ጥቅምት 24 ፣ 2011

የራይድ እና የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ውዝግብ

ወቅታዊ ጉዳዮች

የአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን በትራንስፖርት መጥሪያ መተግበሪያ (application) ዘርፍ እውቅና የተሰጠው ሃይብሪድ ዲዛይንስ (ራይድ)…

የራይድ እና የመንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ውዝግብ
 የአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን በትራንስፖርት መጥሪያ መተግበሪያ  (application) ዘርፍ እውቅና የተሰጠው ሃይብሪድ ዲዛይንስ (ራይድ) የተሰኘው ድርጅት እውቅና ከተሰጠው ውጪ በህገወጥ መልኩ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ሲል ድርጅቱን እገዳ ጥሎበታል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በትናንትና እለት አርብ ጥቅምት 23፣ 2011 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል መግለጫ የሰጠው ራይድ፤ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የጣለብኝ እገዳ መሰረት አልባ ነው ብሏል፡፡ራይድ ወደ 900 የሚደርሱ ኮድ 3 እንዲሁም 200 ባለ ኮድ 1 ተሸከርካሪወችን ለትራንስፖርት በማሰማራቱ ነው እንግዲህ እገዳው የተጣለበት፡፡ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቃለ ምልልሳቸውን ያደረጉት የባለስልጣን መስርያ ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ዳዊት ዘለቀ በማብራሪያቸው ራይድ በሃገሪቱ ህግ በግልጽ የተቀመጠውን እና ባለ 3 ኮድ ተሸከርካሪዎች የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እንደማይሰጡ የሚደነግገውን ህግ ተላልፏል ነው ያሉት፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ድርጅቱ የንግድ እውቅና ያገኘው የትራንስፖርት መጥሪያ አፕሊኬሽን በማበልጸግ ሲሆን ተሸከርካሪዎችን ማሰማራት ህገ ወጥና ድርጊቱም የባለስልጣን መስርያ ቤቱ የስራ ሃላፊነት እንደሆነ አክለው ገልጸዋል፡፡ውዝግቡን ተከትሎም አዲስ ዘይቤ ያናገራቸው የራይድ ታክሲ አሽከርካሪዎች በተለመደው ስራቸው ላይ እንዳሉ ማወቅ ተችሏል፡፡ ባለስልጣን መስርያ ቤቱም ራይድ በህግ የሚጠየቅ መሆኑን በአጽንኦት ገልጻል፡፡ራይድ የትራንስፖርት መጥሪያ መተግበሪያ በማበልጸግ የመጀመሪያውን ድርሻ የሚወስድ ድርጅት ሲሆን ተጠቃሚዎች በሚፈልጉበት ቦታ ሆነው ወደ 8294 በመወደወል አግልግሎቱን እንዲያገኙ ያስችላል፡፡ በአለማችን በዚሁ ዘርፍ ቀዳሚነትን የሚወስደውና በ445 ከተሞች እንዲሁም በ70 ከተሞች የትራንስፖርት መጥሪያ መተግበሪያ አገልግት ሰጪው ኡበር ሲሆን ከተመሰረተ በአጭን ጊዜ ውስጥ አለም አቀፍ እውቅናን አግኝቷል፡፡ 

አስተያየት