You can paste your entire post in here, and yes it can get really really long.
በአህጉረ አፍሪካ ከ44,000 በላይ በኢትዮጵያ ደግሞ ከ3,300 በላይ የጠፉ ሰዎች እንደሚገኙ የአለም የቀይ መስቀል ድርጅት ዛሬ ይዞት በወጣው ዘገባ አስታወቀ። ዘገባው የወጣው በፊታችን እሁድ የሚከበረውን የአለም የጠፉ ሰዎች ቀን በማስመልከት ሲሆን እንደዘገባው ከሆነ በአፍሪካ ከ44,000 በላይ ሰዎች መገኛቸው የማይታወቅ ሲሆን የጠፉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥርም በብሄር ግጭትንና በስደት ምክንያት ከፍ ማለቱን ዘገባው ያስረዳል። የአለም የቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ ከ3,300 በላይ የጠፉ ሰዎችን ስም መመዝገቡን የገለፀ ሲሆን ከተጠቀሰው ቁጥር 64 በመቶ የሚሆኑት ህፃናትና ሴቶች መሆናቸውን በዘገባው አክሎ አስቀምጧል።አህጉራዊ ቁጥሮችእንደዘገባው ከሆነ ናይጄርያ ከ22,000 በላይ የሚሆኑ የጠፉ ሰዎችን በማስመዝገብ ከአፍሪካ ከፍተኛ የጠፉ ሰዎች ቁጥር የተመዘገበባት አገር ስትሆን ከተመዘገቡት የጠፉ ሰዎች መዝገቦች ከ90 በመቶ በላይ የሚሆኑት በአገሪቱ ሰሜን ምስራቃዊ ክፍል ከሚገኘው ግጭት የመነጩ እንደሆኑ ዘገባው አክሎ አስቀምጧል።ናይጄርያን በመከተል ደቡብ ሱዳን ከ5,000 በላይ የተመዘገቡ የጠፉ ሰዎች መዝገቦች ያሉባት አገር ስትሆን፣ ሶማልያ ከ3,200 በላይ፣ በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከ1,800 በላይ፣ በሊብያ ከ1,600 በላይ እንዲሁም በካሜሩን ከ1,500 በላይ የጠፉ ሰዎች እንደሚገኙ ኮሚቴው ተናግሯል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ከላይ የተጠቀሱት አገራት የአህጉሪቱን የጠፉ ሰዎች ቁጥር 82 በመቶ እንዳስመዘገቡ ዘገባው አክሎ ያስረዳል።ኮሮና ቫይረስ እና የኮሚቴው ስራየኮሮና ቫይረስና በተያያዥነት የሚመጡ የተለያዩ ተቋማዊና ማህበረሰባዊ ለውጦች በኮሚቴው ስራ ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳመጣ ኮሚቴው የገለፀ ሲሆን በወረርሺኙ ወቅት የጠፉ ሰዎችን በመፈለግ ስራ ላይ አስፈላጊ የሆኑ የመፈለግያ መንገዶችን በማህበራዊ ርቀት ምክንያት ማድረግ ባለመቻሉ ሰዎችን የማግኘቱ ስራ የበለጠ ከባድ እንዲሆን ማድረጉን የአለም የቀይ መስቀል ኮሚቴ ገልጿል።አለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ከላይ ያስቀመጠው ቁጥር በድርጅቱ የተመዘገቡትን ብቻ የሚወክል መሆኑንና በድርጅቱ ያልተመዘገቡ የጠፉ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ በሪፖርቱ አስታውቋል።