመሩት ማኅበር እንደማያውቅ ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።ይህ ዘገባ ተሰርቶ ካለቀ በኋላ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ መስቀል አደባባይን ጨምሮ በከተማዋ ሊሰሩ የታሰቡ ስራዎችን የሚያሳይ ምስል ከሳች ቪዲዮ(Walk through animation) በፌስቡክ ገፃቸው  ለቀዋል፡፡

አስተያየት