ጥቅምት 28 ፣ 2011

በሃረማያ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ተቃውሞ እያቀረቡ ነው

ወቅታዊ ጉዳዮች

የሀረማያ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬ ጥቅምት28፣2011 ዓ.ም ከንጋት ጀምሮ በከተማዋ በሚገኝ እስታዲየም በመሰብሰብ ተቃውሟቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ የተለያዩ…

በሃረማያ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ተቃውሞ እያቀረቡ ነው
የሀረማያ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ዛሬ ጥቅምት28፣2011 ዓ.ም ከንጋት ጀምሮ በከተማዋ በሚገኝ እስታዲየም በመሰብሰብ ተቃውሟቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ የተለያዩ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ጥያቄዎችን ያነሱት ተማሪዎቹ ከማለዳ አንስቶ እስካሁን ድረስ የተቃውሞ ሰልፋቸውን ቀጥለዋል፡፡ "ኦነግ ለምን ትጥቅ ይፈታል? የኦነግ ባንዲራ በመላው ኦሮሚያ ክልል ከተሞች መውለብለብ አለበት እንዲሁም በምእራብ ወለጋ እና ሌሎች አካባቢዎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ ይቁም!" የሚሉ ጥያቄዎችን እያሰሙ ይገኛሉ፡፡የተፈጠረውን አለመረጋጋት ለማርገብ በአቅራቢያው የሚገኙ የፖሊስ ኃይሎች በቦታው ተገኝተው ጉዳዩንን እየተከታተሉት እንደሚገኙ አዲስ ዘይቤ ከቦታው ያገኛቸው መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ሀረማያ ዩንቨርሲቲ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ አለመረጋጋቶችና የተማሪዎች ተቃውሞ በስፋት ከሚስተዋሏባቸው ዩንቨርሲቲዎች አንዱ ሲሆን በሃገሪቱ የሚገኙ ሌሎችን ዩንቨርሲቲዎች በአሁን ሰአት ተማሪዎችን ተቀብለው ወደ ትምህትር መግባታቸው ይታወቃል፡፡

አስተያየት