የካቲት 11 ፣ 2011

በጅግጅጋ ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመክፈት የመሰረት ድንጋይ መቀመጡ ተገለፅ

ወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎች

ጅግጅጋ ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብቻ ነው ያሏት። ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ተገኝተው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት…

በጅግጅጋ ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመክፈት የመሰረት ድንጋይ መቀመጡ ተገለፅ
ጅግጅጋ ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ብቻ ነው ያሏት። ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ተገኝተው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመክፈት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። 20 ሚልየን ብር የሚያወጣው ይህ ት/ቤቱ በአንድ አመት ይጠናቀቃልም ተብሏል።የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ መሀመድ ኡመር "ሁለት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብቻ ባለበት በሶማሌ ክልል ይሄን ለማሰራት ቀዳማዊት እመቤቷ በማምጣታቸው ትክክለኛ እና ተገቢ ነው።" ብለዋል።"በሀገራችን ያለውን የት/ቤት ቁጥርን መሰረት በማድረግ እንቅቃሴ ጀምረናል" ያሉት ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው "ጅግጅጋም በእቅድ ውስጥ ካሉት ክልሎች መካከል ናት።" ብለዋል።

አስተያየት