You can paste your entire post in here, and yes it can get really really long.
በአዲሱ የመንግስት አደረጃጀት መሰረት የተቋቋመው የጠቅላይ ሚኒስትር ፕሬስ ሴክሬታሪያት በሚል ከዚህ ቀደም የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤትን ኃላፊነት ተረክቦ እንደሚሰራና ሌሎች አዳዲስ ሹመቶችም መደረጋቸውን ዛሬ ጥቅምት 26፣ 2011 ዓ.ም በተሰጠው መግለጫ ተገልጧል፡፡ላለፉት ሰባት ወራት የጠቅላይ ሚኒስትሩን የየዕለት እንቅስቃሴ በማኀበራዊ ሚዲያ ላይ መረጃ በመስጠት ሲያገለግሉ የጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ የኦዴፓ ስራ አስፈጻሚ አባል በሆኑት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተተክተዋል፡፡ አቶ ፍፁም ወደ ቀድሞ መስሪያ ቤታቸው የኢቨስትመነት ኮሚሽን ተመልሰዋል፡፡በጠቅላይ ሚኒስተር ፅ/ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም አገላለፅ ጽ/ቤታቸው ‹‹ወቅታዊ፤ ግልፅና ትክክለኛ መረጃዎችን ለመገናኛ ብዙሃን መስጠት ፡ በመንግስት አሰራር ላይ ከህዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ግብረ መልስ መስጠትና በሚዲያ ተቋማትና በጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር ዋነኛ ዓላማው ነው›› ብለዋል፡፡የፕሬስ ሴክሬታሪያቱ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጠው መግለጫ በሚንስትሮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ የፀደቀውን የመንግስት አዲስ የእቅድ ሰሌዳ (Dashboard planning ) ‹‹ኢትዮጵያ፡ - አዲስቷ የተስፋ አድማስ›› በሚል መርህ የተዋቀረ 11 ነጥቦችን የያዘ ባለአንድ ገፅ የእቅድ ሰሌዳ ይፋ አድርጓል፡፡ እስከ 2012 ዓ.ም የሚተገበረው ይህ የእቅድ ሰሌዳ በሁለት ወሳኝ ማዕቀፎች ስር ስለ ዴሞክራሲና የህግ የበላይነት እንዲሁም የስራ ፈጠራ ተወዳዳሪነት ላይ ትኩተር እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡የሴክሬታሪያቱ ኃላፊነትና የስራ ድርሻ ግልፅ አለመሆን በተጨማሪም ጠ/ሚንስትሩ በምን ያህል ጊዜ ከጋዜጠኞች ጋር እንደሚገናኙ እና የመሳሰሉት ጥያቄዎች በሴክሪታርያቱ ስላልተወሰነባቸው ኃላፊዋ አጥጋቢ መልስ እንዳይሰጡ ሲያግዳቸው ተስተዉሏል፡፡