ቴዲ በሚኖርባት ሸገር በስቱዲዮው ውስጥ ድንቅ ሙዚቃዎችን መቀመር እንጂ፤ ከአድናቂዎቹ ጋር በመድረክ መገናኘት እንደሰማይ ርቆበት ቆይቷል። በ2006 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል ካደረገው የሙዚቃ ዝግጅት በኋላ ዛሬ ጥቅምት 24 2011 በሚሊኒየም አዳራሽ የሚያቀርበው በአዲስ አበባ ከአምስት ዓመት ወዲህ የመጀመሪያው መሆኑ ነው፡፡ባለፉት አምስት ዓመታት በርካታ ኮንሰርቶች ታቅደው፤ ማስታወቂያ ተነግሮላቸውና በርካታ ወጪ ወጥቶባቸው ሳይሳኩ ቀርተዋል፡፡አዘጋጆቹም ለከፍተኛ ኪሳራ ተዳርገዋል፡፡ከ2006 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ዓመታት በየዓመቱ ለአዲስ ዓመት ዋዜማ ሲታቀዱ የነበሩ ኮንሰርቶችና የአልበም ምረቃ ዝግጅቶች ፤ከመንግሥት በኩል “በከተማዋ ባሉ የመርሃ ግብር መደራረቦች የተነሳ ዝግጅቱን ማስተናገድ ከአቅማችን በላይ ነው፤ የዝግጅቱት ፈቃድ ጥያቄ በደብዳቤ በወቅቱ አልቀረበልንም “ በሚሉና በመሳሰሉት ከከተማው አስተዳደር በሚሰጡ ምክንያቶች ሲሰረዙ ቆይተዋል፡፡አዲስ ዘይቤ ያነጋገረቻቸው የድምፃዊው ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታቸው ማንጉዳይ ያለፉትን አምስት ዓመታት ሲያስታውሱ “በክልከላዎቹ ሁሉ በጣም በጣም እናዝን ነበር ፡፡አትዝፈን ነበር የተባለው፡፡ያ ደግሞ አሳፋሪ ነበር ፡፡ከልካዮቹም ጥቂት ሰዎች ነበሩ፡፡በተለይ የምናዝነው የሚፈልገውን እንዳያገኝ ይደረግ ለነበረው ሕዝብ ነበር” በማለት ሁኔታውን ያስታውሳሉ፡፡ከሁሉም በላይ ቴዲ በችግሩ ጊዜ ሁሉ ከጎኑ ሲቆም ለነበረው የአዲስ አበባ ሕዝብ ምስጋናውን ማቅረብ አለመቻሉ ያስቆጨው እንደነበርም ተናገረዋል፡፡አድናቂው መቅደምም ላለፉት ዓመታት በድምፃዊው ላይ ከመንግሥት በኩል ይደረጉ የነበሩትን ጫናዎችና ክልከላዎች ሲያስታውስ መንግስት ካለበት ሃላፊነት አንፃር በማይጠበቅ መልኩ ከአንድ ግለሰብ ጋር እልህ የተጋባ የሚመስል ሁኔታ እንደነበር ያስታውሳል፡፡ከዚህም በተጨማሪ “የፈለግኩትን ማድረግ እችላለሁ” ከሚል አስተሳሰብ የመነጨ የሚመስል ሕገወጥ ድርጊት የመንግሥት መዋቅርና አሰራርን በመጠቀም ይወሰን እንደነበር ይናገራል፡፡የቴዲ የመድረክ ዝግጅት ጫና ሲደርስበትና ሲስተጓጎል የነበረው የመንግሥትን መዋቅር በሚዘውሩ አካላት ብቻ ሳይሆን ቴዲ አፍሮ በዘፈኖቹ በሚያስተላልፋቸው መልእቶች የማይደሰቱት አንዳንድ ወገኖች ጭምርም እንደነበር አድናቂው መቅደም ይናገራል ፡፡ለዚህም በ2005 ዓም በሄንከን ኩባንያ ድጋፍ ሊካሄድ የነበረውና “ቦይኮት በደሌ” ወይም “እምቢ ለበደሌ” በሚል የበይነ መረብ ዘመቻ በድርጅቱ ላይ በተደረገ ጫና የተሰረዘውን የሙዚቃ ዝግጅት በምሳሌነት ይጠቅሳል፡፡በድምፃዊው ላይ ሲደረጉ የነበሩት ጫናዎች ጫፍ የደረሱበት ጊዜም ነበር፡፡ በነሃሴ 2009 ዓም ከአንድ ሺህ የማይበልጡ እንግዶች ተጠርተው “ኢትዮጵያ” የተሰኘ አልበም ሊያስመርቅ ሰዓታት ሲቀሩት ፤ዝግጅቱን የመንግሥት አካላት አስተጓጎሉበት፡፡ ይህም ጉዳይ በሃገር ውስጥ ብቻ ሳይወሰን አለም አቀፍ ወደመሆንም ሄደ፡፡ዋሸንግተን ፖስት “The world loves Ethiopian pop star Teddy Afro. His own government doesn’t.”በሚል ሲዘግብ የካናዳ የፓርላማ አባል የሆኑት አሌክስ ናዳል “የመንግስት እርምጃ የዜጎችን መሰረታዊ መብትን የሚጋፋ ነው፡፡” በማለት ለቀድሞው ፕሬዝዳንት ሙላቱ ተሾመ በፃፉት ደብዳቤ ድርጊቱን ተቃውመዋል፡፡በፎርቹን ጋዜጣ አምደኛ የሆኑት ግርማ ፈይሳ የአራዳ እይታ (View from Arada ) በሚል አምዳቸው ሥር እገዳውን በተመለከተ መንግስት ቴዲን እንዲያውም ሊያመሰግውና ሊሸልመው እንደሚገባ ትዝብታቸውን እንደሚከተለው አስፍረው ነበር፡፡“The album, which is the result of a single creative talent, ought to have been awarded at least words of encouragement by the government. Its message is about nothing but cohesion and dynamism for the country.”መዝፈን ብቻ አይበቃምበእያንዳንዱ የሙዚቃ አልበምና የመድረክ የሙዚቃ ዝግጅት ውዝግብ አጥቶት የማያውቀው ቴዲ በሚቀርብባቸው መድረኮች ሁሉ ለሚገጥሙት ጉዳዮች ቀጥተኛ መልስ ሰጥቶ አያውቅም፡፡ደጋግሞ ሲናገር ከአፉ የሚወጣው ቃል “ፍቅር ያሸንፋል” የሚል ነው ፡፡ኢትዮጵያ የሚለው አልበም ምረቃ ዝግጅት ከታገደ በኃላ ለጋዜጠኞች በሰጠው ቃለ ምልልስ በተለይም ከ”Ethio newsflash” ድረ-ገጽ ጋር ባደረገው ቆይታ ሲናገር ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ማንም ሰው ከፖለቲካ ውጪ መሆን እንደማይችል፤ ፖለቲካዊ ጉዳይ ማነሳትም እንደኩነኔ መታየት እንደሌለበትና ፤በሃሳብ ከመደራጀት ይልቅ በዘር መደራጀት ብዙ ዓመት የተደከመበት ኢትዮጵያዊነት ላይ የፈጠረው አደጋ መኖሩንና ኢትዮጵያዊነትን ማዳን እንደሚያስፈልግ በግልጽ ሲናገር ብዙዎች ቴዲ “መዝፈን ብቻ አይበቃም መናገርም ያሻል” የሚል አቋም ይዟል የሚል እምነታቸውን አንፀባርቀዋል፡፡መቅደም ቴዲ በአስቸጋሪና ፈታኝ ጊዜያቶች ሁሉ በዝምታ ማለፉና በብዙ ጉዳዮች ላይ ቁጥብ መሆኑን እንደሚያደንቅለት ይናገራል፡፡ “የፖለቲካ አቋሙን ከሙዚቃው ባለፈም በንግግርም መግለጹ በሱ የባህሪይ ለውጥ የመጣ ሳይሆን በሁለት ገፊ ምክንያቶች ነው።” በማለት ይከራከራል፡፡ ኢትዮጵያ የተሰኘው አልበም በአለም አቀፍ ደረጃ ያስመዘገበው ደረጃ አለም አቀፍ ሚዲያዎች ለድምፃዊው የተለየ ትኩረት እንዲሰጡ ማድረጉና ሃገሪቷ የነበረችበት ሁኔታ ለሁላችንም አሳሳቢ ስለነበር በወቅቱ እሱም እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ መናገር የነበረበትን ነገሮች እንደተናገረ ያምናል።በመጨረሻም ቅዳሜ ሆነ!ለብዙ ድምጻውያን አልበም ማሳተም የረጅም ዓመታት ምጥ ነው፡፡አልበሙ ከወጣ በኃላ ግን ኮንሰርት ብዙም የሚያሳስባቸው ጉዳይ አይደለም፡፡ለቴዲ አፍሮ ግን ተገላቢጦሽ ነው ፡፡ ኮንሰርት ለእሱ ብቻ ሳይሆን ለአዘጋጆቹም ለአድናቂዎቹም ጭንቅ ነው፡፡ ላለፉት ዓመታት የሆነውም ይሄ ነው ፡፡በእገዳዎች ክልከላዎችና በእምቢታ ዘመቻዎች አልፎ እነሆ በመጨረሻም « ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር » በሚል ርዕስ የተሰየመው ኮንሰርት ዛሬ ጥቅምት 24 2011 በመዲናችን አዲሰ አበባ እውን ሊሆን ነው፡፡ይህን ቀን ቴዲና አደናቂዎቹ ለአምስት ዓመታት ጠብቀዋል፡፡መቅደም ኮንሰርቱን በጉጉት ከሚጠብቁት አድናቂዎች አንዱ ነው፡፡ “Can’t wait to see him “ ይላል፡፡ ለኮንሰርቱ ያለው ጉጉትም በግል ቴዲ አፍሮን መድረክ ላይ በማየት ከሚያገኘው ደስታ የዘለለ ዓላማ እንዳለው ያምናል፡፡ ሃገራችን አሁን ያለችበት ሁኔታ የኢትዮጵያዊነት ስሜት ከመቼውም ጊዜ በላይ የሚያስፈልግበትና ቴዲ አፍሮም ቀኑን ከዚህ ቀደም እንዳደረገው ኢትዮጵያዊነት የሚያታወስበት ቀን ይሆናል በሚል ተስፋ እንዳለው ይናገራል፡፡ከአዲስ አበባው ኮንሰርት በኋላ በቀጣይ በሌሎች ከተሞች ዝግጅት ታስቦ እንደሆን የተጠየቁት አቶ ጌታቸው “ አዎ እንሄዳለን፡፡ የትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ሃገራችን ነው “ በማለት መልስ ሰጥተዋል፡፡ኮንሰርቱ ዛሬ ከብዙ ዉጣ ውረድ በኃላ መሳካቱንና የታለፈውን ውጣ ውረድ በማስታወስም ሁሉ ነገር አላፊ ነው ይላሉ፡፡አዎ ሁሉ ነገር አላፊ ነው፡፡ብዙ መከራ ታልፎ ዛሬ ሸገር የለውጥ አየር ሽው ብሎባታል፡፡ በዝሆን ጠብ የተሰበረው ድልድይ የተጠገነ፤የተረገጠው ሳርም ቀና ይል ዘንድ እግዜሩ ያየው መስሏል፡፡ ለዓመታት በመለየት ስቃይ የተንገላቱ ነፍሶችም እረፍት አግኝተዋል። መንገዱም በፍቅር ተቃኝቷልና ማን ያውቃል እነፊዮሪና ቅዳሜ ሸገርን ያደምቋት ይሆናል፡፡