ታህሣሥ 28 ፣ 2013

ቅኝት፡ ዶሮ 600 ብር ገብቷል

ከተማ

በኢትዮጵያ ክርስትና እምነት ተከታዮች የገና በዓል ሊከበር የቀረው አንድ ቀን ብቻ ነውና ገበያው ተሟሙቆ  የበዓል ሸመታው በየአካባቢው ደርቷል።

Avatar: Mohammed Hassen
Mohammed Hassen

journalism and communications graduate and an expert in communications affairs in the region and mobile journalist at Addis Zeybe.

Workineh Diribsa

I am Workineh, lecturer and researcher at Jimma University; journalist/correspondent for Addis Zeybe media.

ሊዲያ ፍቅሩ

Lidiya Firkru is a mobile journalist from Dire Dawa city at Addis Zeybe

Gezahegn Berhe

Stationed at Bahir Dar city, Gezahgn Berhie is a staffer at Addis Zeybe. He is also an educator of journalism and communication at Bahir Dar University.

ሰላም ፍሰሃ

Selam Fisseha is a graduate of Addis Ababa University Law School and a Mobile Journalist from Addis Ababa at Addis Zeybe.

ተስፋ በላይነህ

Tesfa Belayneh is a mobile journalist from the city of Gondar, working at Addis Zeybe

ቅኝት፡ ዶሮ 600 ብር ገብቷል

በኢትዮጵያ ክርስትና እምነት ተከታዮች የገና በዓል ሊከበር የቀረው አንድ ቀን ብቻ ነውና ገበያው ተሟሙቆ  የበዓል ሸመታው በየአካባቢው ደርቷል።

አዲስ ዘይቤም የገበያው ሁኔታ ምን ይመስላል የሚለውን ለማስቃኘት በተለያዩ ከተሞች ያለውን የገበያ ሁኔታ ተዟዙራ ተመልክታለች።

በጅማ ብሺሼ ገበያ አንድ ኪሎ ቀይ ሽንኩርት በ20ብር፣ ነጭ ሽንኩርት በኪሎ 150ብር፣ አንድ ኪሎ ቲማቲም በ25ብር፣ አንድ ኪሎ ቅቤ በ250ብር እንዲሁም አንድ እንቁላል በ5 ከ50 ሳንቲም እየተሸጠ እንደሆነ የጅማ ሪፖርተራችን ወርቅነህ ድሪብሳ ቅኝቱን አጋርቶናል።

በተመሳሳይ መልኩ አንድ ኪሎ የበሬ ስጋ 250ብር፣ አንድ ኪሎ የበግ ስጋ በ300ብር፣ ዶሮ በ350ብር፣ በግ በ3000ብር፣ በሬ በ18ሺ እየተሸጠ ይገኛል፡፡

ከወትሮዋ ሞቅ ደመቅ ባለችው በጎንደር ቅዳሜ ገበያ ደግሞ ዶሮ እንደ መጠኑ ከ150 ብር እስከ 350 ብር እየተሸጠ መሆኑን የጎንደር ሪፖርተራችን ተስፋ በላይነህ ነው ያጋራን::

እንዲሁም እንቁላል ከ 4 ብር እስከ 5 ብር ፣ በግ ከ1700 እስከ 3000 ብር ሲሸጥ በአትክልት ተራ ደግሞ ቃሪያ በኪሎ 38 ብር ሽንኩርት ከ16 እስክ 18 ብር እየተሽጠ ይገኛል።

የድሬዳዋ ቀፊራ ገበያ ደግሞ ዶሮ ከ200 እስክ 300 ብር እየተሸጠባት ይገኛል። በከተማዋ አትክልት በኪሎ ተሰፍሮ የሚሸጥ ቢሆንም በአብዛኛው የተለመደው ግን በእጅ ማስታጠቢያ እየተሰፈረ መሆኑን የድሬዳዋ ሪፖርተራችን ሊዲያ ፍቅሩ አጫውታናለች ።

እናም ቀይ ሽንኩርት በማስታጠቢያ 150 ብር፣ ቲማቲም በማስታጠቢያ 120 ብር ፣የአንድ ኪሎ  በርበሬ ዋጋ የተፈጨ 360 ብር ዛላው ደግሞ 180 ብር እንዲሁም አንድ እንቁላል በ7 ብር እየተሸጠ ይገኛል። 

በባህር ዳር ... ገበያ አንድ ኪሎ ቀይ ሽንኩርት 17 ብር፣ ቲማቲም 20 ብር፣ ነጭ ሽንኩርት በኪሎ ከ80 እስከ 85 ብር ግብይት እየተደረገ ነዉ፡፡

በአመዛኙ ዶሮ ከ180 እስከ 400 ብር፤ በግ ከ2 ሺህ እስከ 7ሺህ፣ አንድ ኪሎ ቂቤ 250 ብር እንዲሁም እንቁላል እስክ 5 ብር እየተሸጠ እንደሆነ የባህርዳር ሪፖርተራችን ገዛኸኝ በርሄ ዘግቧል፡፡ የበሬ ዋጋም እንዲሁ ከ9ሺህ ብር ጀምሮ ሲሆን በተለይ የደለበ እስከ 22ሺህ ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጅግጅጋ ሴይላዳ ገበያ የበግ ወጋ ከ3000 እስከ 3800 ብር ድረስ የሚገኝ ሲሆን የፍየል ዋጋ ደግሞ ከ4000 እስከ 4300 ድረስ እየተሸጠ ይገኛል።

የዶሮ ዋጋን በተመለከተ ከ480 ብር እስከ 600 ብር ድረስ በመሸጥ ላይ ይገኛሉ። የእንቁላል ዋጋ 6 ብር ሲሆን ቲማቲም በኪሎ 24 ብር ፣ነጭ ሽንኩርት በኪሎ 120 ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል። እንዲሁም ቂቤ  250 ብር እየተሸጠ እንደሆነ የዘገበው የጅግጅጋ ሪፖርተራችን መሃመድ ሃሰን ነው።

በሃዋሳ በተለምዶ አሮጌው ገበያ በሚባለው ደግሞ ቀይ ሽንኩርት በኪሎ 14 ብር ሲሆን ነጭ ሽንኩርት 90 ብር፣ ኮርሪማ 180 ብር፣ ቂቤ እስከ 350 ብር፣ እንቁላል የፈረንጅ 5 ብር የሃበሻ በ6 ብር እየተሸጠ እንደሆነ የአዲስ ዘይቤ የሃዋሳ ሪፖርተር ሙሉነህ ካሳ ዘግቧል።

ዶሮ ከ200 እስክ 450 ብር፣ በግ 1600 ብር እስከ 3900 ብር፣ ፍየል 1800 እስከ 4300 ብር ሲሸጥ በሬ ደግሞ ከ15 እስከ 40ሺህ ብር እየተሸጠ ይገኛል።

በመዲናችን አዲስ አበባ በሾላ ገበያ ደግሞ የበግ ገበያው ከ3500 እስከ 5800 ብር ድረስ የሚገኝ ሲሆን የፍየል ዋጋ ደግሞ ከ4500 እስከ 5800 ድረስ ይገኛል።

የዶሮ ዋጋን በተመለከተ ከ380 ብር እስከ 550 ብር ድረስ በመገበያየት ላይ ይገኛሉ። የእንቁላል ዋጋ 4 ብር ከ75 ሳንቲም እየተሸጠ ይገኛል።

የአትክልት እና ቅቤ ገበያውን ስንመለከት ደግሞ የፈረንጅ ሽንኩርት ከ 17 ብር እስከ 20 ብር ሲሸጥ የሀበሻ ሽንኩርት ከ45 ብር እስከ 50 ብር፣ቲማቲም በኪሎ 25 ብር ፣ነጭ ሽንኩርት በኪሎ 100 ብር እንዲሁም ኮረሪማ ከ100 ብር እስከ120 ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል።

ቅቤ ከ320 እስከ 380 ብር ድረስ በመሸጥ ላይ እንደሆነም አዲስ ዘይቤ ተመልክታለች።

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰኢድ እንድሪስ ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፀው ድርጅቱ 2800 ሰንጋዎች፣ 3000 በጎች እኔ ፍየሎች ለእርድ ብቁ ናቸው ብሏል።

ከኮሮና ወረሽኝ ጋር በተያያዘ እየተወሰዱ ያሉ ጥንቃቄዎችን በተመለከተ ምን እየተደረገ ነው ለሚለው ጥያቄ አቶ ሰኢድ "የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ለሰራተኞቹ ተሰጥቷል። በተጨማሪም የኬሚካል ርጭት የተከናወነ ሲሆን ከስጋ ምርመራው በተጨማሪ የእርድ የፕሮግራሙም በሶስት ፈረቃ ተደርጓል። ይህ የተጠቃሚዎችን እንዲሁም የሰራተኞችን በአንድ ቦታ ተገኝቶ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ታስቦ የተሰራ ነው" ብሏል።

ወቅቱ የገና በአል በመሆኑ አዲስ ዘይቤ የቤት ማስዋቢያነት የሚያገለግል የገና ዛፍ ስንት ይሆን ብላ ጠይቃለች። እንደ ነጋዴዎቹ ከሆነ እቃው እስከ 1300 ብር ድረስ እንደሚሸጥ ሲሆን ረከስ የሚለው እንዲሁም በመጠን የሚያንሰው ደግሞ እስከ 950 ብር ድረስ እየተሸጠ መሆኑን የአዲስ አበባዋ ሪፖርተራችን ሰላም ፍሰሃ ነች የዘገበችው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በእነዚህ ሰባት ከተሞች ቅኝቷን ያደረገችው አዲስ ዘይቤ ህብረተሰቡ ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል ካለማድረግ በተጨማሪ ምንም አይነት ጥንቃቄ እየተደረገ እንዳልሆነ አስተውላለች ።

 

 

 

 

 

 

 

አስተያየት