ሰኔ 19 ፣ 2012

የአፍሪካ የበሸታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው

ዜናዎችኹነቶች

በቅርቡ አለምን እያነጋገረ ያለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ እያስመዘገበ ከሚገኘው ጉዳት በተጨማሪ፣ አገራት የህክምና ስርአታቸውን አቅምና ዝግጁነት ላይ…

የአፍሪካ የበሸታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው
በቅርቡ አለምን እያነጋገረ ያለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ እያስመዘገበ ከሚገኘው ጉዳት በተጨማሪ፣ አገራት የህክምና ስርአታቸውን አቅምና ዝግጁነት ላይ የግምገማ ስራን እንዲሰሩ አስገድዷል። ይህንንም ተከትሎ የአፍሪካ ህብረት በመዲናችን አዲስ አበባ የአፍሪካ የበሸታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል ወይም (African Center For Disease Control and Prevention) የተሰኘ መጠርያ የያዘ ተቋም ለመመስረት ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ይገኛል። የማእከሉ ዋና መቀመጫ በአዲስ አበባ የሚሆን ሲሆን የማእከሉ ግንባታ በቅርቡ እንደሚጀመር ተገልጿል።ህብረቱ ባለፈው አመት ሰኔ 80 ቢልዮን ዶላር ይፈጃል ተብሎ ለሚጠበቀውን የማእከሉን ግንባታ እንዲሰራ ለቻይና መንግስት ስልጣን መስጠቱ ይታወሳል። በተጨማሪም የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ማእከሉ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለምታደርገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጸኦ እንደሚያደርግ አስረግጠው የገለጹ ሲሆን፣ አክለውም ቻይና አህጉሪቱ ቫይረሱን ለመከላከል ለምታደርገውን ያላሳለሰ ጥረት ለመደገፍ ዝግጁ መሆኗን በቅርቡ በተካሄደው የቻይና አፍሪካ ሰሚት ላይ ገልጸዋል። በተጨማሪም የማዕከሉ ግንባታ ቻይና በአፍሪካ ጋር ያላትን ጠንካራ ኤኮኖሚያዊ ተስስር ማሳያ ተደርጎ መወሰድ ይችላል ሲሉ ተናግረዋል። ቻይና ከዚህ ቀደም ሳር ቤት አካባቢ የሚገኘውን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽንን መገንባቷ ይታወሳል።ማእከሉ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ በኩል በሚገኝ መንደር በ90,000 ካሬ ሜትር ላይ የሚገነባ ሲሆን ህንጻው የሚያርፍበት ቦታ 40,000 ካሬ ሜትር እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። ማዕከሉ በውስጡ ላብራቶሪዎችን፣ ማሰልተኛ ማዕከሎችን፣ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን፣ ቢሮዎችን እንዲሁም መኖሪያ ቤቶችን እንደሚይዝ ይጠበቃል።ግንባታው ሲጠናቀቅ ማእከሉ ከአፍሪካ ህብረትንና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን ቀጥሎ በመዲናችን አዲስ አበባ የሚገኝ ሶስተኛ ህብረመንግስታዊ ተቋም ያደርገዋል። የማዓከሉ በአዲስ አበባ መገንባት ኢትዮጰያ በሃጉሪቱ የምትጫወተውን ሚና ወደአዲስ ምእራፍ ከማሻገሩም በላይ ለከተማዋ ተጨማሪ ድምቀት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

አስተያየት