ሚያዝያ 14 ፣ 2012

ኢትዮጵያዊው የፎቶ ግራፍ ባለሙያ ሙሉጌታ አየነ አለምአቀፍ ሽልማት አሸነፈ

ዜናዎችኹነቶች

ኢትዮጵያዊው የፎቶ ግራፍ ባለሙያ ሙሉጌታ አየለ በየአመቱ በሚያዘጋጀው አለም አቀፍ ፕሬስ ፎቶ ሽልማት የዚህ ዓመት አሽናፊ ሆነ፡፡ ሙሉጌታ ያሸንፈው በመካነ…

ኢትዮጵያዊው የፎቶ ግራፍ ባለሙያ ሙሉጌታ አየነ አለምአቀፍ ሽልማት አሸነፈ
ኢትዮጵያዊው የፎቶ ግራፍ ባለሙያ ሙሉጌታ አየለ  በየአመቱ በሚያዘጋጀው አለም አቀፍ ፕሬስ ፎቶ ሽልማት የዚህ ዓመት አሽናፊ ሆነ፡፡ ሙሉጌታ ያሸንፈው በመካነ ዜና ዘርፍ ሲሆን ያሸነፈበት ፎቶ ግራፍ ደግሞ የኢትዮጲያ አየር መንገድ አውሮፕላን የበረራ ቁጥር 302 በተከሰከሰበት ጊዜ የተጎጂዎች ቤተሰቦች በሰዓቱ የተሰማቸውን ስሜት የሚያሳይ ነው።[caption id="attachment_1826" align="alignnone" width="523"] ሙሉጌታ አየነ ያሽነፈበት ምስል[/caption]ለ63ተኛ ጊዜ የተካሄደው የአለም ፕረስ ፎቶ ሽልማት ላይ ከአለም የተውጣጡ በርካታ ባለሙያዎች የተሳትፉበት ሲሆን በመካነ ዜና ዘርፍ ለመጨረሻ ዙር የተመረጡት አራቱ እጩዎች ካንድ ወር በፊት የታውቁ ሲሆን በዚህ ሳምንት ደግሞ የአሶሼትድ ፕሬሱ ሙሉጌታ አየነ አሸናፊ መሆኑ ታውቋል፡፡ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መርሃ ግብር እንዳልተካሄደ እና ሙሉጌታም መገኘት እንዳልቻለ ታውቋል፡፡ ከሽልማቱ በተጨማሪ ያገኘው እውቅና ጥሩ የስራ እድሎችን እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ የስዕል አውደ ርዕዮች ላይ ስራዎቹ እንዲታዩለት እድል እንደፈጠረለት ይናገራል። እስካሁንም አፍሪካ ውስጥ ይህንን ውድድር በማሽነፍ ሙሉጌታ ሁለተኛው ሰው ነው።በደስታ ፎር አፍሪካን በሚዘጋጀው የፎቶ ፊቲቫል ላይ ለሚሳተፉ ስልጠናዎችን በመስጠት በሙያው ብቁ ባለሙያዎችን በማፍራት አስተዋፅዖ እያበረከተ የሚገኘው ሙሉጌታ በአፍሪካ ውስጥ ላሉ ጀማሪ በፎቶ ጋዜጠኝነት ለሚሳተፉ የሱ መሸለም ሞራል እንድሚሆናቸው እና ሙያውን ወደው ለሚሰሩ ጋዜጤኞች ደግሞ ያለውን እውቀት ባገኘው አጋጣሚ እንደሚያካፍላቸው ለአዲስ ዘይቤ ተናግሯል።የፎቶ ግራፍ ባለሙያዋ ማህደረ ኃይለሥላሴ በዚህ ትልቅ ሽልማት ላይ ሙሉጌታ በማሸነፉ በአፍሪካ ውስጥ ለሚገኙ ባለሙያዎች ትልቅ መነሳሳትን እንደሚፈጥር ገልፃ ለውድድር የቀረበው ፎቶ ደግሞ የኢትዮጵያ አውሮፕላን በመከስከሱ ምክንያት ተፈጥሮ የነበረውን ሃዘን በደንብ የሚገልፅ በመሆኑ ለታሪክ ማስታወሻ የሚቀመጥ ነው ብላለች።እንደ አውሮጳዊያን አቆጣጠር በ1956 ከአስራ አንድ ሀገራት የተውጣጡ 42 የፎቶግራፍ ባለሙያዎችን በማቅረብ የጀመረው የወርልድ ፕረስ ፎቶ ሽልማት መቀመጫው ኔዘርላንድ ያደረገ ሲሆን መካነ ዜና፣ አጠቃላይ ዜናዎች፣ ሰዎችን፣ ዘመናዊ ሃሳቦችን ያዘሉ፣ የቀን ተቀን ውሎን እና ተፈጥሮን የሚያሳዩ ፎቶዎች ባለሙያዎቹ የሚወዳደሩባቸው ዘርፎች ናቸው።[caption id="attachment_1825" align="alignleft" width="171"] ሙሉጌታ አየነ[/caption]በመካነ ዜና ዘርፍ የዛሬ ዓመት አሜሪካዊው ጆን ሞሬ አንድ ህፃን ልጅ መንገድ ዳር ላይ ቁማ ስታልቅስ በሚያሳይ ፎቶ አሸናፊ የነበረ ሲሆን እ.ኤ.አ በ2018 ደግሞ ቬኑዝዌላዊው ጁዋን ባሬቶ ሰዎች በአመፅ ውስጥ እሳት እያጠፉ በሚያሳይ ፎቶ አሸናፊ ነበር።ሙሉጌታ አየነ ከዚህ በፊት በ2013 ኢንዲያን አፍሪካን ፎቶ አዋርድ እና ሌሎች ያገኛቸው ሽልማቶች እና እውቅናዎች የሞራል ስንቅ እንደሆኑትና ጠንክሮ በመስራቱ ለዚህ ሽልማት እንደበቃ ለአዲስ ዘይቤ ተናግሯል።

አስተያየት