ነሐሴ 25 ፣ 2012

ኢትዮጵያዊው ፓሌዮአንትሮፖሎጂስት ዶ/ር ዮሐንስ ኃይለስላሴ ከፍ ያለ እውቅናን አገኙ

ዜናዎች

ኢትዮጵያዊው ፓሌዮአንትሮዮሎጂስት ዶ/ር ዩሐንስ ኃይለስላሴ በኒው ሜክሲኮ ዩኒቨርስቲ ስር በሚገኘው ጆርናል ኦፍ አንትሮፖሎጂካል ሪሰርች (Journal of…

ኢትዮጵያዊው ፓሌዮአንትሮፖሎጂስት ዶ/ር ዮሐንስ ኃይለስላሴ ከፍ ያለ እውቅናን አገኙ
ኢትዮጵያዊው ፓሌዮአንትሮዮሎጂስት ዶ/ር ዩሐንስ ኃይለስላሴ በኒው ሜክሲኮ ዩኒቨርስቲ ስር በሚገኘው ጆርናል ኦፍ አንትሮፖሎጂካል ሪሰርች (Journal of Anthropoligical Research) በሚዘጋጀው ጃር ሌክቸር ሲሪስ (JAR Lecture Series) ላይ በተጋባዥ ተናጋሪነት እንዲገኙ መመረጣቸውን ዩኤንኤም ኒውስሩም (UNM Newsroom) ዘገበ። እንደዘገባው ከሆነ ከ3.8 ሚልዮን በላይ አመታትን ያስቆጠረውን የአውስትራሎፒትከስ አናሜንሲስ (Australopithecus anamensis) ቅሪት በማግኘት ከፍተኛ ታዋቂነትን ያተረፉት ዝነኛው ኢትዮጵያዊ አርኪዮሎጂስት ዶ/ር ዮሐንስ በፊታችን መስከረም 13 ቀን 2013 ዓ.ም A new face to an old name: Recent discovery of a cranium of the earliest Australopithecus in Ethiopia በተሰኘ ርዕስ ዙርያ በተሰናዳው ቨርችዋል ሌክቸር ላይ ስራቸውንና በአንትሮፖሎጂ ዘርፍ ላይ በሚያጠነጥኑ የተለያዩ ጉዳዮች ዙርያ ይናገራሉ ተብሎ ይጠበቃል።  ባሳለፍነው ታህሳስ 2012 ዓ.ም ኔቸር (Nature) የተሰኘው ጆርናል በሳይንስ አለም ትልቅ ድርሻ ካላቸው አስር ተመራማሪዎች ዝርዝር ውስጥ ያካተታቸው ኢትዮጵያዊ የፓሌዮአንትሮፖሎጂ ባለሙያ ዶ/ር ዮሐንስ ኃይለስላሴ በተጠቀሰው ዝግጅት ላይ ለመናገር በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ለኒው ሜክሲኮ ዩኒቨርስቲ ኒውስሩም የገለፁ ሲሆን ዘገባው አክሎም በጆርናሉ በሚዘጋጀው ሌክቸር ላይ ከዚህ ቀደም የተናገሩ የሳይንስ ሊቆች በመጥቀስ የእውቅናውን ግዝፈት አስረድቷል። ከተጠቀሱት የሳይንስ ተመራማሪዎች መካከል የዬል ዩንቨርስቲዋ ፓሌዮአንትሮፖሎጂስት ዶ/ር ኤልሳቤት ቭርባ (Dr. Elsabeth S. Vrba), የሉሲን ቅሪተ አካል ያገኙት ዶ/ር ዶናልድ ጆሀንሰን (Dr. Donald Johanson) እና የሚሺጋን ዩኒቨርቲው የአንትሮፖሎጂ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሎሪንግ ብሬስ (Dr. Loring Brace) ይገኙበታል። ከኒው ሚክሲኮ ዩንቨርስቲ ድህረ ገፅ መረዳት እንደሚቻለው ጆርናል ኦፍ አንትሮፖሎጂካል ሪሰርች (Journal of Anthropoligical Research) በፕሮፌሰር ሌዝሊ ስፒየር (Proff. Leslie Spier) በ1938 ዓ.ም ከተመሰረተ ጀምሮ በዪንቨርቲው የሚታተም የሳይንስና ምርምር ህትመት ሲሆን ከ50 በላይ በሚሆኑ አገራት ውስጥ የሚሰራጭ በተለይም በአንትሮፖሎጂ ዘርፍ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ትምህርታዊ ህትመት ነው።  

አስተያየት