ነሐሴ 25 ፣ 2012

ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በዛምቢያ ካቴቴ ቺቦሊያ ነዋሪዎች ጥቃት ደረሰባቸው

ወቅታዊ ጉዳዮች

በዛምቢያ ካቴቴ ወረዳ የቺቦሊያ ኮምፓውንድ ነዋሪዎች ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ አንድ ኢትዮጵያዊ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን ሌሎች ዘጠኝ ሰዎች ደግሞ በቅዱስ…

ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በዛምቢያ ካቴቴ ቺቦሊያ ነዋሪዎች ጥቃት ደረሰባቸው
በዛምቢያ ካቴቴ ወረዳ የቺቦሊያ ኮምፓውንድ ነዋሪዎች ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ አንድ ኢትዮጵያዊ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን ሌሎች ዘጠኝ ሰዎች ደግሞ በቅዱስ ፍራንሲስ ሚሽን ሆስፒታል ጉዳት ደርሶባቸው እየታከሙ እንደሚገኙ ዛምቢያ ሪፖርትስ የተሰኘ መካነ ድር ዘግቧል።እንደዘገባው ከሆነ ቅዳሜ ምሽት የኪቦልያ ነዋሪዎች 50 የሚሆኑ ሕገወጥ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የሚኖሩበት ቤት ገብተው ጥቃት ፈፅመዋል። የምሥራቅ ፖሊስ ኮሚሽነር ሉክሰን ሳካላ ተጠይቀው እንደተናገሩት ከሆነ ከሃምሳዎቹ ሰዎች አንዱ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን፣ ዘጠኝ ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ 38 የሚሆኑ ስደተኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ሁለት ሰዎች እንዳልተገኙም ገልፀዋል።የአካባቢው ነዋሪዎች ህገ ወጥ ስደተኞቹን በራሳቸው እጅ ከማጥቃትና ህግን ከመያዝ ይልቅ በቀላሉ ለባለስልጣናት ማሳወቅ ይችሉ ነበር በማለት ሳካላ ድርጊቱን አውግዘዋል። ፖሊስ አሁንም ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን አቶ ሳካላ አክለው ተናግረዋል። 50ዎቹ ኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ስደተኞች በዛምቢያ በኩል አድርገው ወደ ሳውዝ አፍሪካ ሊያቀኑ የነበረ ሲሆን በዛምቢያ ህገወጥ ካምፕ አዘጋጅተው እንደቆዩ ዘገባው ያመላክታል።

አስተያየት