You can paste your entire post in here, and yes it can get really really long.
አዲሱ ሁሉን አቀፍ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አዋጅ ቀጣይነት ያለው፣ ተደራሽ እና ሁሉንም ዜጎች ያቀፈ የጤና መድህን ለመስጠት ታስቦ የተቀረጸ ነው፡፡እንደ ጤና ጥበቃ ሚኒሰቴር ገለጻ አዋጁ በሙከራ ወቅት ውጤታማ በመሆኑ በፌደራልና በክልል ደረጃ መቀጠል እንዳለበት ታምኖበታል፡፡በዚህም ከአባላት መዋጮ ከየክልሉ እና ከፌደራል እንዲሁም ከሌሎችም ድጋፍ ሰጪ አካላት በሚደረግ አጠቃላይ ድጎማ ለተጠቃሚዎች ተደራሽነት ያለው የጤና አገልግት ይሰጣል ተብሏል፡፡የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ሉሉ አለባቸው አዋጁን አስመልክተው ”የዜጎች የመክፈል አቅም በደንብ መጠናት አለበት፡፡ መንግስት አብላጫውን ድጎማ የሚሸፍን ከሆነ ደግሞ ዘላቂነቱ አጠራጣሪ ነው የሚሆነው ምክንያቱም ወጪውን መሸፈን ከባድ ነው የሚሆነው፡፡” ብለዋል፡፡በብሄራዊ ደረጃ የሚቋቋመው ምክር ቤት በሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር የሚመራ ሆኖ ከፌደራል፣ ከክልል እና ከሲቪክ ማህበራት እንዲሁም ከየክልሉ የተወከሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያካትታል፡፡ የምክር ቤቱ ዝርዝር አሰራርም በሚኒሰትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚወሰን ይሆናል፡፡በተመሳሳይ መልኩ በክልል ደረጃ የሚቋቋመው ምክር ቤት ከክልል ባለድርሻ አካላት የተውጣጡ አባላት እደሚያቅፍ ይጠበቃል፡፡በየአመቱ የሚከፈለው የጤና መድህን መዋጮ የህብተሰቡን የመክፈል አቅም፣ የከተማ እና የገጠር እንዲሁም የነዋሪዎችን ገቢ እርከን ያገናዘበ ይሆናል፡፡በመጨረሻም ሚኒሰቴር መስሪያ ቤቱ ያወጣውን አዋጅ ለህዝብ መነጋገሪያ መድረክ ክፍት እንደሚሆን ገልጾ ለሚመለከታቸው የህብተሰብ ክፍሎች ጥሪ አቅርቧል፡፡