You can paste your entire post in here, and yes it can get really really long.
ሶስት ልጆች አሏት።ሁለቱ ለአቅመ ተማሪ ቤት ደርሰዋል።ስምንት እና አምስት አመት እድሜ ያላቸው ሲሆን ሁሉ ነገሯ ናቸው ልጆችዋ።ወይዘሮ ሕይወት አያሌው(ስሟ ለዚህ ፅሁፍ ሲባል የተቀየረ)መኖሪያዋን ሃያት የጋራ መኖሪያ ቤቶች መንደር ነው።በጥቅምት ወር ባንዱ ቀዝቃዛ ማለዳ ከመገናኛ ሃያ ሁለት ታክሲ ጥበቃ ረዥም ሰልፍ ላይ ትገኛለች።ከአያት ኮንደምንየም መገናኛ ለመድረስ ሁለት ሰዓታትን ፈጅቶባት ነው የደረሰቸው።ልጅዎችዋን ሰዐሊተ ምህረት አካባቢ የሚገኝ ትምህርት ቤት ለማድረስ አስቀድማ ንጋት አስራ አንድ ሰዓት ከጣፋጭ እንቅልፏ ነቅታ ተማሪ ልጆቿን ቀስቅሳ ለትምህረት ቤት ማሰናዳት እና መንገድ በተሸከርካሪዎች ተሞልቶ ሳይጨናነቅ ማድረስ አለባት።እነዚያን የምትሳሳላቸውን ህፃናት ልጆችዋን ጀምበር ሳትወጣ ከእንቅልፋቸው መቀስቀስ ጋር ፈተናው እንደሚጀምር ትገልፃለች።ይህ የዕለት ተዕለት ተግባሯ ነው። የህይወቷ ጉዞ ላይ አድካሚው ድግግሞሽም እ ንደሆነ ትገልፃለች።አዲስ አበባ አሁን ምን አይነት የትራፊክ ፍሰት ያላት ከተማ ናት?በሙያቸው አርክቴክት ናቸው። ማህደር ገብረመድህን በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ላይ “ከቤት እስከ ከተማ” በሚል የፕሮግራም ስያሜ በአርክቴክቸር፣በምህንድስና፣በግንባታ እና የከተማ አኗኗር ላይ የሚያተኩር የሬዲዮ ፕሮግራምን ያሰናዳሉ።በከተማ ፕላኖች፣በግንባታ ንድፈ ሃሳቦች እና ከተማዋ የመንገድ እና ትራፊክ ሰፊ ፕሮግራሞች በተደጋጋሚ በሬዲዮ የሚያቀርቡም ባለሞያ ናቸው።ከአዲስ ዘይቤም ጋር ቆይታ አድርገው ነበር። ስለከተማው የተሸካርካሪ እና እግረኛ ፍሰት ችግሮች ገና ያልተረዳነው እና አሁን ከሚስተዋልበት መጥፎ ሁኔታ ሊባባስ እንደሚችል ይጠቁማሉ።በአዲስ አበባ ያሉ መንገዶች ንድፍ ምን አሉታዊ እና አዎንታዊ ጎኖች አሏቸው?ወ/ሮ ህይወት ምንም እንኳን ነገሮች በትራንስፖርት አገልግሎቱ አስመራሪነት እጅ ባትሰጥም አሰልቺ እና በመንገዶች ጥበት የተነሳ የጎዳናዎች መዘጋጋት ድግግሞሹ መች እንደሚያበቃ እና እርስዋም ልጆችዋም እፎይ የሚሉበትን ቀናት ትጠብቃለች። “የትራንስፖርት እጦቱ እና የመንገዱ ጠዋት እና ምሽት ላይ መዘጋጋት መቼም የሚያበቃ ጉድ አይመስልም።ያለ አንዳች ስራ ታክሲ ውስጥ ለአንድ ጉዞ ብቻ ለሁለት ሰዓት ለዚያውም በየቀኑ መቀመጥ አሰልቺ እና ጊዜን አባካኝ ነው።” ትላለች“መንገዶች በአብዛኛው ጥሩ ሊባሉ የሚችሉ ንድፎች ይወጣላቸውና ትግበራው ላይ ግን ችግሮችን እናስተውላለን፤ለምሳሌ የእግረኛው መንገድ ሳይጠናቀቅ መንገዶች ለአገልግሎት ክፍት ይሆኑ እና እግረኛው በሙሉ ዋናውን መንገድ እንዲጠቀም ይገደዳል።የእግረኛ መንገድ በአግባቡ ያልተሰራለት መንገድ ደግሞ አንደኛውን Highway ነው መሆን ያለበት።የከተማ መንገድ ነው ከተሰኘ ግን አስቀድሞ ስለ እግረኛው መንገድ አጥብቆ ተጨንቆ ሊሰራ እና በአግባቡ ማጠናቀቅ አስፈላጊ ሲሆን በተጨማሪም በቂ የእግረኛ መተላለፊያ እና በቂ ስፋት ያለው የእግረኛ መንገድ ሊኖረው ይገባል።” የሚሉት ማህደር ገብረመድህን (አርክቴክት)በዚሁ አያይዘው ሲገልፁ ከአራት ሳምንታት በፊት ከቤት እስከ ከተማ የሬድዮ ፕሮግራም ላይ ሰፋ ያለ ጥናት የተደረገበት እና የአዲሰ አበባ የተወሰኑ ጎዳናዎችን እንደ ምሳሌ የወሰደ ፕሮግራም አቅርበው እንደነበረ ገልፀው ለምሳሌም ከመስቀል አደባባይ እስከ አምባሳደር ያለው መንገድ የእግረኛ ማቋረጫዎቹ ምቹ አለመሆን መንገደኞች በየመኪኖቹ ስር እየተሸሎኮለኩ መንገድ እንዲያቋርጡ ያደርጋቸዋል ብለዋል።”ከተማዋንም የተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ቦታዎች እና የአረንጓዴ መዝናኛ ስፍራዎች አግባብ የሌለው ስርጭት እና እነኚህን መሰረታዊ ነገሮች ችላ ያለ ነው።” ብለዋል።የአዲስ አበባ የትራፊክ ፍሰት ችግሮች እንዴት ያሉ ናቸው?አቶ አሸናፊ ሃይሌ ደግሞ አዲስ አበባ ተወልደው ያደጉ ባህር ማዶ ተሻግረው ትምህርት ቀስመው የተመለሱ እና በአሁኑ ሰዓት በግብረ ሰናይ ድርጅት ውሰጥ የፕሮግራም ሃላፊ ሲሆኑ የቤተሰብ ሃላፊ ናቸው።የከተማዋ የተሸከርካሪ ቁጥር መብዛት እና የመንገዶች መጨናነቅ የከተማዋን የአለም አቀፍ ገፅታ ሊያጎድፍ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።የግል ተሸከርካሪ ያላቸው እና ሰሚት ሳፋሪ የተሰኘ ሰፈር ነዋሪ ናቸው።በተለያየ ምክንያት መኪናቸው እክል ሲገጥመው ደግሞ በተደጋጋሚ የራይድ የከተማ ኮንትራት ታክሲዎችን፣መደበኛውን የታክሲ አገልግሎት እና አልፎ አልፎ ደግሞ ባቡርም ይጠቀማሉ። “በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓታት ያለው የተጨናነቀ የከተማዋ የትራፊክ ፍሰት አስቀያሚ ነው።የተሸከርካሪዎች እና የመንገዶች ስፋት አልተመጣጠነም።በጣም በማለዳ ወጥቼ እንኳን ከአንድ ሰአት ተኩል በላይ ያለ ምንም ፋይዳ በመንገድ መዘጋጋት ምክንያት ወደ ስራ ቦታዬ ስሄድ እቆያለሁ።አንዳንድ ግዜም በስራ መግቢያዬ ሰዓት አልደርስም።አረፍዳለሁ።”ይላሉ።አዲስ አበባ ውስጥ አምስት መቶ ሃ ስድስት ሺህ በላይ መኪኖች እንዳሉ የጠቆሙት ማህደር ገብረመድህን (አርክቴክት)ከተማዋ ሁሉን ያዋሃደ አይነተኛ የከተማ ፕላን እንደሚያስፈልጋት ጠቅሰዋል። “ለምሳሌ በከተማዋ የሆነ ክፍል ኮንደምንየም ይሰራል እንበል መንገድም ይገነባል ኮንደሚንየሙ ወይም የመኖሪያው ስፍራው አያይዞ የሚጠይቀውን አለያም የሚያስፈልገውን ያህል የትራፊክ ፍሰትን ሊያስተናግድ ብሎም ወደፊት ለሚኖረው ተጨማሪ የተሽከርካሪዎች መጠን እና ፍሰትን ያጣጣመ ሊሆን ይገባዋል።” በማለት አሁን ያለው ተጨማሪ ችግር ይህ መሆኑን ጠቁመዋል።ተማሪው እና ሠራተኛው በተመሳሳይ ሰአት እንደሚወጣ፣የቤት አውቶሞቢል አሽከርካሪዎች፣ከባድ መኪኖችንም በቂ ቁጥጥር ስለማይደረግ በስራ መግቢያና መውጫ ሰዓት መውጣት፣መንገድ ዳር መኪናን ማቆም፣ዋና ጎዳናዎች ዳር የትምህርት ቤቶች መኖር፣ቀላል እና ከባድ የትራፊክ አደጋዎች እና ግጭቶች በስራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓቶች ሲከሰቱ ትራፊክ ፖሊሶች በፍጥነት ቦታው ደርሰው ግጭቱን መርመረው መንገዱን ማስከፈት አለመቻል፣የባቡር መንገድን ለማቋረጥ የተዘጋጁት የእግረኛ መሻገሪያዎች በሰዎች መሞላታቸው እና ታክሲዎች እና አውቶብሶች እዛው መንገዶች ዳር ተሳፋሪዎችን መጫን እና ማውረድን እንደ መንገድ ማጨናነቅ እና የትራፊክ አደጋዎች መንስኤነት በምሬት የጠቀሱት አቶ አሸናፊ “እነኚህ ችግሮች ደግሞ ለእኔ የኢኮኖሚያዊ ጉዳት አለው ምክንያቱም እኔ ቦሌ ስራ ቦታዬ በዘጠኝ ብር መድረስ እየቻልኩ መንገዱ ዝግ በመሆኑ የተነሳ ሌላ ውድ አማራጮችን እንድጠቀም ያስገድዱኛል።ስራ ገበታ ላይ በሰአት ባለመገኘት እና በማርፈድ በተደጋጋሚ ግምገማ ተደርጎብኛል ምን አልባትም ስራዬንም ሊያሳጣኝም ይችል ይሆናል።ሌላው ደግሞ እነዚህን ረጃጅም የታክሲ ሰልፎች ሲሆኑ ስራ ከመድረስህ በፊት ያሉ ከባድ ስራዎች ናቸው።ስራ ቦታዬም ስደርስ ከፍተኛ የድካም ስሜት እየተሰማኝ ስለምደርስ ስራ በአግባቡ አልሰራም እናም ስራን ያጓትታል።” ሲሉ ምሬታቸውን በጥቅሉ ገልፀዋል።ሞላ(ለዚህ ፅሁፍ ሲባል ስሙ የተለወጠ)የሰላሳ ሰባት አመት የመደበኛ አስራ ሁለት ሰው መጫን አቅም ያለው ታክሲ ከስምንት አመታት በላይ ያሽከረከረ ነው።የአዲስ አበባ መንገዶች በመኪኖች መሞላቱ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ እየገለፀ ይሄንንም ካለፉ አመታት ጋር ሲያወዳድረው “ከአራት እና አምሰት አመታት በፊት ከስምንት እስከ አስር ቢያጆ በቀን ውስጥ ከላፍቶ ሜክሲኮ እንሰራ ነበር።አሁን ግን ከጎፋ መብራት ሃይል በቄራ አደርጎ እስከ ሜክሲኮ ያለው መንገድ እጅግ ጠባብ እና የመኪኖችን ብዛት ማስተናገድ የማይችል ነው።ሌሎች አማራጭ መንገዶችን ለመጠቀም እየሞከርን ቢሆንም ምንም የተሻለ መፍትሄ ሊሆን አልቻለም።ይህ ደግሞ የእለት ገቢያችንን እጅግ እየጎዳው ነው።”ይላል።ችግሮቹስ እንዴት ሊፈቱ እየተሞከረ ነው?መፍትሄዎች ምን ይሆኑ?በቅርቡ በከተማው የተገነቡ የአውቶቡስ መጠበቂያዎች አሰራር ፣በአዲስ አበባ ከተማ የስራ ሰዓት መግቢያ እና መውጫ ሰዓቶች ላይ የሚስተዋሉትን የትራፊክ መጨናነቆችን ለመቀነስ በትራንስፖርት ባለስልጣን በተደረጉ ስራዎች የጎዳናዎችን ጠርዞች በመቁረጥ ለማስፋት መሞከር፣አደባባይ አፍርሶ በትራፊክ መብራት መቀየር፣ ትላልቅ መንገዶችን እንደ ማስታገሻ ለመጠቀም ከከተማ እንዲያስወጡ መገንባት፣የነበሩ ጠባብ የከተማዋን መንገዶች የማስፋፋት ስራዎች እና የተለያዩ ጥቅም የሚሰጡ ምልክቶችን እና መስመሮችን ማበጀት የመሳሰሉ ተግባራት ያመጡት ወይም የሚያመጡት መፈትሄዎች እንደማይታዩቸው የሚገልፁት አቶ አሸናፊ አደባባዮችን አፍርሶ በትራፊክ መቆጣጠርያ መብራት መቀየር፤ ምልክት ሰጪ መብራቶችን አስፋልት ላይ መግጠም፤ የከተማዋን ጠባብ መንገዶችን ከእግረኛ መንገድ በመቀነስ የማስፋት ስራ እና የመንገድ ጠርዞችን በማፍረስ ዋና ጎዳናዎችን ለማስፋት የተሰሩት ስራዎች እነዚህ የአዲስ አበባ የትራንሰፖርት ፍሰት እንከኖችን ሊያስቀሩት እንዳልቻሉ እና እንደ ቀጠሮ አለማክበርን፣ልጅ ማጫወቻ ሰዓትን ማሳጣት እና ከቤተሰብ አባላት ጋር በቂ ግዜ እንዳይኖር ይወስናል የሚለት አቶ አሸናፊ በጀርመን ሃገር በትምህርት ላይ ቆይታቸው ያስተዋሉትን አንዳንድ መፍትሄዎች እንዲህ ይጠቁማሉ።”የከተማዋ ነዋሪዎች ለስራ የሚገቡበት እና የሚወጡበት ሰዓቶች ላይ የባቡር ፉርጎዎችን መጨመር፣ልክ ጀርመን ሃገር እንዳለው ልማድ የቱንም ያህል ተሳፋሪ ቢኖር በየሰላሳ ሰከንድ ወይም በተወሰኑ ደቂቃዎች ድግግሞሽ ባቡሮቹ ስለሚመጡ ብዙ ግዜን በጥበቃ ሰው እንዳያሳልፍ ያደርገዋል።እዚህም ያንን ብልሃት ብንሞክረው መልካም ነው።ይህ የሚደረግ ከሆነ ደግሞ የግል መኪና ያለው ሰው እንኳን የነዳጅ ወጪን ለመቆጠብ መኪናውን በመተው ባቡሮችን እንዲጠቀም ያደርገዋል።እዚህ የሚስተዋሉት ባቡሮች ፉርጎዎች ባለ አንድ ወይም ሁለት ነው።ይሄ ደግሞ መፍትሄ አይሆንም።የበለጠ ቢሰራበት ሊሻሻል ይችላል።”ማህደር ገብረመድህን(አርክቴክት) “አንድ ከተማ አንድ አይነት ቁጥጥር እና ምዘናን የሚያደርግ እና ያልተበታተኑ አሰራሮችን የሚተገብር፣ ኃላፊነቶች እና ውሳኔ ሰጪነት ከፖለቲካ አንፃር ሳይሆን ከሞያ አንፃር የሆኑ አሰራሮችን ልማድ ያደረገ አሰራር ሊኖረን ይገባል።” ይላል።ይህም ጉዳይ ቸል ስለተባለ እና ፖለቲካዊ እና ሞያዊ አተያዮች ሰፊ ልዩነት ያላቸው፤ የቁጥጥር እና የውሳኔ እና የግንባታ ስራዎች በተለያዩ መስሪያ ቤቶች የሚሰጡ ስለሆኑ ከተማ መሰረተ ልማቶች የንድፍ፣የግንባታ እና ሌሎች ጥፋቶች በሚፈጠር ግዜ እያወቁ መፍትሄ ሊያበጁ አይችሉም።”ብሎ ያለውን ክፍተት ከአዲስ ዘይቤ ጋር ተወያይቶበታል።ይህን ችግርም ለመቅረፍ የተለያዩ አማራጮችን መጠቀምን እንደ መፍትሄ የሚያየው የታክሲ አሽከርካሪው ሞላ በበኩሉ የትራፊክ ፖሊሶች ቁጥርን መጨመር አንዱ መፍትሄ እንደሚሆን ይጠቁማል።የትራፊክ ፖሊሶችን ቁጥር መጨመር በየመንገዱ የሚፈጠሩ አነስተኛ የተሽከርካሪዎች ግጭቶች በሚፈጠሩ ሰዓት በፍጥነት ቦታ ላይ በመድረስ መንገዶች ወዲያውኑ አንዲከፈቱ ያደርጋል በሚለው አመኔታው ሲሆን የመንገደኞች ማቋረጫ መንገዶች በድልድይ እንደተሰሩ ሁሉ ብዛታቸው ቢጨመር መልካም መሆኑን ይገልፃል።