You can paste your entire post in here, and yes it can get really really long.
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የአመራር አባል ዶ/ር ጌታሁን ካሳ በራሳቸው ፈቃድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመልቀቅያ ደብዳቤን እንዳስገቡና ከትላንትናው ቀን ጀምሮ የምርጫ ቦርዱ አካል እንደማይሆኑ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በይፋዊ የፌስቡክ ድህረ ገፅ ላይ ባሰፈረው መለዕክት አስታወቀ። በትላንትናው እለት በገፁ ላይ በሰፈረው መልዕክት መሰረት ዶክተሩ በራሳቸው ፈቃድ ከአባልነታቸው ራሳቸውን ያገለሉ ሲሆን ይህን ውሳኔ በወሰኑበት ምክንያት ዙርያ ምንም አይነት መረጃ ከቦርዱም ሆነ ከዶ/ር ጌታሁን አልቀረበም።የኢትዮጵያ መንግስት የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት የአገሪቱን ጤና ሚንስቴርን ምክረ ሀሳብ ከሰማ ወዲህ ባለፈው ሳምንት ስድስተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ እንዲካሄድ ከወሰነ ሳምንት እንኳን ሳይሞላው ዶ/ሩ ራሳቸውን ከስልጣን ማግለላቸው ብዙ አንድምታን የሚፈጥር ሊሆን ቢችልም አዲስ ዘይቤ ግን በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ ባለሙያዎች ጋር በመምከር የሚከተለውን ትንተና ሰጥታለች።የመጀመርያው ጥያቄ ውሳኔው በምርጫውና በምርጫው ይዘት ላይ ሊያመጣ የሚችለው አንድምታ አለ ወይ ብሎ መጠየቅ ነው። በዚህ ዙርያ አዲስ ዘይቤ ያናገራቸው የሰብአዊ መብት ጠበቃው አቶ አምሀ መኮንን “የዶክተር ጌታሁን ውሳኔ አዲስ ነገር አይደለም። የቦርዱ አባላት በግል ጉዳይ ቦርዱን የመልቀቅ ሙሉ መብት አላቸው። ዶክተሩም የራሳቸው እቅድ ይኖራቸዋል።” በማለት ውሳኔው በምርጫው ላይ ይህ ነው የሚባል ተፅዕኖ ይኖረዋል ብለው እንደማያስቡ ተናግረዋል። አክለውም ምንም እንኳን የውሳኔው ፖለቲካዊ አንድምታ ብዙ ባይሆንም ከተአማኒነትና ከአሰራር አንፃር ቦርዱ በአፋጣኝ የዶክተሩን ቦታ መሙላት ይጠበቅበታል በማለት ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።የፖለቲካ ሳይንስ ባለሙያ ወ/ሮ ሀና ስምኦን ከአቶ አምሀ ጋር ይስማማሉ። “በርግጥ የዶክተሩ መልቀቅ ቦርዱ ውሳኔ በሚወስንበት ወቅት ቴክኒካዊ ችግሮችን ሊፈጥርበት ይችላል። ከዛ ባለፈ ግን አንድ የምርጫ ቦርድ አባል ራሱን ማግለሉ ምክንያቱ ባልታወቀበት ሁኔታ መላምቶችን ከማስቀመጥ ባለፈ ወደ ሚዛናዊ ድምዳሜ አይወስድም።” በማለት የ[gallery columns="3"][gallery columns="3"]ምርጫ ቦርድም ሆነ ከዶክተሩ ስለለቀቁበት ምክንያት ግልፅ መረጃ ባለመኖሩ ውሳኔው በዚህ ወቅት በምርጫው ላይ ፖለቲካዊ አንድምታን ይኖረዋል ለማለት አያስችልም ብለዋል። ወ/ሮ ሀና አክለውም “ገና ቀነ ገደብ ያልወጣለት ምርጫ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም።” በማለት የተናገሩ ሲሆን ምርጫው እስከ አመቱ መጨረሻ ላይካሄድ መቻሉንና የምርጫ ቦርድ በኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ሳቢያ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎችን ስለሚያደርግ የዶክተር ጌታሁን ቦታ በተገቢው ሁኔታና በገለልተኛ ግለሰብ እስከተተካ ድረስ ይህ ውሳኔ ምርጫው በመካሄዱም ላይ ሆነ በምርጫው ይዘት ላይ የሚያመጣው አንድምታ አለ ማለት ለእርሳቸው ውሀ የማይዝ ክርክር እንደሆነ ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።የተወካዮች ምክር ቤት በመስከረም 8 2013 ዓ.ም የቀረበውን የኢፌድሪ የጤና ሚንስቴር ሪፖርትን ተከትሎ የኢትዮጵያ ስድስተኛ ብሄራዊና ክልላዊ ምርጫዎች ትግራይ ክልልን ጨምሮ በአስሩም የክልል መንግስታትና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች እንዲካሄድ መወሰኑ የሚታወስ ነው። ምርጫው አሁንም መቼና በምን ሁኔታ እንደሚካሄድ ከመንግስት አካላትም ሆነ ከምርጫ ቦርድ የተሰጠ ማብራርያ ባይኖርም ስድስተኛው አገራዊና ክልላዊ ምርጫ በያዝነው አመት እንደሚካሄድ ግን የተለያዩ መረጃዎች ያስረዳሉ።