You can paste your entire post in here, and yes it can get really really long.
የስኳር ድንች ገበያ አሁን ባለው የእድገት ደረጃ ሚቀጥል ከሆነ ከ2013 እስከ 2020 ድረስ ውጤታማ እየሆነ እንደሚቀጥል ግሎባል ሪፖርት (Global Report) ያወጣው መረጃ ላይ ገለፀ። ምርምሩ የስኳር ድንች ገበያ አሁን ያለውን ይዘት እና ወደፊት ሚቀጥልበትን አዝማሚያ የሚተነትን ሲሆን በተጨማሪም የስኳር ድንች ገበያን ስለሚያንቀሳቅሱት ሰዎች እና የኢንዱስትሪው ባለሞያዎች ስለሚያስተውሉት የገበያ ሁኔታ ተገልጿል።በምርምር ሪፖርቱ መሰረት በስኳር ድንች ገበያ አለማችን ላይ ትልቁን ሚና እየተጫወቱ ያሉት አገራት ቻይና፣ አሜሪካ፣ ታንዛኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ኢንዶኔዥያ፣ አንጎላ፣ ዮጋንዳ፣ ቪየትናም፣ ማዳጋስካር፣ ህንድ እና ኢትዮጵያ ናቸው። በሪፓርቱ ላይ ገበያው በአይነት ሲከፋፈል ትኩስ እና በረዶ የያዘ ስኳር ድንች በመባል ይጠራል። የገበያው ሂደት ክፍፍል በበኩሉ የንግድ ምግብ ኢንዱስትሪ፣ ለቤት የሚገዙ እና መመገቢያ ቦታዎች የሚያቀርቧቸው ተብሎ ተከፋፍሏል።ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የስኳር ድንች ገበያ ተስፋፍቷል። ከዚህ መካከል በአዲስ አበባ ከተማ የስኳር ድንች ሽያጭ ላይ የተሰማሩት ወ/ሮ ከበቡሽ ብርሃኔ ለአዲስ ዘይቤ በገለፁት መሰረት የስኳር ድንች ገበያ ከበፊቱ ብዙም ለውጥ የለውም ብለው በአሁኑ ወቅት የአስር ፍሬ ስኳር ድንች ዋጋ ሀያ ብር እንደሆነ ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል። ወ/ሮ ከበቡሽ አክለውም ስኳር ድንች ከሌላው ጊዜ የበለጠ በፆም ወቅት የበለጠ ፍላጎት እንደሚያሳይ ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።