ነሐሴ 20 ፣ 2012

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንግስት ባስቸኳይ ሊፈፅማቸው የሚገቡ ተግባራት እንዳሉ አስታወቀች

ዜናዎች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በተከቷዮቿና በደብሮቿ ላይ አነጣጥሮ የተፈጸመ ነው ያለችውን ጥቃት በተመለከተ ዛሬ…

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንግስት ባስቸኳይ ሊፈፅማቸው የሚገቡ ተግባራት እንዳሉ አስታወቀች
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በተከቷዮቿና በደብሮቿ ላይ አነጣጥሮ የተፈጸመ ነው ያለችውን ጥቃት በተመለከተ ዛሬ መግለጫ ሰጥታለች። መግለጫው ጥቃት የተፈጸመባቸውን አካባቢዎች ተዘዋውሮ በጎበኘው የቤተ ክርስቲያኒቱ ልኡካን ቡድን ቀዳሚ ሪፖርት ላይ የተመሰረተ ሲሆን ከድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ሁከት ስድሳ ሰባት ምዕመናን እንደተገደሉባት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስታውቃለች።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተፈጠረው ሁከት ምክንያት ተጎድተዋል ወደ ተባሉ አካባቢዎች ተሰማርታ ምልከታ ካካሄደች በኋላ በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት በሰጠችው መግለጫ መሰረት ከድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ፣ በሐረሪ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር በተፈጠረ ሁከት 67 ምዕመናን ሲገደሉ ከ7 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።በአጠቃላይም ሁከቱን መነሻ በማድረግ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምዕመናን ንብረት መውደሙም በመግለጫው ላይ ተገልጿል። በኦሮሚያ ክልል፣በድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር እና በሌሎች አካባቢዎች ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ እንደ ሰውም አስክሬናቸው በክብር አልተቀበረም ፣ ሴቶች በባለቤታቸው፣በወንድምና በአባታቸው ፊት መደፈራቸው በምልከታ መረጋገጡ በመግለጫው ላይ የተገለፀ ሲሆን በጉዳት ጥናት መረጃው መሰረት ጊዜያዊ እርዳታን ከማድረስ እና ከመልሶ ማቋቋም ባሻገር መንግስት ባስቸኳይ ሊፈፅማቸው የሚገቡ ተግባራት እንዳሉ እንደሚያምን ዐብይ ኮሚቴው ገልፅዋል።

አስተያየት