ጥር 17 ፣ 2014

ዲያጂዮ የሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን ለ ቢ.ጂ.አይ ለመሸጥ ስምምነት ላይ ደረሰ

ዜና

ዲያጂዮ በኢትዮጵያ የሚሰጠውን አገልግሎት በሚያስመጣቸው ምርቶቹ እንደሚቀጥልም በመግለጫው አስታውቋል።

Avatar: Addis Zeybe
አዲስ ዘይቤ

የኢትዮጵያን አስደናቂ የከተማ ባህል፣ ታሪክ፣ ወቅታዊ ዜና እና ሌሎችንም ያግኙ።

ዲያጂዮ የሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን ለ ቢ.ጂ.አይ ለመሸጥ ስምምነት ላይ ደረሰ

ዲያጂዮ ሰበታ የሚገኘውን ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካን ለ ቢ.ጂ.አይ ለመሸጥ ስምምነት ላይ መድረሱን ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ። ሜታ አቦ የካስቴል ግሩፕ አካል ለሆነው ቢ.ጂ.አይ የተሸጠበት የዋጋ መጠን እስካሁን ይፋ ያልተደረገ ሲሆን ስምምነቱ ሙሉ ለሙሉ በተያዘው የግሪጎሪያን አዲስ አመት መጀመሪያ ላይ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

ሜታ አቦ ቢራ ፋብሪካ ለእንግሊዙ ዲያጂዮ በ 255 ሚሊየን ዶላር በ 2004 ዓ.ም. በመሸጥ ወደ ግል ይዞታነት የተዛወረ ሲሆን ፋብሪካው ላይ ተጨማሪ የማስፋፊያ ስራ ለመስራት ዲያጂዮ 119 ሚሊየን ዶላር ኢንቨስት አድርጓል። በተጨማሪም በ 2013 ዓ.ም. የማልት መጠጦች ፋብሪካውን ለማስፋፋት 14 ሚሊየን ዶላር ወጪ አድርጓል።

ዲያጂዮ በኢትዮጵያ የሚሰጠውን አገልግሎት በሚያስመጣቸው ምርቶቹ እንደሚቀጥልም በመግለጫው አስታውቋል።

ዲያጂዮ የአልኮል፣ ቢራና የወይን መጠጦችን በማምረት ግንባር ቀደም የእንግሊዝ ኩባንያ ሲሆን፣ ጆኒዎከር፣ ክራውን ሮያል፣ ስሚርኖፍ፣ ካፒቴን ሞርጋን፣ ጊነስና ሌሎች ምርቶቹ ይታወቃል።

የካስቴል ግሩፕ አካል የሆነውና ሜታ አቦን ለመግዛት ስምምነት ላይ የደረሰው ቢ.ጂ.አይ ከሃገሪቱ የቢራ ገበያ ከ50% በላይ ድርሻ ያለው ድርጅት ነው። ቢ.ጂ.አይ በአዲስ አበባ፣ ሐዋሳ፣ ወልቂጤ፣ ኮምቦልቻና ራያ ከተሞች ግዙፍ የቢራ ፋብሪካዎች እንዲሁም በዝዋይ የሚገኘውን የወይን እርሻና ወይን መጥመቂያ ፋብሪካ በባለቤትነት ያስተዳድራል። 

አስተያየት