ሐምሌ 10 ፣ 2012

የትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አሜሪካዊ ደራሲ መዓዛ መንግስቴ መጽሓፍ በዋሺንግተን ፖስት ሙገሳን አገኘ

ወቅታዊ ጉዳዮች

የዋሺንግተን ፖስት ጸሓፊ ላውራ ሴአይ በዛሬው እለት የመአዛ መንግስቴን ዘ ሻዶው ኪንግ The Shadow King የተሰኘውን መጽሓፍ በአድናቆት የሚገልጽ…

የትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አሜሪካዊ ደራሲ መዓዛ መንግስቴ መጽሓፍ በዋሺንግተን ፖስት ሙገሳን አገኘ
የዋሺንግተን ፖስት ጸሓፊ ላውራ ሴአይ በዛሬው እለት የመአዛ መንግስቴን ዘ ሻዶው ኪንግ The Shadow King የተሰኘውን መጽሓፍ በአድናቆት የሚገልጽ ጽሁፍ ይዛ ወታለች። መቼቱን በ1928 ዓም ያደረገው የመአዛ መጽሓፍ በአውዱ ልብ-ወለድ ሲሆን የታተመው በ2011 ዓ.ም ነበረ።ከሌሎች ልብ ወለድ መጽሓፎች በተለየ በተወራሪውም በወራሪውም በኩል የነበረውን ስሜትና ኩናቴ መዘገቡ መጽሓፉን ለየት ያደርገዋል ሲል ዘገባው አስነብቧል። የዋና ገጸ ባህሪዋ ሂሩትን ግላዊ ታሪክ፣ በሷና በቤተሰቧ ለጦርነቱ ስለተሰጠው አገራዊ ምላሽ፣ በጣሊያን ወታደሮች (በተለይም በአይሁድ  ጣሊያን ወታደሮች) ዘንድ ስለነበረው ስሜትና ስለ በአገራቸው መወረርና በህዝቡ ላይ በተጋረጠው የመገዛት አደጋ በአጼ ኋይለሥላሴ  ዘንድ የነበረው ሁናቴ በመጽሓፉ በአግባቡ መተረኩን የላውራ ጽሑፍ ይገልጻል።መዓዛ መንግስቴ በ1966 ዓም በአዲስ አበባ የተወለደች ሲሆን በተለያዩ ወቅቶች በናይጄርያ፣ በኬንያና በአሜሪካ ኖራለች። ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አሜሪካዊ ደራሲ፣ በ2004 የወጣው ቢኒዝ ዘ ላየንስ ጌዝ(Beneath the Lion's Gaze)የተሰኘው የመጀመርያ መጽሓፏ በጊዜው በዘጋርዲያን የአፍሪካ ምርጥ 10 ወቅታዊ መጽሓፍት ዝርዝር ውስጥ መካተቱ ይታወሳል። በተጨማሪም መጽሓፍ ፈረንሳይኛን፣ ጀርመንኛን እንዲሁም ጣልያንኛን ጨምሮ ወደ ሰባት ቋንቋዎች መተርጎሙ ልዮ ያደርገዋል። 

አስተያየት