የካቲት 12 ፣ 2011

አቅምን ያገናዘበ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች የሚመች መኪና ለስምንተኛ ጊዜ በጅግጅጋ በሚከበረው ፎረም ላይ ለተመልካች ቀረበ።

ወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎች

ተሽከርካሪ የሰራው ባለ ብሩህ አዕምሮው ከወላይታ- "ከውጪ የሚገቡ መኪኖች ውድ መሆናቸው እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ከግምት ያላስገባ ተሽከርካሪ አለመኖር…

አቅምን ያገናዘበ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች የሚመች መኪና ለስምንተኛ ጊዜ በጅግጅጋ በሚከበረው ፎረም ላይ ለተመልካች ቀረበ።
ተሽከርካሪ የሰራው ባለ ብሩህ አዕምሮው ከወላይታ- "ከውጪ የሚገቡ መኪኖች ውድ መሆናቸው እንዲሁም አካል ጉዳተኞችን ከግምት ያላስገባ ተሽከርካሪ አለመኖር ይሄን ተሽከርካሪ ለመስራት ችያለሁ።"አጃዬ ማጆር በወላይታ ዞን አረካ ከተማ የ10ኛ ክፍል ተማሪ ነው። አቅምን ያገናዘበ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች የሚመች መኪና በመስራት ለስምንተኛ ጊዜ በጅግጅጋ በሚከበረው ፎረም ላይ ለተመልካች አቅርቧል።በአንድ ሊትር እስከ 40 ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚችለው ተሽከርካሪው መኪናው በአካባቢ በሚገኙ ብረታ ብረቶች ተስርቷል። እስከ 60 ሺህ ብር ወጪ እንዳወጣና ይሄንንም ከቤተሰብ እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ድጋፍ እንዳገኘ አጃዬ ይናገራል።አሁን ባለው የመኪና ገበያ ከ 300 ሺህ ብር በላይ እንደሚሸጥ በዚህ ንግድ ላይ የተሰማሩት ባለሞያዎች ይናገራሉ። ስለዚህ እነዚህን መኪኖች እዚህ ብናመርት ይሄን ገንዘብ በሁለት እጥፍ መቀነስ እንደሚቻል የብሩህ አእምሮው ባለቤት ያስረዳል።"አንድን ነገር መስራት አንችልም ብለን ከምንቀመጥ ሞክረን ያቃተን ምን እንደሆነ ስናውቀው በቀጣይ ማድረግ ያለብንን እንድናውቅ ይረዳናል። ስለዚህ ማድረግ የማንችለው ነገር የለም የሚለው አስተሳሰብ እንድናዳብር ይረዳናል። እኔንም የረዳኝ ይሄ አመለካከቴ ነው። " ሲል የእድሜ እኩዮቹን ይመክራል።ይሄን የፈጠራ ችሎታውን በአዕምሮአዊ ንብረት እውቅና ለማግኘት ከክልል መስተዳደሩ ጋር እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጾ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ የሚያደርግለት ከተገኘ ከዚህ የተሻለ ተሽከርካሪ መስራት እንደሚቻል በልበ ሙሉነት ይናገራል።

አስተያየት