የካቲት 1 ፣ 2011

በመገንባት ላይ የሚገኙት የንግድ ሱቆች ህገወጥ መሆናቸው ተገለፀ

ወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎች

በአዲስ አባባ ከቆርቆሮ እና ከላስቲክ የተሰሩ ሱቆች ከከተማው ኘላን ውጪ እንዲሁም ህግን ያልተከተሉ መሆናቸውን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሀላፊ ለአዲስ…

በመገንባት ላይ የሚገኙት የንግድ ሱቆች ህገወጥ መሆናቸው ተገለፀ
በአዲስ አባባ ከቆርቆሮ እና ከላስቲክ የተሰሩ ሱቆች ከከተማው ኘላን ውጪ እንዲሁም ህግን ያልተከተሉ መሆናቸውን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ሀላፊ ለአዲስ ዘይቤ ገልጸዋል ፡፡እነዚህን ሱቆች ሰጥተዋል የተባሉ የአዲስ ከተማ ሀላፊዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ምንጫችን ጨምረው ገለፀዋል፡፡በአዲስ አበባ ከሶስት ዓመታት በፊት ስልጠና ወስደው ያለስራ ለተቀመጡ ወጣቶች የተሰጡት የንግድ ሱቆች ፈጣን የግንባታ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛል፡፡እንደ ወጣቶቹ አገላለጽ "የግንባታ ቁሳቁሱ ከእንጨት እና ከዳስ አሊያም ከቆርቆሮ የሆነበት ምክንያት ውሉ ከሁለት ዓመት በኃላ ሲቋረጥ የሚሰጠውን የካሳ መጠን ለመቀነስ ታስቦ ነው፡፡" ብለዋል፡፡የንግድ ቦታዎችን በሚመለከት ከዚህ ቀደም የሚቆጣጠረው የመስሪያ ቦታዎች ማስፋፊያ እንደሆነ ነገር ግን የአዲስ አበባ ም/ ከንቲባ ታከለ ኡማ የከተማዋን ጽ/ቤቶችን ሲቀንሱ ወደ ጥቃቅንና አነሰተኛ መዘዋወሩን ያገኘነው ጠቁሟል ፡፡ጉዳዩን በተመለከተ የሚመለከታቸውን መ/ቤቶች ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም፡፡

አስተያየት