ነሐሴ 20 ፣ 2012

የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ሬድዋን ሁሴን ለእንግሊዝ መንግስት ቅሬታ አቀረቡ

ወቅታዊ ጉዳዮችዜናዎችቪዲዮ

በትላንትናው እለት በለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ላይ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን አርማና መፈክር ባነገቡ ሰልፈኞች የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የኢትዮጵያ…

የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ ሬድዋን ሁሴን ለእንግሊዝ መንግስት ቅሬታ አቀረቡ
በትላንትናው እለት በለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ላይ የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን አርማና መፈክር ባነገቡ ሰልፈኞች የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በውጪ ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሬድዋን ሁሴን በኩል በኢትዮጵያ ለሚገኘው የእንግሊዝ ኢምባሲ አቤቱታ ማቅረቡን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዘገበ። ጥቃቱን የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በተለያዩ ማህበራዊ ድህረገጾች በመሰራጨት ላይ የሚገኝ ሲሆን በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ አንድ ግለሰብ በኢምባሲው ላይ የተሰቀለውን የኢትዮጵያ ባንዲራ በማንሳት የኦነግን ባንዲራ ሲሰቅል ይታያል።እንደዘገባው ከሆነ ሚንስትር ዴኤታዉ በትላንትናው እለት ከእንግሊዝ ኢምባሲ ከፍተኛ ባለስልጣን አሌክስ ካሜሮን ጋር የተገናኙ ሲሆን አቶ ሬድዋን በዲፕሎማስያዊ ግንኙነትን ዙርያ የወጣውን የ1953ቱ የቪዬና ስምምነት በማስታወስ የእንግሊዝ መንግስት ለኢምባሲው ተገቢውን ጥበቃ የማድረግ ግዴታ እንዳለበት አስታውሰዋል። የእንግሊዝ ኢምባሲን በመወከል አሌክስ ካሜሮን በበኩላቸው ለተገጠረው ጥቃት ይቅርታ ከጠየቁ በኋላ በስምምነቱ መሰረት የእንግሊዝ መንግስት ለኢትዮፕጵያ ኢምባሲ ተገቢውን ጥበቃ እንደሚያደርግ ቃል እንደገቡ ዘገባው በተጨማሪ ያስረዳል። በጉዳዩ ዙርያ አዲስ ዘይቤ ሚንስትር መስሪያ ቤቱንና የእንግሊዝ ኢምባሲን ለማነጋገር ቢሞክርም ምላሽ ሳያገኝ ቀርቷል።በለንደን በሚገኘው የአፄ ኃይለሥላሴ ሀውልት ላይ ባሳለፍነው የሐምሌ ወር ማንነታቸው ባልታወቀ ሰልፈኞች ጥቃት እንደደረሰበት የሚታወስ ነው።

አስተያየት